TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UpdateSport መሀመድ ሳላህ የቢቢሲ የ2018 የአፍሪካ ምርጥ ተጨዋች ምርጫን አሸነፈ!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ ወደ ነገ 09:00 ተላለፈ። ዛሬ ሊደረግ የነበረው ይህ ጨዋታ በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች መካከል በተከሰተ #ረብሻ ሳይካሄድ ቀርቷል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የአውሮፓ ቻምፕዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ድልድል ይፋ ሆኗል...

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በስፔን ቫሌንሽያ በተደረገው የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር አትሌት ፀሓይ ገመቹ በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን የርቀቱን የኢትዮጵያ ርከርድ አሻሽላለች፡፡ ፀሓይ ገመቹ 30 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባትና በጥሩነሽ ተይዞ የነበረውን ሰዓት በ15 ሰከንድ በማሻሻል ነው ማሸነፍ የቻለችው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በ12ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ ዛሬ ሶስት ጨዋታዎች ሲከናወኑ፦ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የአማራ ደርቢ 0ለ0 በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡ ባሕርዳር ከነማን ከፋሲል ከነማ በባሕር ዳር አለማቀፍ ስታዲዮም ያገናኘው ጨዋታ ያለምንም ግብ ነው የተጠናቀቀው፡፡ በሌላ ጨዋታ በደቡብ ደርቢ ሀይቆቹን ሀዋሳ ከነማ ን ከደቡብ ፖሊስ ያገኛነው ጨዋታ በሀይቆቹ 3ለ2 በሆነ ውጤት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ ወልዋሎ አዲግራትን በሜዳው የጋበዘው አዳማ ከነማ 1ለ0 በሆነ ውጤት ድል አድርጓል፡፡

ፎቶ፥ ባሕር ዳር እና ፋሲል ከነማ
ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport አትሌት #ስንታየው_ለገሰ በዘንድሮው የናይጄሪያ ሌጎስ ማራቶን ለማሸነፍ ችሏል፡፡ ኢቢሲ ቫንጋርድን ጠቅሶ እንደዘገበው አትሌቱ ውድድሩን 2:17:26 በሆነ ሰአት 1ኛ ሆኖ በማጠናቀቁ የ50ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሆኗል፡፡ ኬኒያዊው አትሌት ጆሽዋ ኪፕኮሪር 2ኛ በመውጣት የ40 ሺህ ዶላር ተሸላሚ ሲሆን ሌላኛው ያገሩ ልጅ ዊሊያም የጉን 3ኛ በመውጣት የ30 ሺህ ዶላር ተሸልሟል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የቀድሞው የአርሰናል ክለብ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በሚቀጥለው ወር በአሰልጣኝነት ወይም የእግር ኳስ ዳይሬክተር በመሆን ወደ እግር ኳስ ስራቸው ሊመለሱ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ አርሰናልን ለ22 አመታት ያሰለጠኑት ፈረንሳዊው አርሰን ቬንገር ሶስት የፕሪሚየር ዋንጫ ካሸነፉበት የሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር የውድድር አመቱ ከመጀመሩ በፊት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡ እንደ ዘ ታይምስ ዘገባ አርሰን ቬንገር ከአራት ያላነሱ የቅጥር ጥያቄዎች የደረሷቸው ሲሆን ሁሉም ግን ከእንግሊዝ ክለቦች ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ አሰልጣኙ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ለመሩት አርሰናል ካላቸው ክብር የተነሳ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወት ተቃራኒ ክለብ ማሰልጠን አይፈለጉም ነው የተባለው፡፡ የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን ክለብ ከፖርቹጋላዊው የፓስ ሴንት ክለብ የእግር ኳስ ዳይሬክተር አንቴሮ ሄኔሪኬ ጋር መለያየቱን ተከትሎ አርሰን ቬንገርን ለቦታው እንደሚፈልገው ነው የተጠቆመው፡፡ ከፓሪሱ ክለብ ውጪ አንድ ስሙ ያልተገለፀ ብሄራዊ ቡድንም የአንጋፋውን አሰልጣኝ ግልጋሎት እንደሚፈልግ ታውቅል፡፡ አርሰን ቬንገር ለማራኪ እግር ኳስ ካላቸው ፍልስፍና ባየር ሙኒክ፤ኤሲ ሚላን እና ሪያል ማድሪድ በመሳሰሉ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ጋር ስማቸው ሲያያዝ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ዘ ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የመጀመሪያ ዙር የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ በPSG 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል። በሌላ ጨዋታ ደግሞ ሮማ በሜዳው ፖርቶን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport የ20 ዓመቱ ኢትዮጵያዊ #ሳሙኤል_ተፈራ በበርሚንግሐም የ1500 ሜትር የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር የዓለም ክብረ-ወሰን አሻሻለ። ሳሙኤል ውድድሩን በ3 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ከ04 ማይክሮ ሰከንድ ጨርሷል። ላለፉት 22 አመታት አይነኬ ሆኖ የቆየው እና በሞሮኳዊው ሒሻም ኤል ጎሩዥ ተይዞ የነበረው ክብረ-ወሰን 3 ደቂቃ ከ31 ሰከንድ ከ18 ማይክሮሰከንድ ነበር። ባለፈው ሳምንት ክብረ-ወሰኑን ለማሻሻል 0.01 ሰከንድ ብቻ ሲቀረው ውድድሩን ያጠናቀቀው ሌላው ኢትዮጵያዊ ዮሚፍ ቀጀልቻ ሁለተኛ ሆኖ አጠናቋል። ዮሚፍ በዚህ ውድድር የዓለም ክብረ-ወሰንን የማሻሻል ዕቅድ ነበረው። የአውስትራሊያው ስቴዋርት ማክስዌይን ውድድሩን በሶስተኛነት አጠናቋል። ሳሙኤል ውድድሩን ካሸነፈ በኋላ "ይኸን ማመን አልችልም። በውጤቱ ተደስቻለሁ። የዓለም ክብረ-ወሰን ባለቤት መሆን የተለየ ስሜት ይፈጥራል" ሲል ተናግሯል።

via dw
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport በበርኒግሀም የቤት ውስጥ ሩጫ ውድድር በሴቶች 3 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንደኛ እስከ አራተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀቁ፡፡ በዚህም #አልማዝ_ሳሙኤል በ8 ደቂቃ 54 ሰከንድ 60 ማይክሮሰከንድ አንደኛ ደረጃን በመያዝ  አጠናቅቃለች፡፡ #አክሱማዊት_እምባየ በ8 ደቂቃ 54 ሰከንድ ከ97 ማይክሮሰከንድ እና #መስከረም_ማሞ በ8 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ03 ማይክሮሰከንድ በመግባት ሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡ ሌላኛዋ #ኢትዮጵያዊ አትሌት #እጅጋየሁ_ታየ በ8 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ28 ማይክሮሰከንድ በመግባት የአራተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቅ ችላለች፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia