#UpdateSport የቀድሞው የአርሰናል ክለብ አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በሚቀጥለው ወር በአሰልጣኝነት ወይም የእግር ኳስ ዳይሬክተር በመሆን ወደ እግር ኳስ ስራቸው ሊመለሱ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡ አርሰናልን ለ22 አመታት ያሰለጠኑት ፈረንሳዊው አርሰን ቬንገር ሶስት የፕሪሚየር ዋንጫ ካሸነፉበት የሰሜን ለንደኑ ክለብ ጋር የውድድር አመቱ ከመጀመሩ በፊት መለያየታቸው ይታወሳል፡፡ እንደ ዘ ታይምስ ዘገባ አርሰን ቬንገር ከአራት ያላነሱ የቅጥር ጥያቄዎች የደረሷቸው ሲሆን ሁሉም ግን ከእንግሊዝ ክለቦች ውጪ መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ አሰልጣኙ ከሁለት አስርት አመታት በላይ ለመሩት አርሰናል ካላቸው ክብር የተነሳ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሚጫወት ተቃራኒ ክለብ ማሰልጠን አይፈለጉም ነው የተባለው፡፡ የፈረንሳዩ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን ክለብ ከፖርቹጋላዊው የፓስ ሴንት ክለብ የእግር ኳስ ዳይሬክተር አንቴሮ ሄኔሪኬ ጋር መለያየቱን ተከትሎ አርሰን ቬንገርን ለቦታው እንደሚፈልገው ነው የተጠቆመው፡፡ ከፓሪሱ ክለብ ውጪ አንድ ስሙ ያልተገለፀ ብሄራዊ ቡድንም የአንጋፋውን አሰልጣኝ ግልጋሎት እንደሚፈልግ ታውቅል፡፡ አርሰን ቬንገር ለማራኪ እግር ኳስ ካላቸው ፍልስፍና ባየር ሙኒክ፤ኤሲ ሚላን እና ሪያል ማድሪድ በመሳሰሉ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ጋር ስማቸው ሲያያዝ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ዘ ታይምስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia