TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ📞ዶናል ትራምፕ

ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በስልክ ተወያዩ። ሁለቱ መሪዎች በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ሕይወታቸውን ላጡ ዜጎች ቤተሰቦች የኀዘን መግለጫ ተለዋውጠዋል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጠንካራ ተቋም መሆኑን አድንቀው በተፈለገበት ቦታ ሁሉ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኝነታቸውን አስታውቀዋል። ፕሬዝዳንቱ በማስከተልም በኢትዮጵያ ባለፉት ወራት ለተካሄዱ ሁሉን አቀፍ ለውጦች ያላቸውን ድጋፍ ገልፀዋል። ሁለቱ መሪዎች ውይይታቸውን በሀገራቱ መካከል ያለውን ረጅም ጊዜ የዘለቀ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተው አጠናቅቀዋል።

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አህመድ የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ #ኳታር ገብቷል፡፡ የልዑካን ቡድኑ ዶሃ ሲደርስ የአገሪቱ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር፣ በኢትዮጵያ የኳታር አምባሳደር እንዲሁም በኳታር የኢትዮጵያ አምባሳደር አቀባበል አድርገውለታል፡፡

ምንጭ፡ በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው ሁሉ🔝

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ ስለማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ያስተላለፉት መልዕክት::

Via PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"አዲስ ወግ"🔝

በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አዘጋጅነት ትናንት የተጀመረውና ዛሬ ከሰዐት በኋላ በቀጠለውና የመጨረሻ በሆነው በሸራተን ሆቴል እየተካሄደ ባለው 'አዲስ ወግ' የተሰኘና ባለፈው አንድ አመት የመጣውን ለውጥ ብሎም ያጋጠሙ ፈተናዎችን በሚዳስሰው የውይይት መድረክ ''የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ማጽናት በኢትዮጵያ፤ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አካሄዶች'' በሚል ርዕስ ውይይት እየተካሄደ ነው። በውይይቱ ላይም የኢፌዲሪ ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ተገኝተዋል።

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኦዴፓ ለ29ኛ ዐመት ምስረታ በዓሉ ባወጣው መግለጫ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት የሚኖሩባት ሀገር ለመመስረት እታገላለሁ ብሏል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር #ዐቢይ_አሕመድ ዜጎች የእኔ ማለት ትተው የእኛ ማለት እንዲጀምሩ የሚል ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አሕመድ መጋቢት 19 ቀን 2011 ከአገር ውስጥና ከውጭ #ጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሾች👆

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ከሰጡት ምላሽ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦

• አዲስ አበባ የሁሉምናት እንጂ የአንዱ ብቻናት የሚለው ትክክል አይደለም።

• በህገመንግስቱ የተቀመጠው የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ላይ ያለው የልዩ ጥቅም መብት ግን ሊረጋገጥ ይገባል፤ የሚለውን ሀሳብ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው ሊደግፈው የሚገባ ነው።

• ኢህአዲግ የቀድሞ ጥምረቱ አለ፤ ብዙዎች የተለያየን የሚመስላቸው የልዩነት ሀሳቦች ሲኖሩ አራቱ ፓርቲዎች በውስጣዊ ውይይት ብቻ ይገድቡት የነበረው ሂደት ቀርቶ ፓርቲዎቹ የልዩነት አቋማቸውን በአደባባይ መግለፃቸው ነው ጥምረቱ የሌለ የሚያስመስለው።

• ይህ አካሄድ ወደፊትም ይቀጥላል ሆኖም ተግባራዊ የሚሆነው በጋራ የወሰነው ሀሳብ ነው

• ይበልጥ ወደ አንድ ለመወሃድ የጀመርነው ሂደትም ይቀጥላል።

• የፌደራል መንግስት ተዳክሟል ለማለት መለኪያው መሆን ያለበት ሀገር ስትወረር መመከት ሲያቅተው ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በብቃት መመከት አልችል ሲል ነው።

አሁን ግን በዚህ መልኩ የሚገለፅ አንዳችም ተግዳሮት አልገጠመንም በክልሎች የሚፈጠሩ ችግሮች ላይ ጣልቃ የማንገባው ክልሎች በራሳቸው መፍታት አለባቸው ብለን ስለምናምን ነው፤ ይህ ደግሞ ተገቢ ነው።

• ከኤርትራ ጋር ያደረግነው ስምምነት መሰረት ያደረገው ሰላምን ነው፤ በቀጣይ ኢኮኖሚ: ንግድ እና መሰል በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለመስማማት በሂደት ላይ ነን፤ ስለዚህ ከህዝብ የተደበቀ ሌላ ስምምነት የለንም፡፡

• ዲያስፖራው አሁንም ሀገሩን ለመደገፍ የጀመረውን መንገድ ሊገፋበት ይገባል፤ ይሁን እንጂ በማህበራዊ ሚዲያ በሚወጡ መረጃዎች ተስፋ የመቁረጥ ነገር ይታያል ይህ ተገቢ አይደለም ሁሉም ነገር ቀድሞ በተግባባንበት መልኩ እየተተገበረ ነው፤ ስለሆን ወደ ኋላ ማለት አይገባም

• በኮዬ ፌጬ የኮንደሚኒዮም ግንባታ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል ወሰን ያለው ውዝግብ ተፈቶ ለኮንዶሚኒዮም ባለእድለኞች ቤቶቹ እንዲተላለፉ እየተሰራ ነው

• በኦዲፒና በአዴፓ እንዲሁም በኦዲፒ በራሱ ውስጥ አንድነት እንጂ ምንም አይነት የተለየ ልዮነቶች የለም ነግር ግን በመካከላቸው የልዮነት ሀሳብ ይኖራሉ እነሱንም በመነጋገር እየፈታን ነው

• ከለውጡ በሃላ ኢኮኖሚው በሚፈለገው ደረጃ ውጤቶች ያልታየው ኢኮኖሚው ችግር ውስጥ ሆኖ ስለተቀበልነው እሱን የማስተካከል ስራ እየተሰራ ቆይተናል፡፡ በዚህም በርካታ ሀገራት ድጋፍ ስላደረጉ ውጤት ማግኘት ተችሏል፡፡

• አሁን ላይ ኢኮኖሚው ከታመመበት ሁኔታ ላይ ወጥቶ ጤናማ ሆኗል፡፡

• የአማራና የትግራይ ክልል ውጥረት በቀጣይ በእርግጠኝነት የሚረግብና ወደ ሰላም የሚመለስ ነው፡፡ ሁሉቱም ወገን በኦሮሚያና በሶማሊያ ክልሎች መካከል የተፈጠረው ግጭት ያመጣውን ኪሳራ ስለሚያውቁ መካከላቸው ያለው ልዮነት በሰላም ይፈታሉ፡፡

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
etv Live🔝

#ከመጋቢት_እስከ_መጋቢት በሚል ርዕስ የጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ ሀላፊነታቸውን የተረከቡበት #1ኛ_ዓመት በሚሊኒየም አዳራሽ እየተከበረ ይገኛል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ሀላፊነታቸውን የተረከቡበት 1ኛ ዓመት አስመልክቶ በሚሊኒየም አዳራሽ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፦

• በዚህ አመት በሄድኩበት ስፍራ የደገፋችሁን ወገኖች የሞታችሁልኝ የቆሰላችሁልኝ ወገኖች ልባዊ ምስጋናዬን ላቀርብ እፈልጋለሁ

• እናንተ ያለ እኔ መኖር ትችላላችሁ እኔ ግን ያለ እናተ የማልረባ ነኝ

• ለውጡ እንደ ደራሽ ውሃ ሳይሆን በብዙ ዋጋ የመጣ በመሆኑ ለውጡን ማስቀጠል ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚተው አደራ ነው

• አምና በዚህ ጊዜ የአገሪቱ ቀጣይነት በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ከጨለማ ጊዜ መውጣት መቻሉን መዘንጋት ተገቢ አይሆንም

• ለህዝባችን ያለፈውን ድል ብቻ በመናገር ሳይሆን ተደጋጋሚ ድሎችን ማስመዝገብ ይኖርብናል

• ባልተለወጠ ባህል እና ባልታደሰ ተቋም ለውጥ መጀመር ከባድ ነው

• ላለፉት 100 አመታት ኢትዮጵያ በአንድ አመት አምጥታ የማታውቀውን ባለፉት 7 ወራት ብቻ 13 ቢሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ማምጣት ተችሏል

• 8 ቢሊዮን ዶላር ባለፉት 7 ወራት ለግሉ ሴክተር ተሰጥቷል

• 8 አመቱን ያከበረውን የህዳሴ ግድብ እንዲቀጥል ቁርጠኛ አመራር ተሰጥቷል

• በኢትዮጵያውያን መካካል አንገት የሚቀላውን ሳይሆን የሰላም ሰይፍ በመምዘዝ ሰላምን ማስከበር ያስፈልጋል

•ለውጡ በድል ብቻ የታጀበ አይደለም፣ ኢትዮጵያውያን ሊሰሙት የማይፈልጉት መፈናቀል ተከስቷል

•ድሉን በጋራ እንዳመጣነው ሁሉ ችግሩንም በጋራ እንፈተዋለን

•አቅፎ ማለፍ ሳይሆን ጥሎ ማለፍ ላይ የተመሰረተው የሀገራችን ፖለቲካ ለለውጡ እንቅፋት እየሆነ ነው

•እኛ ሀላፊነት መውሰድ ባለመቻላችን የሚያድጉ ልጆች ተጧሪ እንዳይሆኑ ሁለም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል

•የምንሰራውና የምንነጋገረው ኢትዮጵያን ትልቅ ለማድረግ መሆን አለበት፡፡ ጉልበታች ለኢትዮጵያ ልማት አንጂ ህዝብ ለማፈናቀል መዋል የለበትም

•መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገነዘብ የሚፈልገው አማራ፣ ኦሮሞ፣ ትግራይ፣ ጋምቤላ ብሎ ኢትዮጵያ ከሌለ ሙሉ መሆን አንችልም

•ሁላችንም ማወቅ ያለብን ኢትዮጵያ ለማኝ አገር ናት፤ ድንቅ ሳይንቲስት፣ አርቲስት፣ ባለሃብት ብንፈጥር የለማኝ አገር ሳይንቲስት፣ አርቲስት፣ ባለሃብት መባሉ አይቀርም

Via etv
@tsegabwolde @tijvahethiopia
የጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ ሀላፊነታቸውን የተረከቡበት 1ኛ ዓመት አስመልክቶ በሚሊኒየም አዳራሽ ባደረጉት ንግግር በቀጣይ አመት ሊሰሩ የሚገቡ ስራዎችን አመላክተዋል፦

• መላው ኢትዮጵያውያን ይቅር በመባባል በጋራ ወደ ፊት እንዲጓዙ ማድረግ

• የተጀመረው ተቋማዊ ለውጥ ያልተሟላ በመሆኑ ተቋማት የመገንባት ስራ አጠናክሮ መቀጠል

• በቱሪዝም ዘርፍ በርካታ ሰራዎች ይሰራሉ

• በግብርና ዘርፍ በተለይም በትናንሽና መካከለኛ መስኖ ስራዎች ውጤተማ ስራዎችን ማከናወን

• የማዕድን ዘርፍ በማስፋፋት ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር

• የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ፍጻሜውን ለመቋደስ ወሳኝ በመሆኑ ህግ የሚያስከብሩ እና የሚተገብሩ አካላት በጠንካራ መሰረት የሚገነቡበት ጊዜ ይሆናል

• የተፈናቀሉ ዜጎች እንዲቋቋሙ ይሰራል

• በቀጣይ አመት የሚደረገው ምርጫ ለአፍሪካ አርአያ በሆነ መልኩ የሚደረግ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ይህን አንዲጠበቁ እፈልጋለው

• የጎደለ ነገር ካለ ኢትዮጵያውያን ዝቅ ብዬ ይቅርታ መጠየቅ ፈልጋለሁ

• የጎደሉ ነገሮች ባለማወቅ እና ሁኔታዎች በለመመቻቸታቸው እንጂ ዳተኛ በመሆን የተከሰቱ አይደሉም ብለዋል

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia