TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በሐሰተኛ ደረሰኝ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ግብይት ፈጽመዋል የተባሉ 124 ድርጅቶች #እየተመረመሩ ነው። በሕገወጥ ድርጊታቸው ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ ግብር መሰብሰብ አልተቻለም ተብሏል።

Source: JAD Business Group
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀሰተኛ መረጃ ተጠንቀቁ‼️

ትላንትና በአዲስ አበባ ከተማ በተካሄደው የኢትዮ-ኤርትራ ሩጫ ላይ ቦንብ ፈነዳ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጭ የነበረው መረጃ ሀሰተኛ እንደሆነ ልታውቁት ይገባል። ሩጫው በሰላም ተጀምሮ በሰላም ነው የተጠናቀቀው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አማራ ክልል⬇️

በአማራ ክልል የሚገኙ ከተሞች የመብራት ኃይል #እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አስታወቀ።

የፌዴራል መንግስትም በክልሉ ያለው ኢ-ፍትሃዊ የመብራት አቅርቦች ችግር እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ፈንታ ደጀን ለኢዜአ እንዳስታወቁት፤ በክልሉ የሚገኙ ከተሞች በመብራት ኃይል አቅርቦትና እጥረት ምክንያት የሚፈለገውን ተግባር ማከናወን አልቻሉም።

ባለፉት ዓመታት በክልሉ የሚገኙ ከተሞች ከሌሎች ክልሎች አንጻር ፍትሃዊ የኃይል ስርጭት እያገኙ እንዳልሆነ ገልጸዋል።

ክልሉ በከተሞች ያለው የመብራት አቅርቦት እንዲስተካከል በተደጋጋሚ ጠይቋል ያሉት አቶ ፈንታ፤ የፌዴራል መንግስት ችግሩን እንዲፈታ ጠይቀዋል።

የቢሮው ሃላፊ አሁን እየታየ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭትና አቅርቦት ችግር ሊፈታ እንደሚችል ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ ኃይል ስርጭት ችግር በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ የማሰራጫ መስመሮችን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በቅርቡ ለኢዜአ መግለጹ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የምትመለከቱት የMETC(ሜቴክ) ንግድ ፈቃድ ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቦንጋ...

"ሀይ ፀግሽ ዛሬ መንገድ ተከፍቶ በከፊል እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ሆኖም ግን ዘላቂ መፍትሔ ይፈልጋል። Esa ነኝ ከቦንጋ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ‼️

አዲስ አበባ #ጎዳና ቤቴ የሚሉ ዜጎች #እየበዙባት ነው ተባለ፡፡ ውሎ እና አዳራቸውን ጎዳና ያደረጉ ዜጎች መብዛት ከራሳቸው አልፎ በከተማዋ ጭምር የተለያዩ ማህበራዊ እና ምጣኔ ሐብታዊ ቀውሶች እንዲከሰቱ ምክንያት ሆነዋል ነው የተባለው፡፡

በመሆኑም ይህን ሀገራዊ ችግር ለመቀነስ የሚመለከታቸው አካላት እጅ ለእጅ ተያይዘው መረባረብ እንደሚኖርባቸው ተጠቁሟል፡፡

መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ የልማት ድርጅቶች ጎዳና የወጡ የማህበረሰቡ አባላትን ለማንሳት ማህበራዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ
ጥሪ ቀርቦላቸዋል፡፡

የአዲስ አበባ ማህበራዊ ጥበቃ ፈንድ እና ልማታዊ ሴፍትኔት ኤጀንሲ ሲናገሩ እንደሰማነው ከሆነ በ2011 ዓ.ም መግቢያ ላይ ባደረገው የሃብት ማሰባሰብ መርሃ ግብር የ34 ሚሊዮን ብር እርዳታ ከባለሃብቶች ቃል ተገብቶለት ነበር፡፡

ነገር ግን እስካሁን መሰብሰብ የተቻለው 6 ሚሊዮን ብር መሆኑን ኤጀንሲው ተናግሯል፡፡

ሌሎቹ ቃል የገቡትን እንዲሰጡ ቢጠየቁም የተለያዩ ምክንያቶችን በመጥቀስ አልከፈሉም ተብሏል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት ጎዳና ላይ የወጡ ዜጎች እንዲነሱ ቢደረግም አሁንም ድረስ ቁጥሩ እየጨመረ እንጂ ሲቀንስ አይታይም ብሏል ኤጀንሲው፡፡

ሰዎቹን ከጎዳና ላይ ለማንሳት በቂ ጥናትና ዝግጅት አለማድረግ ወደ ጎዳና እንዲመለሱ ምክንያት ሆኖ መቆየቱን ሰምተናል፡፡

በየጎዳናዎቹ ጥጋጥግ ኑሮአቸውን ያደረጉ አብዛኛዎቹ ዜጎች ማለትም ከ90 በመቶ በላዮቹ ከመላው አገሪቱ ገጠሮች ስራ አጥነትና ድህነት የገፋቸው መሆናቸው ሲነገር ሰምተናል፡፡

ኤጀንሲው በየጎዳናው የወደቁ ዜጎችን ማቋቋም በሚቻልባቸው አማራጮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ለሁለት ቀናት ውይይት አድርጓል፡፡

ኤጀንሲው በዚህ ዓመት ከ5 ሺ በላይ ሰዎችን ከጎዳና ለማንሳት ማቀዱን በውይይቱ ወቅት ተናግሯል፡፡

እነዚህን ዜጎች የተለያዩ ስልጠናዎችና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ በማድረግ ለ1 ዓመት ካቆየሁ በኋላ በድርጅቶች እንዲቀጠሩና የራሳቸውን ስራ እንዲጀምሩ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

ለዚህም የባለሃብቶች እና የረጂ ድርጅቶችን እገዛ ጠይቋል፡፡ የአዲስ አበባ ጎዳና ነዋሪዎችን ቁጥር በዘላቂነት ለመቀነስ ከክልሎች ጋር ሆኖ በጋራ መስራት እንደሚገባም ሃሳብ ቀርቧል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በኦዞን ንጣፍ የተከሰተውን ጉዳት በ50 ዓመታት ሙሉ በሙሉ ማገገም እንደሚችል ሳይንቲስቶች #አረጋገጡ። በኦዞን የአየር ንጣፍ ላይ ተከስቶ የነበረዉን ጉዳት በ50 ዓመታት ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንዲያገግም ማድረግ እንደሚቻል የመንግስታቱ ድርጅት ሪፖርት አመልክቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን‼️

ህዳር 29 ቀን 2011 ዓ.ም የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ላይ ብሔሮች ከራሳቸው በተጨማሪ የአንድ ሌላ ብሔር ባህላዊ አለባበስና ጭፈራ ትርዒት እንደሚያሳዩ ተጠቆመ፡፡

የ13ኛው የኢትዮጵየ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል ዝግጅት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፣ የክልሎች ምክር ቤቶች አፈ-ጉባዔዎች የበዓሉ አስተባባሪ ጽህፈት ቤትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ትላንት በአዲስ አበባ ተገምግሟል።

የበዓል ዝግጅት አስተባባሪ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ኑረዲን ማህሙድ እንዳሉት፤ በዓሉ አገራዊ አንድነት፣ ሰላምና መቀራረብ ሊያመጡ የሚችሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እየተከናወኑ ነው።

ከነዚህም መካከል የራስ ብቻ ሳይሆን አንዱ ብሔር የሌላውንም ባህል ጨምሮ እንዲያሳይ ለማድረግ ሁሉም የቤት ስራ ወስዶ ዝግጅት እንዲጀምር መደረጉ እንደሆነ ጠቁመዋል።

በዚህም መሰረት ትግራይ ክልል ከራሱ በተጨማሪ የኦሮሞ ህዝብን ባህል የሚያሳይ ትዕይንት ለማሳየት፣ ኦሮሚያ ክልል ደግሞ ከደቡብ ብሔሮች መካከል የተወሰኑትን መርጦ፣ ደቡብ ደግሞ የአማራን አማራ ደግሞ የሱማሌን ለማሳየት ፍቃደኛ መሆናቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።

ሁሉም ክልል ከራሱ በተጨማሪ የሌላውን ክልል አንድ ወይም ከዚያ በላይ ብሄር ባህላዊ አለባበስ ጭፈራና ትዕይንቶችን ለማሳይት ዝግጅት እያደረገ ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ከዚህም ሌላ በዓሉ ሲከበር አገራዊ አንድነት የሚያጠናክሩ ምክክሮች በማድረግ እንዲሆንና ሲምፖዚዬሞች እንዲዘጋጁ በመወሰኑ ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ጽሁፎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

በአገሪቱ የተለያዩ አከባቢዎች በተለይ ደግሞ ግጭቶች ተከስተው በነበሩባቸው አካባቢዎች ላይ ሁሉም የሚሳተፍበት ህዝባዊ መድረክ በማዘጋጀት ውይይትና እርቅ እየተደረገ እንደሆነ አመላክተዋል።

ምንጭ፦ ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢራቅ‼️

በኢራቅ የካቢኔ አባላት #በፌስቡክ ማስታወቂያ ተመረጡ፡፡ የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር #አደል_አብዱል_ማህዲ በበይነ መረብ ከተወዳደሩ 15 ሺ ሰዎች መካከል የካቢኔያቸው አባል የሚሆኑ 5 ሰዎችን መርጠዋል። ይህ በከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊነት ውስጥ ያልተለመደ የቅጥር መንገድ መጀመሪያ በጠቅላይ ሚኒስትር ማህዲ የፌስቡክ ገጽ ላይ የተዋወቀ ሲሆን ከሚያስፈልጉት 14 የካቢኔ አባላት መካከል 5ቱ በዚህ መንገድ ተመርጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢቦላ ወረርሽኝ‼️

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በቅርቡ ያገረሸው ኢቦላ ወረርሽኝ በአገሪቷ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅና #አሰከፊ ነው ሲል የአገሪቷ ጤና ጥበቃ ሚንስትር አስታውቀዋል።

ከባለፉት አራት ወራት ጀምሮ ቢያንስ 200 ሰዎች በወረርሽኙ ሕይወታቸው ሲያልፍ ወደ 300 የሚሆኑ የተጠረጠሩ ህመምተኞች ተገኝተዋል።

ወረርሽኙን ለመግታት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረገ ሲሆን እስካሁን 25 ሺህ ለሚሆኑ ሰዎች #ክትባት ተሰጥቷል።

ይሁን እንጂ የአገሪቱ ፖለቲካዊ #አለመረጋጋትና የጤና ባለሙያዎች ላይ በተለያየ ጊዜ ጥቃት በመድረሱ ለዓመታት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት ተፈታትኖታል።

የጤና ጥበቃው ሚንስትር ኦሊ ኢሉንጋ በዚህ ሰዓት 319 በበሽታው የተያዙና 198 ሞት መመዝገቡን ገልፀዋል።

"ቤተሰቦቻቸውን ላጡ፣ ያለ አሳዳጊ ለቀሩ ሕፃናትና ለተበተኑ የቤተሰብ አባላት የተሰማኝን ሀዘን እገልፃለሁ ፤ መፅናናትን እመኛለሁ፤ በፀሎትም አስባቸዋለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

ባለስልጣኑ እንደተናገሩት ግማሽ ያህሉ ተጎጂዎች 800 ሺህ ህዝብ ከሚኖርባት የሰሜናዊ ኪቩ ግዛት ቤኒ ነዋሪዎች ናቸው።

አገሪቱ በአውሮፓውያኑ 1976 ካጋጠማት ስሙ በውል ካልታወቀው ወረርሽኝ በኋላ የአሁኑ በጣም አሰቃቂውና አስፈሪው ነው።

ኢቦላ ከሰውነት ከሚወጣ ፈሻሽ እና ሌሎች ኢንፌክሽኖች አማካኝነት ይተላለፋል፤ ምልክቱም ጉንፋን መሳይ ህመም፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ፣ ውስጣዊና ውጫዊ መድማት ናቸው።

ምንጭ፦ OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫው በቅርቡ በሰብአዊ መብት ጥሰትና #በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ እና በቁጥጥር ሥር እየዋሉ በሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች እና
በሌሎች ወቅታዊ የፍትሕ ሥርዓት ጉዳዮች ላይ የሚሰጥ ነው ተብሏል። መግለጫው ዛሬ ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ እንደሚሰጥ ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሜቴክ‼️

ሜቴክ ላይ ሲደረግ የነበረው ምርመራ እየተገባደደ ነው። በብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ውስጥ ተፈፅሟል የተባለውን ከፍተኛ ሙስና ማጣራት ከጀመረ ወራት ተቆጥረዋል። በማጣራቱ ሂደት በርካታ መረጃዎች ተሰብስበዋል። ይሁንና ከመስሪያ ቤቱ የተሰወሩ፣ ያልተሟሉና የተጭበረበሩ መረጃዎችን የማጣራቱ ስራ አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል።

ዋዜማ ከምርመራው ጋር ቅርበት ካላቸው ምንጮች እንደሰማቸው የሙስና ስንሰለቱ ከፖለቲካ አመራሩ ከግል ባለሀብቶችና በውጪ ሀገር ካሉ ኩባንያዎች ጋር የተያያዘና እጅግ ፈታኝ ነበር።

ባለፉት ወራት ከሜቴክ መካከለኛ አመራሮች ከባለሙያዎችና ጉዳዩን ከሚያውቁ ጋር የመርማሪ ቡድኑ አባላት እየተገናኙ መረጃ ሲያሰባስቡ ነበር። ይሁንና መቀሌ የመሸጉት የሜቴክ አመራሮች የደህንነት መስሪያቤት አባላትና እስካሁንም በሜቴክ ውስጥ እየሰሩ ያሉ ሀላፊዎች በመመሳጠርና መረጃ በማዛበት ምርመራው እንዳይሳካ ለማድረግ ሞክረዋል። መረጃ በማሸሽም ምርመራውን ለማስተጓጎል ሞክረዋል።

እንደመረጃ ምንጮቻችን ለምርመራው እጅግ ጠቃሚ መረጃ በመስጠት ትብብር ያደረጉም አሉ። በምርመራው ሂደት የተባበሩት ላይ የግድያ ዛቻና ማስፈራራት የደረሰባቸውም እንደነበሩ ተሰምቷል።

አሁን ከሀገር ውጪ የሚገኙና ለምርመራው እጅግ ጠቃሚ መረጃ ያቀበሉ ግለሰብ እንደሚሉት የሜቴክ ጥፋቶች በሁለት ይከፈላሉ።

አንዱ የማያውቁትንና የማይችሉትን ስራ ለመስራት በመሞከር ሳይሳካ ሲቀር ደግሞ ከማረምና ከማቆም ይልቅ እንደገና አዲስስ ህተት በመደመር የተፈፀመ ወንጀል ነው። ሁለተኛው ጥፋት ሆነ ተብሎ በተደራጀና በተቀነባበረ መንገድ የህዝብ ሀብትን በዘመድ አዝማድ እየዘረፉ የማሸሽ ወንጀል ተሰርቷል ይላሉ።

ሜቴክ ውስጥ ውድ ህይወታቸውን መስዋዕት አድርገው ለሀገራቸው የለፉና ሽልማት የሚገባቸው ሰዎች አሉ።

አንዳንዶች ሙስና ሲፈፀም “ለምን?”  ብለው ስለጠየቁ ከስራ የተባረሩና የደረሱበት ያልታወቀም አሉ።

ከሕወሀት አመራሮች መካከል ሜቴክ የህዳሴው ግድብ እንዳይሰጠው በሌሎች ስራዎቹም ቁጥጥር እንዲደረግበት የጠየቁ እንደ ከሀዲ ተቆጥረው ተዋክበዋል። በተለይ ከመለስ ዜናዊ ሞት በኋላ ሜቴክ በሀገሪቱ ውስጥ ያሻውን ማድረግ የሚችል ተቋም በመሆኑ ሀገሪቱ ልትሸከመው ከምትችለው በላይ ዕዳ ውስጥ ከቷታል።

የሜቴክ ችግሮች የቀረበላቸው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኋይለማርያም ደሳለኝ ጉዳዩ አንስተው ለመጠቅ እንኳን አልደፈሩም የሚሉት ምንጫችን ያቀረብንላቸውን መረጃ ሂዱና ለፍትህ ሚኒስቴር አቅርቡ፣ ሜቴክ የመከላከያ ተቋም ስለሆነ ገመናችንን አደባባይ ማውጣት ተገቢ አይደለም የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል ብለዋል።

እስከ መስከረም ወር መጨረሻ በሜቴክ ውስጥ በሀላፊነት ሲሰሩ እንደነበረና አሁን ከምርመራው ጋር በተያያዘ ወደ ውጪ ሀገር መውጣቻውን የነገሩን ምንጫችን ከቀናት በፊት የተጀመረው አንዳንድ የሜቴክ አመራሮችንና ስራተኞችን የማሰር ሂደት የተሟላ መረጃ ለመሰብሰብና ምርመራውን የተሟላ ለማድረግ አስፈላጊ እርምጃ ነው።

የታሰሩት ሁሉ ወንጀለኛ ናቸው ማለት ላይሆን ይችላል፣ ይሁንና መረጃ የማሸሽ ሁኔታ ስላለ ይህን ለመግታት ታስቦ ይመስለኛል ብለዋል።

መቀሌ የተደበቁት የሜቴክ አመራሮችን ህግ ፊት ማቅረብ አይቀሬ ነው ያሉት ግለሰቡ በጉዳዩ ላይ ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር ውይይት መደረጉን እንደሚያውቁ ነግረውናል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አህመድ እርምጃ ከመወሰዱ በፊት መረጃ እንዲሰባሰብ ባዘዙት መሰረት ለወራት መረጃዎቹ ሲዘጋጁ ነበር። በቅርቡ የተጠናቀረው መረጃ ሲደርሳቸውና በጉዳይ ላይ ገለፃ ሲደረግላቸው “አሁን ይህን ጉድ ለህዝቡ ምን ብለን ልንነግረው ነው?”  ሲሉ መደመጣቸውን ያስታውሳሉ።

ምንጭ:- ዋዜማ ራዲዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንጻ ግንባታ የመጨረሻ ወለል ኮንክሪት ሙሌት ስራ ተከናውኗል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ለማ መገርሳ!

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ለሚስተዋሉ የፀጥታ ችግሮች ሁነኛ መፍትሄ ፍለጋ በጥሞናና በሰከነ መንፈስ #መወያየትን እንደሚጠይቅ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ ተናገሩ፡፡

የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የሠላም ኮንፈረንስ በሻሸመኔ ከተማ ተካሂዷል፤ ተሳታፊዎቹ ከምስራቅ እና ምዕራብ አርሲ ፤ ባሌ ፤ ቦረና ፤ ምስራቅ እና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች የተውጣጡ ናቸው። በውይይቱ ላይ የኦሮሞን ህዝብ የትግል ታሪክ እና አሁን ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ፅሁፍ ቀርቧል።

ፅሁፉን ያቀረቡት የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ / ኦዴፓ / የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘረፍ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ ናቸው፤ አቶ አዲሱ ባቀረቡት ፅሁፍ በቄለም ወለጋ ፤ ምዕራብ ወለጋ ፤ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ጉጂ ዞኖች የፀጥታ ችግሮች እየታዩ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የእነዚህን ችግሮች ጉዳት አስቀድሞ በመረዳት ከወዲሁ መፍትሄ መስጠት ይገባልም ብለዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሣ በበኩላቸው በደቡብ እና ምዕራብ ኦሮሚያ የታጣቁ ሃይሎች ችግር እየፈጠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ከእነዚህ የታጠቁ ሃይሎች ጋር ውይይት ቢደረግም በሰከነ መንፈስ መደማመጥ አለመቻሉን አክለዋል። የሚሻለው ግን በሰከነ መንፈስ መነጋገር እንደሆነ ርዕሰ መስተዳድሩ ግልጽ አድርገዋል።

የሚታዩ የፀጥታ ችግሮች የልማት ስራዎችን ለማከናወን እንቅፋት እንደሆኑም አቶ ለማ ተናግረዋል።

ህዝቡም ይህንኑ በመረዳት በተሳሳተ መንገድ ላይ ያሉ ወገኖችን ወደ ትክክለኛው መስመር ሊመልሳቸው ይገባል ብለዋል።

ከውጪ የገቡ ሃይሎች በሠላማዊ መንገድ እንዲታገሉ ግፊት ሊያደርግ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፋና TV‼️የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ እየሰጠ ያለውን መግለጫ ፋና ቲቪ በቀጥታ እያስተላለፈ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንትነቱ በፍቃዱ #ለቀቀ

አትሌት ሃይሌ መልቀቂያ ደብዳቤውን ለጠቅላላ ጉባኤ አባላት ማዘጋጀቱን ዛሬ ቦሌ በሚገኘው የራሱ ቢሮ ለስፖርት ጋዜጠኞ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

በደብዳቤው እንዳመለከተውም እስከ ቀጣዩ የምርጫ ወቅት ድረስ ኮሎኔል አትሌት #ደራርቱ_ቱሉ የፕሬዚዳንትነቱን ቦታ ተክታ እንድትሰራ መወከሉንም ገልጿል።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዴፓ እና አዴኃን ተዋሀዱ‼️

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ(አዴኃን) #ውህደት መፍጠራቸውን በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

አዴፓ በመግለጫው እንዳስታወቀው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ(አዴኃን) ወደ በረሀ ወርዶ የታገለላቸው ሀሳቦች አዴፓም አቋም ይዞ የሚታገለው ሀሳብ ነው፤ ስለሆነም ሁለቱ ድርጅቶች መዋሃዳቸው ለአንድ ዓላማ መቆማቸውን ያሳያል፡፡

ከዛሬ ጀምሮም የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ(አዴኃን) ውህደት ፈጥረናል ብለዋል፡፡

አዴኃን በቅርቡ የተፈጠረውን ለውጥ ተከትሎ በሰላም ለመታገል ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ የገባ ድርጅት ነው፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

"የሰኔ 16ቱ የአዲስ አበባው የቦምብ ጥቃት የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት የቀድሞ #ሀላፊ የተመራ ነው"

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል።

በመግለጫው እስካሁን በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል 36 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው እና ሰባት ድብቅ እስር ቤቶች በአዲስ አበባ ተገኝተዋል።

በሽብር ወንጀል የተጠረጠሩ የተጠረጠሩበት ወንጀል ዜጎችን በድብቅ ማሰር፣ መደብደብ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ብልት ላይ ውሃ ማንጠልጠል
የመሰሉ ወንጀሎች ይገኙበታል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia