TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዶ/ር አብይ ሀዘናቸውን ገልፁ‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አህመድ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ውስጥ በሰላማዊ ዜጎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት መንግሥት የተሰማውን ሀዘን ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቃቱ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመ #ዘግናኝ ድርጊት ሲሉ ኮንነውታል። ለተጎጂ ቤተሰቦችና በሀዘን ላይ ለሚገኙት መላው ኬንያውያን የተሰማቸውን ልባዊ ሀዘን ገልጸዋል። ትናንት ናይሮቢ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት 14 ሰዎች መገደላቸውን የኬንያው ፕሬዚዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ ዛሬ መግለጻቸው ይታወሳል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚር #ዐቢይ_አሕመድ ከ32ኛው አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ከመካፈል ጎን ለጎን የሚያካሂዷቸውን የተለያዩ ስብሰባዎች ቀጥለዋል። ከፍልስጤም ፕሬዝዳንት #ማህሙድ_አባስ፣ ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት #ሲሪል_ራማፎሳና ከኬንያው ፕሬዝዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን አካሂደዋል።

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መሪዎቹ ሀዋሳ ገብተዋል...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #አብይ_አህመድና የኬንያው ፕሬዚዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጉብኝት እያደረጉ ነው። የሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፍጹም ከተማ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ÷ ጉብኝቱ የሚካሄደው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ለማጠናከር በማሰብ ነው ብለዋል።

Via ena
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መሪዎቹ አርባምንጭ ገብተዋል...

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠ/ሚ ዶ/ር #ዐብይ_አህመድ እና የኬንያው ፕሬዘዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ አርባምንጭ ከተማ ገብተዋል። መሪዎቹ አርባምንጭ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ፎቶ፦ Gamo Zone Administration Public Realtion office
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ትላንት ማምሻውን ለፕሬዝዳንት #ኡሁሩ_ኬንያታ በተዘጋጀ የእራት ግብዣ ላይ ፕሬዚዳንቱ በንግግራችው አዲስ አበባ #የኬንያኖችም የሁሉም ከተማ መሆንውን ገልጸዋል። በተያያዥነትም የሸገርን ማስዋብ ፕሮጀክት #እንደሚደግፉ ገልጸው የኬንያ ባለሀብቶች በገበታ ለሸገር ከጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና #ኢትዮጵያዊያን ጎን እንደሚቆሙ #ቃል_ገብተዋል

#PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikbahethiopia