TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ በተደራጀ ሁኔታ ገንዘብ የማሰባሰብ ተግባሩን ጀመሯል። ይህንን አስመልክቶ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት የወጣውን መግለጫ ከላይ አንብቡት።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮ-ቴሌኮም በአዲስ አበባ ስራ አጥነትን ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የራሱን #አስተዋፃኦ ለማበርከት ተዘጋጅቻለሁ አለ። የድርጅቱ ሀላፊ ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ እንደገለፁት በቴክኖሎጂ ለስራ ፈጠራ ዕገዛ በማድረግም ሆነ በሌሎች የስራ ዘርፎች ስራ ፈላጊዎች እንዲሳተፉ ለማድረግ በሩ ክፍት ነው።

ምንጭ፦ ዋዜማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የብሄር ብሄረሰቦች ቀን⬇️

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች በዓል #የተራራቁና #የተኳረፉ ሕዝቦችን በማስታረቅና በማቀራረብ #ይከበራል ተባለ፡፡

የበዓሉን አከባበር አስመልክቶ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዓሉ እስካሁን ሲከበርበት የቆየው መንገድ የተለያዩ #ክፍተቶች እንዳሉበት በጥናት #ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

በሕዝቦች መካከል የቆየውን አብሮ የመኖር፣ የመቻቻልና የመከባበር እሴቶች ከማስጠበቅ አንፃር ክፍተቶች ነበሩ ብለዋል፡፡

አሁን ኢትዮጵያ ላይ እየታየ ያለው ሁኔታም ለዚህ ማሳያ ነው ያሉት አፈ ጉባኤዋ የብሔር ማንነትንና ኢትዮጵያዊነትን በማጣመር የዘንድሮውን በዓል ለማክበር ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ሰው በብሔሩ ብቻ የሚፈናቀልበት፣ የሚጠቃበትና የሚገደልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ያሉት አፈ ጉባኤዋ በኢትዮጵያ ሕዝቦች መካከል መጠራጠርና አለመተማመን ተፈጥሯል፣ በህብረተሰቡ ውስጥም በርካታ ቁስል አለ ብለዋል፡፡

የዘንድሮ በዓል የተራራቁ የሚቀራረቡበትና ለመፃኢ የጋራ ተስፋቸው የሚተባበሩበት መንገድ የሚታሰብበት ሆኖ እንደሚከበር ተናግረዋል፡፡

በተለይም የጎላ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች በጥናት ላይ የተመሰረተ የሰላምና የማረጋጋት ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡

ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ሳይንሳዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን በመጠቀም ዘላቂነት ያለው ሰላም ለመፍጠር ከወዲሁ ስራዎችን ጀምረናል ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

ለ13ኛ ጊዜ የሚከበረው የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በአዲስ አበባ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

በበዓሉ ዝግጅት ወጣቶችና የኪነ ጥበብ ሰዎች እንደሚሳተፉ የተናገሩት ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ እለቱን የኢትዮጵያውያን ቀን አድርጎ ያከብራል ብለዋል፡፡

ለበዓሉ አከባበር የሚወጣው ወጪም ለወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ የሚውል ሲሆን ድግስ የማይበዛበት ዝግጅት ይደረጋል ብለዋል፡፡

የዘንድሮ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል በብዝሃነት የደመቀ ኢትዮጵያዊነት በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን⬆️የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ #ሙፈሪያት_ከሚል ዛሬ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንን ጎብኝተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ኢንጂነር ታከለ⬆️

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የአሜሪካውን አምባሳደር #ማይክ_ሬይነርን በፅ/ቤታቸዉ ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸው የከተማ አስተዳደሩ በጀመራቸው የለውጥ እና የልማት ስራዎች ላይ መክረዋል።

በዚህም በአካባቢ ጥበቃ፣ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ዙሪያ አሜሪካ የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ ፍላጎት እንዳላት አምባሳደሩ አብራርተዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነት ፓርቲ እና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ፓርቲ አብረው ለመስራትና ወደ #ውህደት የለመሸጋገር የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አምባሳደር #ሳህለወርቅ_ዘውዴ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው የአሜሪካ ኢምባሲ የደስታ መግለጫ አስተላለፈ፡፡ ያለ #ሴቶች ተሳትፎ አንድ ማህበረሰብ #ውጤታማ እንደማይሆን የተገነዘበው የኢትዮጵያ መንግስት ሴቶችን ወደ ሃላፊነት ማምጣቱ ሊያስመሰግነው ይገባል ብሏል የአሜሪካ ኢምባሲ በመግለጫው፡፡ መንግስት ሴቶችን ያቀፈ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ጠንካራ እርምጃ በመውሰዱ ኢምባሲው #አድናቆቱን ገልጿል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አርባ ምንጭ⬆️ለአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች በአርባ ምንጭ ከተማ አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ከከተማይቱ ወጣቶች የደረሰን መልዕክት ያስረዳል።

ፎቶ፦ ሙሌ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#update⬆️ልጆቻቸውን ወደ ትግራይ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚልኩ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ያሉ ወላጆች ሥጋት #እንዳያድርባቸው የክልሉ ርዕሰ - መስተዳድር ዶ/ር ድብረፅዮን ገብረሚካኤል አሳስበዋል፡፡

የትምህርቱን ዘመን #ሰላማዊ ለማድረግ እየተካሄደ ያለው ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የገለፁት የክልሉ ፕሬዚዳንት ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ቤተሰቦቻቸው እንደላኩ አድርገው እንዲያስቡ መክረዋል፡፡

ምንጭ፦ voa የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሐረር የውኃ አገልግሎት በአንድ ሣምንት ውስጥ #እንደምታገኝ የሐረሪ ክልል የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ አስኪያጅ አስታውቀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia