TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አስቸኳይ መረጃ‼️

በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የኢህአዴግ 11ኛ ድርጅታዊ ጉባዔ በሠላም መጠናቀቁን በማስመልከት በሲዳማ ብሔር ባህላዊ ጫዋታ ( #በቄጣላ) እንደሚበሰር ተገለፀ።

"ሀገራዊ አንድነት ለሁለንተናዊ ብልፅግና" በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 23-25/2011 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ በመካሄድ ላይ ያለው የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ በድል መጠናቀቁን ለማብሠር ነገ ቅዳሜ መስከረም 26/2011 ዓ.ም. በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትሪ ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ እና የግንባሩ ምክትል ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሪ አቶ #ደመቀ_መኮንን ጨምሮ የየሁሉም ክልሎች ርዕሳኔ መስተዳድሮች፣ የእህትና አጋር ድርጅቶች አመራሮች እንዲሁም የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ተሳታፊ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከጧቱ 1:00 ጀምሮ የቄጣላ ትዕይንት ከታዬ በኋላ ጉባዔው በይፋ ይዘጋል።

በመሆኑም በተባለው ሰዓት በቦታው ተገኝታችሁ ትዕይንቱን እንድትከታተሉ የሲዳማ ዞን አስተዳደር ጥሪውን ያቀርባል።

መስከረም25/2011 ዓ.ም
ሀዋሳ,ሲዳማ

ምንጭ፦ የሲዳማ ዞን ባህል፣ ቱሪዝም እና መንግስ ኮሚኒኬሽን
@tsegabwolde @tikvahethiopia