FBC (Fana Broadcasting Corporate)
198K subscribers
60.1K photos
736 videos
23 files
53.8K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
በህወሓት ወረራ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በአሸባሪው ህወሓት ወረራ ምክንያት የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ላልወሰዱ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው ፈተና በሰላም ተጠናቋል፡፡ የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ በድሉ ውብሸት፥ በአካባቢው በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ዘግይተው ፈተናውን የወሰዱ…

https://www.fanabc.com/በህወሓት-ወረራ-የ12ኛ-ክፍል-መልቀቂያ-ፈተና/
በ35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የሀገራት መሪዎች አዲስ አበባ መግባታቸውን ቀጥለዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በመሪዎቹ ስብሰባ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ፕሬዚዳንት ፋርማጆ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የግብርና ሚኒስትሩ ኡመር ሁሴን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። በርናባስ ተስፋዬ ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን…

https://www.fanabc.com/በ35ኛው-የአፍሪካ-ህብረት-የመሪዎች-ጉባኤ-ላ/
የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ምክር ቤቱ ዝርዝራቸውን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን የዕጩ ኮሚሽነሮች ላይ ህብረተሰቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸው ምክር ቤቱ ዝርዝራቸውን ይፋ አደረገ፡፡ ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://publielectoral.lat/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

https://www.fanabc.com/የኢትዮጵያ-አገራዊ-ምክክር-ኮሚሽን-የዕጩ-2/
አቶ ደመቀ መኮንን የአቶሚክ ኃይልን ለልማት ለመጠቀም ዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ትብብር እና ድጋፍ እንዲያደርግ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የዓለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የሆኑትን ራፋኤል ማሪያኖ በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ደመቀ መኮንን ፥ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያ የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባን በስኬት በማስተናገድ ላይ እንደምትገኝ ጠቅሰው ፥…

https://www.fanabc.com/አቶ-ደመቀ-መኮንን-የአቶሚክ-ኃይልን-ለልማ/
የአለም ባንክ ለጥራት መሰረተ ልማት ተቋማት የ14 ነጥብ 6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለም ባንክ አንድ አካል የሆነው ብሔራዊ የጥራት መሠረተ ልማት ፕሮጀክት ለቀጣይ 18 ወራት በጥራት ቁጥጥር ስራ ላይ ለተሰማሩ የጥራት መሠረተ ልማት ተቋማት የ14 ነጥብ 6 ሚሊየን አሜሪካን ዶላር በጀት አጽድቋል፡፡ ፕሮጀክቱ ላለፉት አምስት ዓመታት የጥራት መሠረተ ልማት አገልግሎቶችን ማሻሻል ዓላማ አድርጎ በመስራት በአገልግሎት ሰጪ እና ተቀባይ…

https://www.fanabc.com/የአለም-ባንክ-ለጥራት-መሰረተ-ልማት-ተቋማ/
አሜሪካ ለሶርያ አሸባሪ ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ጦር አዛዥ የነበሩት ቤን ሆጅስ ዩናይትድ ስቴትስ ዋይፒጅ /ፒኬኬ ለተባለው የሶርያ አሸባሪ ድርጅት የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ጠይቋል ፡፡ የቀድሞ የአሜሪካ ጦር አዛዥ ቤን ሆጅስ ፥ አሜሪካ በሶሪያ ለሚገኙ አሸባሪ ድርጅቶች የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ጠይቀዋል፡፡ የቀድሞው የጦር አዛዥ ከሁድሰን ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ባልደረባ ከሆኑት ሚካኤል ዶራን ጋር…

https://www.fanabc.com/አሜሪካ-ለሶርያ-አሸባሪ-ድርጅት-የምታርገ/
በሁለተኛ ዙር ሲሰጥ የነበረው የ2013 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፀጥታ ችግር ምክንያት የ2013 ዓ.ም አገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ላልወሰዱ ተማሪዎች ሲሰጥ የነበረው ፈተና በሰላም መጠናቀቁን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ። የህወሓት የሽብር ቡድን እና ተባባሪዎቹ በፈጠሩት የፀጥታ ችግር ምክንያት በ2013 ዓ/ም ፈተናውን መውሰድ ያልቻሉ ተማሪዎች በሁለተኛ ዙር ከጥር 24/2014 ጀምሮ ፈተናውን ሲወስዱ ቆይተዋል። ሀገር አቀፍ…

https://www.fanabc.com/በሁለተኛ-ዙር-ሲሰጥ-የነበረው-የ2013-ዓ-ም-አገር/
በሀረሪ ክልል በ6 ወራት 580 ሚሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27 ፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሃረሪ ክልል ባለፉት 6 ወራት 580 ሚሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡ የቢሮው ሃላፊ አቶ በቀለ ተመስገን የክልሉን የ6 ወራት የገቢ አፈፃፀምን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ፥ በ2014 ዓ.ም በ6 ወራት ውስጥ 593 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ለመሰብስብ ታቅዶ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ የተሰበሰበው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ…

https://www.fanabc.com/በሀረሪ-ክልል-በ6-ወራት-580-ሚሊየን-ብር-ገቢ-ተ/
በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን 2 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች፡፡   የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው 1 ለ 0 ቢሸነፍም ዛሬ በተደረገው ጨዋታ 2 ለ0 በማሸነፍ 2 ለ 1 በሆነ ድምር ዉጤት ወደ መጨረሻው…

https://www.fanabc.com/በሴቶች-ከ20-ዓመት-በታች-ዓለም-ዋንጫ-ማጣሪያ/
ቻይና እና ሩሲያ በጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ በመደጋገፍ እንደሚሰሩ በድጋሚ አረጋገጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ እና የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን ወሳኝ በሆኑ የጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ በመደጋገፍ እንደሚሰሩ አረጋገጡ፡፡ ከውይይታቸው በኋላ መሪዎቹ ባወጡት የጋራ መግለጫ፥ ሀገራቱ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ዘላቂ ልማት ላይ በጋራ ለመሥራት ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡ ሀገራቱ በውስጥ ጉዳዮቻቸው ላይ ጣልቃ የሚገባ ማንኛውንም የውጭ ኃይል በጥብቅ…

https://www.fanabc.com/ቻይና-እና-ሩሲያ-በጋራ-ጥቅሞቻቸው-ላይ-በመ/
የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሽታይ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሽታይ በ35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች አቀባበል እንዳደረጉላቸው ኢዜአ ዘግቧል። 35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ “የአፍሪካ አህጉርን የስርዓተ ምግብ…

https://www.fanabc.com/የፍልስጤም-ጠቅላይ-ሚኒስትር-ሞሃመድ-ሽታ/
ታዳጊ ልጆች የሳይበር ምህዳሩ ላይ ሊገጥማቸዉ የሚችሉ የጥቃት ተጋላጭነቶች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ታዳጊ ልጆች በአሁኑ ጊዜ ከሳይበርና ከቴክኖሎጂ ነክ መገልገያዎች ጋር ከፍተኛ ግንኙነት እና መስተጋብር እንዳለቻው እርግጥ ነዉ ። ታዲያ ይህ ቴክኖሎጂ ከሚሰጠዉ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ባሻገር በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲዉል ካልተደረገ በታዳጊ ልጆች ላይ በርካታ ጉዳቶችን ሊያስከትል ይችላል። በመሆኑም ወላጆች እና አሳዳጊዎች ታዳጊ ልጆች ከቴክኖሎጂ ጋር ከሚፈጥሩት መስተጋብር…

https://www.fanabc.com/ታዳጊ-ልጆች-የሳይበር-ምህዳሩ-ላይ-ሊገጥማ/
ኢትዮጵያ እያስተናገደች ያለቸው የህብረቱ ጉባኤ ጫናዎችን ተቋቁማ በዲፕሎማሲው መስክ ስኬታማ መሆኗን ያሳየ ነው – የውጭ ሃገራት የሚዲያ ባለሙያዎች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እያስተናገደች ያለችው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ጫናዎችን ተቋቁማ በዲፕሎማሲው መስክ ስኬታማ መሆኗን ያሳየ መሆኑን የውጭ ሃገራት የሚዲያ ባለሙያዎች ገለጹ፡፡ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ባለሙያዎቹ ጉባኤው የአዲስ አበባን ብሎም የኢትዮጽያን መረጋጋትና አንድነት ያሳየ እንደሆነ አብራርተዋል ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ህብረትን ለመዘገብ የመጣው እና የአፍሪካ…

https://www.fanabc.com/ኢትዮጵያ-እያስተናገደች-ያለቸው-የህብረ/
አቶ ደመቀ መኮንን ከአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአልጀሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ራማታን ጋር ተወያይተዋል።   በወቅቱም አቶ ደመቀ መኮንን የአልጀሪያ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት የቆየ መሆኑን በማንሳት፥ በቀጣይ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በኢትዮጵያ በኩል ፍላጎት መኖሩን…

https://www.fanabc.com/አቶ-ደመቀ-መኮንን-ከአልጀሪያ-የውጭ-ጉዳይ/
ኢትዮጵያ እና ጀርመን በውሃና ኢነርጂ አቅርቦት በጋራ የሚሰሯቸውን ስራዎች አጠናክረው ለመቀጠል ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጀርመን በውሃና ኢነርጂ አቅርቦት በጋራ የሚሰሯቸውን ስራዎች አጠናክረው ለመቀጠል ተስማሙ።   የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባደር እስቴፈን አወርን ጋር ተወያይተዋል።   በውይይታቸውም ጀርመን በኢነርጂ፣ በመጠጥ ውሃ ፣ በስነ ንፅህና እንዲሁም በአቅም ግንባታ ስራዎች እና በፋይናንስ የምታደርገው ድጋፍ ኢትዮጵያ ለያዘችው…

https://www.fanabc.com/ኢትዮጵያ-እና-ጀርመን-በውሃና-ኢነርጂ-አቅ/
አፍሪካ በፀጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል-አፍሪካ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የተለያዩ አፍሪካ አገራት የዓለም አቀፍ ግንኙነትና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ገለጹ።   ለ35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ አዲስ አበባ የተገኙ ታዳሚዎች እንደገለጹት፥አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራት የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል።…

https://www.fanabc.com/አፍሪካ-በፀጥታው-ም-ቤት-ቋሚ-መቀመጫ-እንዲ/
ግብጽ ወይስ ሴኔጋል – ሁለቱን የሊቨርፑል ኮከቦች በተቃራኒው ያገናኘው የፍጻሜ ጨዋታ



https://www.fanabc.com/ግብጽ-ወይስ-ሴኔጋል-ሁለቱን-የሊቨርፑል-ኮ/
የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ባስቀመጠው አቅድ መሰረት የህብረቱ የመሪዎች ጉባኤ ሰላማዊ ሂደቱን ጠብቆ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጸጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ባስቀመጠው አቅድ መሰረት የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ሰላማዊ ሂደቱን ጠብቆ እየተካሄደ መሆኑን የጋራ ግብረ ኃይሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡   የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለጉባኤው ሰላማዊነት እያደረጉት ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የጋራ ግብረ-ኃይሉ ጥሪ አቅርቧል።   የአፍሪካ ህብረት 40ኛው የስራ አስፈጻሚ…

https://www.fanabc.com/የጸጥታና-ደህንነት-የጋራ-ግብረ-ኃይል-ባስ/
ለስኬት ያልበቃው የአፍሪካ ህብረት ሙከራ (በበላይ በቀለ)



https://www.fanabc.com/ለስኬት-ያልበቃው-የአፍሪካ-ህብረት-ሙከራ/
የእጩ ኮሚሽነሮች ምርጫ ኢትዮጵያዊ ብዝኃነትን ያካተተ እንዲሆን ተሞክሯል-አፈ ጉበዔ ታገሳ ጫፎ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን እጩ ኮሚሽነሮችን ለመምረጥ በተደረገው ሂደት ኢትዮጵያዊ ብዝሃነትን ያካተተ እንዲሆኑ ለማስቻል ጥረት መደረጉን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉበዔ ታገሳ ጫፎ ገለጹ።   አፈ-ጉበዔው እጩ ኮሚሽነሮችን አስመልክቶ ለሕዝብ አስተያየት መስጫ በተዘጋጀ መድረክ ላይ እንደተናገሩት÷እጩ ኮሚሽነሮቹ ለዚህ ታሪካዊ ሃላፊነት ሲታጩ በአገራችን አንድነትና በኢትዮጵያዊነት መሰረት ቆመው…

https://www.fanabc.com/የእጩ-ኮሚሽነሮች-ምርጫ-ኢትዮጵያዊ-ብዝኃ/