FBC (Fana Broadcasting Corporate)
198K subscribers
60.1K photos
736 videos
23 files
53.8K links
This is FBC's official Telegram channel.

For more updates please visit www.fanabc.com
Download Telegram
የትግራይ ሕዝብ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላሙን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ከፍጻሜ እንዲደርሱ ሕዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላሙን እንዲጠብቅ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በትግራይ ደቡብ ምሥራቅ ዞን በሕዝብ ከተወከሉ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ጋር በወቅታዊ ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም የውይይቱ ዋና ዓላማ “በክልሉ የተጀመሩ ሥራዎች እንዴት ማጠናቀቅ እንዳለብን በመነጋገር የመፍትሄ ሐሳቦችን ለማስቀመጥ ነው” ብለዋል፡፡

የትግራይ ሕዝብ አሁን ላይ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰላምና አንድነት ያስፈልገዋል ያሉት አቶ ጌታቸው፥ በዚህም የክልሉ ሕዝብ የልማት ተግባራቱን እያከናወነ ሰላሙንና አንድነቱን መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ሕዝቡ የጀመራቸውን የልማት ሥራዎች ከዳር ለማድረስም ይጠበቅበታል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
እስራኤል ተጨማሪ የሂዝቦላህ ከፍተኛ አመራር መግደሏን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል በሊባኖስ በፈጸመችው የአየር ላይ ጥቃት ተጨማሪ የሂዝቦላህ ከፍተኛ አመራር መግደሏን አስታውቃለች፡፡ በሊባኖስ በመሸገው ሂዝቦላህ ላይ የሚወሰደው ሁለንተናዊ እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ገልጿል፡፡ በዛሬው ዕለትም በቤሩት በተመረጡ የሂዝቦላህ ይዞታዎች ላይ የተሳካ የአየር ላይ ጥቃት መፈጸሙን ጦሩ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል፡፡ በዚህም የሂዝቦላህ ደህንነት ሃላፊና…

https://www.fanabc.com/archives/264017
በሐረሪ ክልል የኮደርስ ስልጠና በተደራጀ አግባብ እየተሰጠ መሆኑ ተመላከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የኮደርስ ስልጠና በተደራጀ አግባብ እየተሰጠ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ተናገሩ። አቶ ኦርዲን እንዳሉት÷የኮደርስ ስልጠና በርካታ ዜጎች በቴክኖሎጂ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ያለንበት ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን በመሆኑ ወጣቱ በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንዲሳተፍ ለማድረግ ስልጠናው አይተኬ ሚና አለው ብለዋል። በሐረሪ…

https://www.fanabc.com/archives/264021
ባለሃብቶች በክልሉ ኢንቨስት በማድረግ ኢኮኖሚን ለማሻሻል መስራት አለባቸው – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለሃብቶች በኢንቨስትመንት ዘርፍ በመሰማራት ኢኮኖሚን ለማሻሻል መስራት አለባቸው ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡ ርዕሰ መስተዳደሩ በአርባምንጭ ከተማ በግል ባለሃብት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነባውን ሆቴል መርቀው ከፍተዋል፡፡ አቶ ጥላሁን በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ባለሃብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች በመሰማራት ኢኮኖሚን ለማሳደግ ጉልህ…

https://www.fanabc.com/archives/264024
ሩሲያ 125 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትታ ጣለች

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ የሀገሪቱን አየር ክልል ጥሰው የገቡ 125 የዩክሬን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መትታ መጣሏን ገልጻለች፡፡ ጥቃት ለማድረስ የአየር ክልል ጥሰው የገቡ 125 ዩኤቭ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በተሰካ ሁኔታ ማምከን መቻሉን የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ 67 ድሮኖች በደቡባዊ ሩሲያ መምከናቸውን የአካባቢው አስተዳዳሪ አንድሪይ ቦቻሮቭ የተናገሩ ሲሆን÷ ምንም…

https://www.fanabc.com/archives/264027
በክልሉ የኮሪደር ልማት ሥራን ለማጠናከር የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ሥራ አጠናክሮ ለማስቀጠል የተቀናጀ ርብርብ እንደሚያስፈልግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ገለጹ፡፡ የኮሪደር ልማት ሥራን በክልሉ ሁሉም ከተሞች ተግባራዊ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ አቶ ጥላሁን በዚህ ወቅት÷ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የኮሪደር ልማት ሥራን…

https://www.fanabc.com/archives/264030
አቶ አሻድሊ ለኮደርስ ስልጠና ስኬታማነት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ለኮደርስ ስልጠና ስኬታማነት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አቶ አሻድሊ÷የተጀመረው የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ሥልጠና የዲጂታል ኢትዮጵያን ስኬት እውን ለማድረግ የተያዘውን ጥረት ለማሳካት ያስችላል ብለዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ዜጎች የቴክኖሎጂ እውቀታቸውን በማዳበር በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ…

https://www.fanabc.com/archives/264033
የልብ ህመምን ጨምሮ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሚያስከትሉት ጫና አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሚያስከትሉት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ዜጎች የአመጋገብ ሥርዓትን በማስተካከል ተጋላጭነታቸውን መቀነስ እንዳለባቸው ጤና ሚኒስቴር አሳሰበ። የኢትዮጵያ የልብ ማኅበር ከጤና ተቋማት ጋር በመተባበር “ልብን ለተግባር እናውል” በሚል መሪ ሃሳብ ዓለም አቀፉ የልብ ቀን በአዲስ አበባ አክብሯ። በኢትዮጵያ ለ9ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ…

https://www.fanabc.com/archives/264036
Live stream finished (12 minutes)
ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው በቶተንሃም ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቶተንሃም ሆትስፐር ማንቼስተር ዩናይትድን አሸንፏል፡፡

ምሽት 12፡30 ላይ በኦልትራፎርድ በተደረገው ጨዋታ ቶተንሃም ሆትሰፐር ማንቼስተር ዩናይትድን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የቶተንሃም ሆትስፐርን የማሸነፊያ ግቦች ቤሬናን ጆንስን፣ ኩልሴቭስኪ እና ዶሚኒክ ሶላንኬ አስቆጥረዋል፡፡

በማንቼስተር ዩናይትድ በኩል አምበሉ ቡሩኖ ፈርናንዴዝ ከእረፍት በፊት በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡

ቀድም ብሎ 10 ሰዓት ላይ በተደረገ ጨዋታ ኢፕስዊች ታውን ከአስቶንቪላ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።
በመዲናዋ በትራፊክ አደጋ የ2 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ከገላን ወደ ሰፈራ በሚወስደው መንገድ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 2 የመንገድ ዳር ችግኝ የሚንከባከቡ ሠራተኞች ሕይወት አለፈ፡፡

አደጋው በተለምዶ ሰፈራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቀኑ 11:30 ላይ አንድ ሲኖትራክ ተሽከርካሪ እና የህዝብ አይሱዙ ተሽከርካሪ ተጋጭተው ነው የደረሰው፡፡

በዚህም የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉና በ4 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንዲሁም ለጊዜው ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ሕክምና እየተከታተሉ መሆኑንም የክ/ከተማው ፖሊስ መረጃ አመላክቷል።