TIKVAH-ETHIOPIA
#Sidama በመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ። በሲዳማ ክልል ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ፣ ወንሾ ወረዳ ግሽሬ ጉዱ ሞና ሆሞ በሚባለው አካባቢ ትላንት የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰምቷል፡፡ በመሬት መንሸራተት አደጋ ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ በ6 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል፡፡ #SidamaRegionCommunication…
#Update

በሲዳማ ክልል በወንሾ ወረዳ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ወገኖቻችን ቁጥር 9 ደርሷል።

6 ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በይርጋለም ሆስፒታል ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ፤ በዛው ሲዳማ ክልል በቡራ ወረዳ በድንገተኛ ውኃ ሙላት የሁለት ሕጻናት ሕይወት አልፏል። #ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia