TIKVAH-ETHIOPIA
#Haile " ሙሉን አፍርሰን እየገነባን ነው። ከመንግሥት ምንም ማካካሻ አልተደረገልኝም " - ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ከዚህ በፊት በሻሸመኔ በጸጥታ ችግር ስለወደመው ሆቴል ሁኔታ እና በጎንደር  ከተማ በሚገኘው ሪዞርት በኩል በጸጥታ ችግር የገጠማቸውን የገቢ መቀዛቀዝን በተመለከተ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሆቴል ምረቃ መርሀ ግብር በተገኙበት ወቅት ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከዚህ…
ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ምን አሉ ?

ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ከ2 ሳምንት በፊት በወላይታ ሶዶ ሆቴላቸው ባስመረቁበት ዕለት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ነበራቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በዋነኝነት ያነሳው ከፀጥታ ጋር በተገናኘ በስራቸው ላይ እየተፈጠረ ስላለው ተግዳሮት ነው።

ሻለቃ ኃይሌ የጎንደር ኃይሌ ሪዞርትን በተመለከተ ፤ " 56 ሩሞች አሉኝ፣ አራትም አምስትም ሰዎች እያደሩበት ነው " ብለዋል።

ይህም በክልሉ የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር እንደሆነ ጠቁመዋል።

ገቢው በምን ያህል ቀንሷል ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ " አለ እንዴ ለመሆኑ ቢዝነሱ " ብለው፣ " 56፣ 57 ሩም ተይዞ አምስት ሰዎች ስላሳደርክ ምንድን ነው ገቢው ? በግማሽ ፐርሰንት ነው ? በምን ፐርሰንት ነው? አላውቅም " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ፦

- እኔ አሁን እንደዚህ ሳወራ ‘እሱ ደግሞ ስለ ሆቴል ያወራል እንዴ? ሰው እንደዚህ እየሞተ’ ሊባል ይችላል። አዎ ልክ ነው። ሰው እየሞተ ነው። ግን እኔ ኃላፊነት አለብኝ እዛ ውስጥ ላሉ #ሠራተኞች።

- የሆቴል ቢዝነስ የሚበረታታ አይደለም። የገበያው መጥፋት አንዱ Problem ሆኖ፣ Major Problem ደግሞ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች መወደድ ነው። ከውጭ ማምጣት በጣም አስቸጋሪ ሆኗል። ብናመጣም በጣም ጥቃቅን ነገሮችን ነው።

- አሁን እኮ ባይገርምህ የምንበላበት ሰራሚክ ሰሀን ነው እያጣን ያለነው። ይሄ ለምን ሆነ ? አትልም የጋራ ችግር ነው። 

- ቁጥር አንድ የጸጥታውን ችግር ማስቆም። የጸጥታው ችግር ካልቆመ እንኳን ቱሪስት እኛም ወደዚህ ለመምጣት (ወደ ወላይታ ሶዶ) አልቻልንም።

- በ24 ሰዓት አርባምንጭ ደርሸ ስራየን እሰራ ነበር። የዛሬ 6 ዓመት አሁን ግን ያ ተረትተረት ሁኖ ቀርቷል። ወደዛ ዓመት ካልተመለስን ምንም ዋጋ የለውም።

- ይኼ ነገር እስካልሆነ ድረስ እንዳውም አሁን Instead of that ሆቴሎች እየተዘጉ እያየን እኛ አሁን እያዋጣችሁ ነው የምትከፍቱ ? ያልከኝ እንደሆነ ተስፋ አለን።

- የዛሬ 8 ዓመት በአንድ ቀን ሌሊት 2 ሆቴሎች ሲቃጠሉ ባለቤት ሊኖረው ይገባል።

- እኔ እየተወጣሁ፣ ‘ይሄንን ቀጥረህ አሰርተህ፣ ይሄንን እንዲህ አድርግ’ ሳይሆን፣ ዋናው ኢምፓርታንቱ ታክስ እየከፈልኩ ነው።  ታክስ ስከፍል ደግሞ መጠበቅ፣ ችግር ደግሞ ሲገጥመኝ መንግሥት እንደ መንግሥት ‘ኦ ይሄ እኮ ግለሰቤ ታክስ ሳስከፍለው ኑሬአያለሁ፣ አሁን ደግሞ እኔ ሰላሙንና ፀጥታውን ደግሞ በአግባቡ ባለመወጣቴ ለዚህ መክፈል አለብኝ’ ብሎ ማሰብ አለበት።

- እኔ አላቃጠልኩትም መንግሥት እንደ መንግሥት መወጣት ነበረበት። እኛ ለብዙ ዓመታት እንግዲህ በኢንቨስትመንት ተሰማርተን ትልቅ ስራ እየሰራን ነው።

- እኔ ብቻ አይደለሁም ብዙ ሰዎች እንባቸውን አፍሰው ወደ ላይ እረጭተው ተቀምጠዋል። ይሄ ደግሞ ትክክል አይደለም። አትሊስት እንደ መንግሥት ኃላፊነት የሆነ ነገር መደረግ አለበት እንጅ።

- ዛሬ ለመውቀስ አይደለም። አይደለም ይሄ እንዳው ዝም ተብሎ እንኳ የሆነ ተራ ጨርቅ እንኳ ተቃጥሎ ያስቆጫል። 

- እኔ አሁን ሻሸመኔ ላይ ስመጣ ሁል ጊዜ እዛ ግቢ በር ያ ሁሉ እቃ ተቃጥሎ ተከምሯል። በእውነት እንደ ልማት ያው እኔ ብቻ አይደለሁም የሀገር ሀብት ነው የሀገር ልፋት ነው።

ያንብቡ ፦https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-02-12

@tikvahethiopia