TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች ዛሬ መግለጫ አውጥተዋል። መግለጫቸው ፤ በአውሮፓ ኅብረት እና በአፍሪካ፣ በካሪቢያንና በፓስፊክ ሀገራት መካከል የተፈረመውንና የሳሞአ ስምምነት በመባል የሚታወቀውን የንግድና የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነት የተመለከተ ነው። ጉባኤው ስምምነቱ ተካተውበታል ያላቸውን ጎጂ ሀሳቦች በዝርዝር አስፍሯል። ከነዚህም መካከል ፦ - በስምምነቱ…
ስለ ግብረሰዶማዊነት እና ተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ ?

ዛሬ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ነው ስላላቸው ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

ቋሚ ሲኖዶስ ምን አለ?

- ግብረ ሰዶማዊነት በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተገለጸው ለአንድ ሀገርና ሕዝብ ከነጎረቤቶቹ መጥፋት ምክንያት የሆነ ተግባር ነው። የሰዶምና ገሞራ በመቅሰፍተ እሳት መቃጠል ከእነርሱ መቀጣትም  አልፎ ላለውና ለመጪው ትውልድ አስተማሪ የሆነ ምልክት እንዲሆን ነው።

- ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ግብረ ሰዶማዊነትን የምትቃወመው ተፈጥሮዋዊ ስላልሆነ ብቻ ሳይሆን በብሉይ  ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ትምህርት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ፣ ተቀባይነት የሌለው፣ ኃጢአት በመሆኑ ነው፡፡

- ቅድስት ቤተክርስቲያን ጾታዊ ግንኙነት ወይም የተቀደሰ ጋብቻ በተቃራኒ ጾታዎች ብቻ የሚፈጾም እንዲሆን ታስተምራለች።

- ግብረ ሰዶማዊነት የሰውን ልጅ ተፈጥሯዊ ማንነት የሚንድ፣ መሠረተ እምነትንና ቀኖናን የሚሽር፣ ማኅበራዊ ዕሴት የሚያጠፋ፣ ከሥነ ምግባር መገለጫዎች በአሉታዊ ገጽ የቆመ፣ ሕሊናን የሚያውክ ለትውልድ ጥፋት፣ ለሀገር መውደም ምክንያት የሆነ አጸያፊ ተግባር ነው፡፡

- ቅድስት ቤተክርስቲያን ይህን ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ወደ ንሥሓና ድኅነት እንዲመጡ፣ ከሥጋና ከመንፈስ ስብራት እንዲፈወሱ ዘወትር ጥሪ ታደርጋለች እንጅ ማንም ሰው የኃጢአቱ ወይም የርኩሰቱ ተባባሪ እንዲሆን አትፈቅድም።

- በሀገራችን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕግ የተከለከለ ነው።

- ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህን ተግባር (የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ) በግልጥ በሕገ መንግሥታቸውና በልዩ ልዩ ማኅበራዊ ድንጋጌዎቻቸው እንደ ጥሩ ነገር እንደ ፍትሐዊነትና አካታችነት በመቁጠር በይፋ የደነገጉ የምዕራቡ ዓለም ሀገራት መኖራቸው ግልጽ ነው። እነዚሁ ሀገራት ያላቸውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም መከታ በማድረግ በእምነታቸው፣ በባሕላቸው በማኀበራዊ መገለጫቸው ይህን አጸያፊ ድርጊት ፈጽመው በማይቀበሉ የአፍሪካና የምሥራቁ ዓለም ሀገራት ላይ ቢቻል በማግባባት፣ ካልሆነም የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና በማሳደር እንዲቀበሉ የጥፋት ልማዳቸውን እንዲጋሩ ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉትን ድብቅና ግልጽ እንቅስቃሴዎችን እንቃወማለን።

- ይህ ግብረ ርኩሰት በዘመናችን ተቀባይነት እንዲኖረው፣ የሚደረጉ ሁለገብ ማግባባቶች ፣ተጽዕኖዎችና ተያያዥነት ያላቸው ስምምነቶች በሀገራችን መንግሥት ተቀባይነት አግኝተው እንዳይፈጸሙ በጥብቅ እናሳስባለን።

- ከመገናኛ ብዙኃንና ከሌሎችም የመረጃ ምንጮች ለማወቅ እንደተቻለው ግብረ ሰዶማዊነትንና ተያያዥነት ያላቸውን ተግባራት የንግድ፣ የፖለቲካ ፣ የኢኮኖሚ ፣የፍትሕና የሰብዓዊነት ግንኙነቶች አካል በማድረግ በቃላትና በዓረፍተ ነገሮች ውስጥ አስርጎ በማስገባት አሣሪ ስምምነቶች እንዲፈጸሙ ለማድረግ ያለው ሃደት በአፋጣኝ እንዲፈተሽ። የሀገራችን መንግሥት ብሎም የአፍሪካ መንግሥታት የአህጉራችንን ሃይማኖታዊ ማኅበራዊና ሥነ ልቦናዊ ዕሴቶች አስጠብቀው እንዲቀጥሉ ጥብቅ ጥሪ እናቀርባለን።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

አቶ ጌታቸው ረዳ ምን አሉ ?

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በዛሬው እለት በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ቃለመጠይቅ ለክልሉ ሚድያዎች ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፤ የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ተሳትፎውበት ከፌደራል መንግስት ጋር በአዲስ አበባ ስለተካሄደው ውይይትና ውጤት አስመልክቶ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።

አቶ ጌታቸው ፤ " ለፌደራል መንግስት የስራ አፈፃፀም ሪፓርት አቅርበናል። በአከባቢያችን ያለው ፓለቲካዊ ሁኔታ እጅግ ጥንቃቄ የሚሻ በመሆኑ እንደ አገር የውስጥ ሰላማችን መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባ ከፌደራል መንግስት ጋር መግባባት  ተደርሷል " ብለዋል።

ከፌደራል መንግስት በተካሄደው ውይይት በሃይል ስለተያዙ የትግራይ ግዛቶች መነሳቱ ያብራሩት ፕረዚደንቱ " በተለይ በምዕራባዊ ዞን  በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ሰፋሪዎች በሰፈሩበት፤ የፌደራል ተቋማት ዴሞግራፊ ለመቀየር በሚንቀሳቀሱበትና ተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው ባልተመለሱበት ፤ መፍረስ የሚገባቸው ሳይፈርሱ ፤ ህዝባችን ነፃ ባልወጣበት ሁኔታ ሪፈረንደም ማድረግ አይቻልም " ሲሉ ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ወር መጋቢት የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታትና የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች በተገኙት የፕሪቶሪያ ስምምነት አተገባበር ላይ ያተኮረ ውይይት ይካሄዳል ያሉት አቶ  ጌታቸው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለውይይቱ ስኬት የበኩሉ አስተዋፅኦ ለማድረግ ዝግጁ ነው ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ህወሓት መልሶ እንደ ፓለቲካ ፓርቲ የመመዝገብ ጉዳይ የሚመለከት ጥያቄም ቀርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

በዚህም፤ ከህወሓት የፓለቲካ ፓርቲነት ምዝገባ ጋር ተያይዞ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ የፌደራል መንግስት እንደማይደግፈው በመግለፅ ያለው የህግ ክፍተት በአስቸኳይ ታርሞ ምዝገባው እንዲፈፀም ጉዳዩ ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ተመርቷል ብለዋል።

መረጃውን የትግራይ ሚድያዎችን ዋቢ አድርጎ ያዘጋጀድ የመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።
                 
@tikvahethiopia            
#ሜትርታክሲ #ሀይገርባስ

ገቢዎች ሚኒስቴር ስለ ሀይገር ባስ እና ሜትር ታክሲዎች ምን አለ ?

የገቢዎች ሚኒስቴር ፤ የሀይገር ባስ እና የሜትር ታክሲዎች የታክስ አከፋፈል ስርዓት ውሳኔ ሳያገኝ በእንጥልጥል ቆይቷል ብሏል።

ነገር ግን ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ በንግድና በታክስ ህጉ መሠረት ተፈጻሚ መደረግ እንዳለበት ተገልጾ ከገንዘብ ሚኒስቴር ውሳኔ እንደተሰጠበት ገልጿል።

በዚህም ፦

1ኛ. የታክሲ ማህበራት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 17 መሰረት የሂሳብ መዝገብ መያዝ የሚጠበቅባቸው የደረጃ " ሀ " ታክስ ከፋዮች በመሆናቸው የሂሳብ መዝገብ ይዘው የሚጠበቅባቸውን ግብር አስታውቀው እንዲከፍሉ፤

2ኛ. ዓመታዊ ግብራቸውን በሂሳብ መዝገብ ካላቀረቡ በገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 410/2009 እና በመመሪያ ቁጥር 138/2010 በትራንስፖርት ቁርጥ ግብር ስርአት መሰረት አመታዊ የገቢ መረጃ እየተወሰደ እንደ ድርጅት በተሸከርካሪዎቹ  ዓይነትና ምርት ዘመን ግብር በሚከፈልበት ገቢ ላይ 👉 30 በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር በግምት እንዲሰላና መዝገብ ባለመያዝ በህጉ መሰረት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጠየቁ፤

3ኛ. የአክሲዮን ማህበራት በንግድ ህጉ መሠረት ለአባላት የሚከፈለው የትርፍ ድርሻ (Dividend) ግብር  የሚከፈልበት ስለሆነ የሂሳብ መዝገብ ካልያዙ አመታዊ የተጣራ ትርፍ ላይ ወይም በቁርጥ ግብር የገቢ መጠን ተመስርቶ የንግድ ትርፍ ግብር ከተከፈለ ግብር ከሚከፈልበት ገቢ ላይ የተከፈለው ግብር ተቀንሶ ቀሪው መጠን ላይ ህጉን ተከትለው ካፒታላቸውን እስካላሳደጉ ድረስ የትርፍ ድርሻ ግብር 👉 10 በመቶ እንዲከፍሉ እንዲደረግ እንደተወሰነ ለግብር ከፋይ የሀይገር ባስና ሜትር ታክሲ ባለንብረቶች አሳውቋል።

@tikvahethiopia‌‌
#አቢሲንያ_ባንክ

በቨርችዋል ባንካችን 24/7 ገንዘብ ማስገባት ይችላሉ።


አቢሲንያ የሁሉም ምርጫ!

#virtualbanking #bankinginethiopia #banksinethiopia #ITM #bankofabyssinia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Haile " ሙሉን አፍርሰን እየገነባን ነው። ከመንግሥት ምንም ማካካሻ አልተደረገልኝም " - ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ከዚህ በፊት በሻሸመኔ በጸጥታ ችግር ስለወደመው ሆቴል ሁኔታ እና በጎንደር  ከተማ በሚገኘው ሪዞርት በኩል በጸጥታ ችግር የገጠማቸውን የገቢ መቀዛቀዝን በተመለከተ ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ የሆቴል ምረቃ መርሀ ግብር በተገኙበት ወቅት ማብራሪያ ሰጥተዋል። ከዚህ…
ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ምን አሉ ?

ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ ከ2 ሳምንት በፊት በወላይታ ሶዶ ሆቴላቸው ባስመረቁበት ዕለት ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ ነበራቸው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ በዋነኝነት ያነሳው ከፀጥታ ጋር በተገናኘ በስራቸው ላይ እየተፈጠረ ስላለው ተግዳሮት ነው።

ሻለቃ ኃይሌ የጎንደር ኃይሌ ሪዞርትን በተመለከተ ፤ " 56 ሩሞች አሉኝ፣ አራትም አምስትም ሰዎች እያደሩበት ነው " ብለዋል።

ይህም በክልሉ የሚስተዋለው የጸጥታ ችግር እንደሆነ ጠቁመዋል።

ገቢው በምን ያህል ቀንሷል ? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም፣ " አለ እንዴ ለመሆኑ ቢዝነሱ " ብለው፣ " 56፣ 57 ሩም ተይዞ አምስት ሰዎች ስላሳደርክ ምንድን ነው ገቢው ? በግማሽ ፐርሰንት ነው ? በምን ፐርሰንት ነው? አላውቅም " ሲሉ ተናግረዋል።

አክለውም ፦

- እኔ አሁን እንደዚህ ሳወራ ‘እሱ ደግሞ ስለ ሆቴል ያወራል እንዴ? ሰው እንደዚህ እየሞተ’ ሊባል ይችላል። አዎ ልክ ነው። ሰው እየሞተ ነው። ግን እኔ ኃላፊነት አለብኝ እዛ ውስጥ ላሉ #ሠራተኞች

- የሆቴል ቢዝነስ የሚበረታታ አይደለም። የገበያው መጥፋት አንዱ Problem ሆኖ፣ Major Problem ደግሞ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች መወደድ ነው። ከውጭ ማምጣት በጣም አስቸጋሪ ሆኗል። ብናመጣም በጣም ጥቃቅን ነገሮችን ነው።

- አሁን እኮ ባይገርምህ የምንበላበት ሰራሚክ ሰሀን ነው እያጣን ያለነው። ይሄ ለምን ሆነ ? አትልም የጋራ ችግር ነው። 

- ቁጥር አንድ የጸጥታውን ችግር ማስቆም። የጸጥታው ችግር ካልቆመ እንኳን ቱሪስት እኛም ወደዚህ ለመምጣት (ወደ ወላይታ ሶዶ) አልቻልንም።

- በ24 ሰዓት አርባምንጭ ደርሸ ስራየን እሰራ ነበር። የዛሬ 6 ዓመት አሁን ግን ያ ተረትተረት ሁኖ ቀርቷል። ወደዛ ዓመት ካልተመለስን ምንም ዋጋ የለውም።

- ይኼ ነገር እስካልሆነ ድረስ እንዳውም አሁን Instead of that ሆቴሎች እየተዘጉ እያየን እኛ አሁን እያዋጣችሁ ነው የምትከፍቱ ? ያልከኝ እንደሆነ ተስፋ አለን።

- የዛሬ 8 ዓመት በአንድ ቀን ሌሊት 2 ሆቴሎች ሲቃጠሉ ባለቤት ሊኖረው ይገባል።

- እኔ እየተወጣሁ፣ ‘ይሄንን ቀጥረህ አሰርተህ፣ ይሄንን እንዲህ አድርግ’ ሳይሆን፣ ዋናው ኢምፓርታንቱ ታክስ እየከፈልኩ ነው።  ታክስ ስከፍል ደግሞ መጠበቅ፣ ችግር ደግሞ ሲገጥመኝ መንግሥት እንደ መንግሥት ‘ኦ ይሄ እኮ ግለሰቤ ታክስ ሳስከፍለው ኑሬአያለሁ፣ አሁን ደግሞ እኔ ሰላሙንና ፀጥታውን ደግሞ በአግባቡ ባለመወጣቴ ለዚህ መክፈል አለብኝ’ ብሎ ማሰብ አለበት።

- እኔ አላቃጠልኩትም መንግሥት እንደ መንግሥት መወጣት ነበረበት። እኛ ለብዙ ዓመታት እንግዲህ በኢንቨስትመንት ተሰማርተን ትልቅ ስራ እየሰራን ነው።

- እኔ ብቻ አይደለሁም ብዙ ሰዎች እንባቸውን አፍሰው ወደ ላይ እረጭተው ተቀምጠዋል። ይሄ ደግሞ ትክክል አይደለም። አትሊስት እንደ መንግሥት ኃላፊነት የሆነ ነገር መደረግ አለበት እንጅ።

- ዛሬ ለመውቀስ አይደለም። አይደለም ይሄ እንዳው ዝም ተብሎ እንኳ የሆነ ተራ ጨርቅ እንኳ ተቃጥሎ ያስቆጫል። 

- እኔ አሁን ሻሸመኔ ላይ ስመጣ ሁል ጊዜ እዛ ግቢ በር ያ ሁሉ እቃ ተቃጥሎ ተከምሯል። በእውነት እንደ ልማት ያው እኔ ብቻ አይደለሁም የሀገር ሀብት ነው የሀገር ልፋት ነው።

ያንብቡ ፦https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-02-12

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአፍሪካ ሕብረት ጉባኤ መቼ ነው ? 37ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። 44ኛው የአባል ሀገራቱ የሥራ አስፈጻሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከመሪዎች ጉባዔ ቀደም ብሎ የካቲት 6 እና 7 ቀን 2016 ዓ.ም ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል። የአፍሪካ ሕብረት የ2024 መሪ ቃል " ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ…
#AU

የሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ጨምሮ የተለያዩ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ነው።

በ44ኛው የአፍሪካ ህብረት የአስፈፃሚዎች ም/ቤት ስብሰባ ላይ የሚሳተፉ የተለያዩ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ እየገቡ ናቸው።

ከትላንትና ምሽት ጀምሮ የሶማሊያ ፣ ቡሩንዲ ፣ ኬኘቨርዲ ፣ ኮሞሮስ እና የካሚሮን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አዲስ አበባ ገብተዋል።

የህብረቱ የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ስብሰባ ከነገ ጀምሮ ለ2 ቀናት የሚካሄድ ይሆናል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara #Merawi በአማራ ክልል ፤ በየጊዜው በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መከላከያ እና በ " ፋኖ " ታጣቂ ኃይሎች መካከል ግጭቶች ይደረጋሉ። በእነዚህ ግጭቶችም በሁለቱም በኩል ከሚሞተው የግጭቱ ተካፋይ ባለፈ ንፁሃን ሰዎች ሰለባ እየሆኑ እንዳለ በተደጋጋሚ ተገልጿል። ምንም እንኳን #መንግሥት ፤ " ከእውነታው ያፈነገጠ እና ሚዛናዊነት የጎደለው " ብሎ ቢያጣጥለውም የኢትዮጵያ…
" ' ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል ' እንዲሁም የ ' ፋኖ አባላት ናቸው ' በሚል ሲቪሎች ተገድለዋል " - ኢሰመኮ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ በአማራ ክልል አሳሳቢነቱ ስለቀጠለው የትጥቅ ግጭት እና በሲቪል ሰዎች ላይ ስለተፈፀመው ከሕግ ውጭ ግድያ  ዛሬ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫ ፤ የመንግሥት ኃይሎች በሰሜን ጎጃም ዞን፤ መርዓዊ ከተማ ከህግ ውጭ ግድያ መፈፀማቸውን አሳውቋል። እስካሁን ማንነታቸውን ለይቶ በተረጋገጠው 45 ሲቪል ሰዎች ተገድለዋል። ቁጥሩ ግን ከዚህም ሊጨምር እንደሚችል ጠቁሟል።

ኢሰመኮ ምን አለ ?

- በመርዓዊ ከተማ ጥር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በታጠቁ ኃይሎች (በተለምዶ ፋኖ በመባል የሚጠሩት) መካከል ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት አካባቢ ጀምሮ ውጊያ ተካሂደ ነበር።

- እስከ አሁን ድረስ በተደረገ ክትትል ኮሚሽኑ ማንነታቸውን ማረጋገጥ የቻላቸውን ቢያንስ 45 ሲቪል ሰዎችን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች " ለፋኖ ድጋፍ አድርጋችኋል '' በሚል ምክንያት ከሕግ ውጭ ገድለዋል።

- " የፋኖ አባላት ናቸው " በሚል ተጠርጥረው የተያዙ እና ለጊዜው ብዛታቸውን ለማረጋገጥ ያልተቻለ ሰዎች በተመሳሳይ ሁኔታ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡

- እስከአሁን ድረስ ማንነታቸውን በመለየት ለማረጋገጥ የተቻለው 45 ሲቪል ሰዎችን ብቻ ሲሆን፤ ነገር ግን የጉዳቱ መጠን ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል ምክንያታዊ ግምት ለመውሰድ ተችሏል።

- ምስክሮች በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ ለኢሰመኮ ሲገልጹ፣ ለቀን ሥራ በጠዋት ከቤታቸው ወጥተው ድንገት ተኩስ ሲከፈት በአንድ ቦታ ተጠልለው የነበሩ 18 ሲቪል ሰዎች የተገደሉ መሆኑን ገልጸዋል።

- ምስክሮች ቀበሌ 02 አካባቢ በተለምዶ ሚሊኒየም ተብሎ በሚጠራ ሰፈር አንድ የጠፋ አባልን ሲያፈላልጉ የነበሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች " በፍለጋው አልተባበሩም " ያሏቸውን 8 ሲቪል ሰዎችን መግደላቸውን እንዲሁም 12 ባጃጆች በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች መቃጠላቸውን ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ፦

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሽበል በረንታ ወረዳ የዕድውኃ ከተማ ጥር 10 ቀን 2016 ዓ.ም. በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ ታጣቂዎች ከተማዋን ለቀው ከወጡ በኋላ ቤት ለቤት በተደረገ ፍተሻ፣ እንዲሁም መንገድ ላይ የተገኙ ቢያንስ 15 ሰዎች (ሴቶችን ጨምሮ) በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ ተገድለዋል።

በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል።

እንዲሁም በምዕራብ ጎጃም ዞን፣ ቋሪት ወረዳ፣ ወይበይኝ ቀበሌ፣ አብሥራ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ጥር 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ለወታደራዊ ቅኝት በአካባቢው የተሰማሩ የመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሳ 6 ሲቪል ሰዎችን ከየቤታቸው አውጥተው ከሕግ ውጭ እንደገደሏቸው ምስክሮች ለኢሰመኮ አስረድተዋል፡፡

(ከኢሰመኮ የተላከልን መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ነዳጅ ሲቀዱ የስልክ ቁጥርዎን መንገር ሳይጠበቅብዎ ቴሌብር ሱፐርአፕን http://onelink.to/fpgu4m በመጠቀም ብቻ ክፍያ ይፈጽሙ!

በቴሌብር ሱፐርአፕ አስቀድመው፣ ለአንድ ጊዜ ብቻ ታርጋዎን እና አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት ተሸከርካሪዎን ነዳጅ ሲያስሞሉ የብር መጠኑን ብቻ በማስገባት ኪው.አር ኮድዎን በነዳጅ ቀጂዎ ስካን በማስደረግ ክፍያዎን በቀላሉ መፈጸም ይችላሉ።

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EMA ከ600 በላይ የሕክምና ባለሙያዎችና ውሳኔ ሰጪዎች ውይይት ሊያደርጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ገለጸ። የማኀበሩ ራዕይ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችል ጤናማና የበለጸገ ማህበረሰብ እውን ለማድረግ ይረዳ ዘንድ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መ/ቤቶች የጤና ሚኒስትርን ጨምሮ የማህበረሰብ ክፍሎች፣ ከስፔሻሊቲ ሶሳይቲዎች፣ ከማኀበሩ አባላት ጋር በመሆን ምክክር የሚያደርግበት ዓመታዊ…
#EMA

የቲክቫህ ኢትዮጵያ የአዲስ አበባ አባል ፤ ከኢትዮጵያ ሕክምና ማኀበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትዕግስት መኮንንን ጋር ቆይታ  አድርጎ ነበር።

በዚህም ወቅት መሰረታዊ የሚባሉ ጥያቄዎችን አንስቷል።

1ኛ. በጤና ተቋማት እየታዩ ያሉና ትኩረት የሚሹ ችግሮች ምንድን ናቸው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" አሁን በስፋት በዋነኝነት እንደተግዳሮት ሆኖ የሚታየው የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት መኖር ነው።

የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት በሚፈለገው ልክ ተቋማት  የሚጠበቅባቸውን ሥራ ለመስራት ትልቅ ተግዳሮት እየሆነ ነው። "

2ኛ. ማህበሩ #የጤና_ባለሙያዎችን ጉዳዮች ተደራሽ ማድረግ አንዱ ዓላማው እንደመሆኑ መጠን በደመወዝ እጥረት የጤና ባለሙያዎች ወደ ውስጥም ሆነ ውጪ አገራት እየፈለሱ (የትግራይ ክልል) መሆኑን በተመለከተ ማኅበሩ እንደማኀበር ምን እየሰራ ነው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" እርግጥ ነው ይሄ ነገር ማኀበሩ እውቅና የሚሰጠው ጉዳይ ነው። ከሥራ ማጣት ጋርም ተያይዞ፣ ከተለያዩ ችግሮች አንፃር የባለሙያዎች ፍልሰት እንዳለ እሙን ነው። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ እንደዚህ ነው የሚል ጥናታዊ ፅሑፍ አልሰራንም።

ግን ችግሩ እንዳለ፣ በጥልቀት አትኩሮት መሰጠት እንዳለበትም ለተለያዩ አካላት ግብዓት ስንሰጥ ቆይተናል።

ይሄ አገሪቱም ካለችበት የኢኮኖሚ ጉዳይ፣ ለጤና ሴክተሩ ከሚሰጠው ትኩረት አንፃር እጥረት አለ፣ መድረስ ያለብን ደረጃ ላይ አልደረሰንም። ይህ ባለበት ሁኔታ የመፍለሱ፣ ሥራ የማጣቱ ጉዳይ እየታዬ ስለሆነ እንደ አገር ያለው ችግር ነው ለዚህ የዳረገው። "

3ኛ. የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደ ጤና ተቋማት የሚሄዱ ሕሙማን መጉላላት፣ የቀጠሮ መንዛዛት ስለሚገጥማቸው በወቅቱ መታከም ሲገባቸው ከሕመማቸው ጋር ለመቆየት እንደሚገደዱ ሕሙማን በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ ይደመጣል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ማኀበሩ ምን እየሰራ ነው ?

ወ/ሮ ትዕግስት መኮንን ፦

" የታካሚዎች መጉላላት፣ በወቅቱ የሚፈለገውን የሕክምና አገልግሎት አለማግኘት አጠቃላይ የሥርዓት ችግር ቢሆንም፣ ችግሩን ምን አመጣው ? በሚለው ጉዳይ ብዙ ነገሮች ሊጠቀሱ ይችላሉ።

ለምሳሌ፦ የሕክምና መሣሪያዎች ግብዓት እጥረት መኖር፣ ለጤና ሴክተር የሚሰጠው የበጀት እጥረት፣ ከዶላር ጋር ተያይዞ ያለው ችግር በቀጥታ ለዚህ ችግር አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ቁጥሩን ለመግለጽ ለጊዜው ባላስታውሰውም ማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት ፍላጎቱ እየጨመረ መጥቷል።

እንደ አጠቃላይ በታካሚዎች፣ በሐኪሞች፣ በዘርፉ ያለውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ውይይት የማኀበሩ 60ኛ ዓመታዊ ጉባኤ በዚህ ወር ሲደረግ ይነሳል። ይበልጥ ትኩረት ይሰጠዋል ተብሎ ይጠበቃል። "

#TikvahEthiopiaAA

@tikvahethiopia