" ወንጀሉ እየረቀቀ በመምጣቱ ከህብረተሰቡ ጋር ለመስራት የሚያስችል አሰራር ተዘርግቷል " - የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ

➡️ ጥቆማ መስጫ ነፃ የስልክ መስመር  6073

የአዲስ አበባ ፍትህ ቢሮ ከዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት(IOM) በጋራ በመተባበር  በሰው የመነገድ ሰውን በህገወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀል ለመከላከል የሚያስችለውን አሰራር በመዘርጋት ህብረተሰቡ መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ አቀረበ።

ቢሮው ከተማው የወንጀሉ መነሻ፣ መተላለፊያና መዳረሻ በመሆኑ ወንጀሉ የሚፈፀመው በህብረተሰቡ ውስጥ በመሆኑ  በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብሏል።

ወንጀሉ እየረቀቀ እና እየተወሳሰበ መምጣቱን የገለፀው ቢሮው ከህብረተሰቡ ጋር ለመስራት የሚያስችለውን አሰራር ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር መዘርጋቱን ይፋ አድርጓል።

በዚህም ፤ ህብረተሰቡ ወንጀሉን በጋራ ለመከላከል እንዲቻል በነጻ የስልክ መስመር 6073 ላይ መረጃ በመስጠት እንዲተባበር  ጥሪ አቅርቧል።

በሌላ በኩል ፥ ወንጀሉን በትብብር መከላከል የሚያስችሉ የተለያዩ አደረጃጀቶችን እስከ ወረዳ ድረስ በማደራጀት ወንጀሉን በተመለከተ  ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ፈጠራ ስራ በመስራት ላይ እንዳለ ይፋ አድርጓል።

@tikvahethiopia