TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ቦረና ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ከያቤሎ ወደ ሻሸመኔ ሲያቀና ይርጋጨፌ ላይ በደረሰው የመኪና መገልበጥ አደጋ የሞቱ ተማሪዎቹ 2 (ሴቶች) መሆናቸውን አሳውቋል።

የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ቀደም ብሎ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መልዕክት ሶስት ሴቶች እና ሁለት ወንዶች በአደጋው ህይወታቸው መላፉን አሳውቆ ነበር።

ህብረቱ ፤ ቀደም ብሎ የደረሰው መረጃ 5 ተማሪዎቹ ህይወታቸው እንዳለፈ የሚገልፅ ሲሆን በኃላ በተደረገው የማጣራት ስራ ሶስቱ የተቋሙ ተማሪዎች እንዳልሆኑ ታውቋል።

የቦረና ዩኒቨርሲቲ በደረሰው አሳዛኝ አደጋ ወደ ቤተሰቦቻቸው የሚመለሱ 2 ሴት ተማሪዎቹ ህይወታቸው እንዳለፈና 12 ተማሪዎቹ እንደተጎዱ አስረድቷል።

በደረሰው አደጋ ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናት ለተጎዱት ፈጣን ምሕረትን ተመኝቷል።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ በደረሰው አደጋ ከሞቱ 9 ሰዎች መካከል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አመራር አባሉ አቶ ሃምዛ ቦረና ወላጅ እናት ይገኙበታል።

ዘግይቶ የደረሰ ፦ ዛሬ ከሟቾች መካከል አንዲት ሴት የሪፍትቫሊ ዩኒቨርሲቲ አዳማ ካምፓስ ተማሪ እንደምትገኝበት ጓደኞቿ አሳውቀውናል።

@tikvahethiopia