TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Sudan

የጎረቤት ሀገር ሱዳን ጦርነት #ሰላማዊ መፍትሄ እንዲገኝ ኢጋድ በኢትዮጵያ፣ አዲስ አበባ  የሰላም ስምምነት እንዲጀመር ለማድረግ እየሰራ መሆኑ ታውቋል።

በሱዳን ሚያዚያ ወር የጀመረው ጦርነት ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን በርካቶች ህይወታቸውን እያጡ ፣ ከቤታቸው እየተፈናቀሉ፣ ንብረትም እየወደመ፣ የሀገሪቱ ኢኮኖሚም እየወደቀ ይገኛል።

ተፋላሚዎቹ የሱዳን ጦር እና ፈጥኖ ደራሹ (RSF) ካርቱም ላይ ከሚያደርጉት ጦርነት ባሻገር ጦርነቱ የዳርፉር ክልልን ጨምሮ ወደ ሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች የተስፋፋ ሲሆን በምዕራብ ዳርፉር ውስጥም የጎሳ ግጭት መቀስቀሱ ታውቋል።

ትላንትም የሱዳን መንግሥት ጦር ሠራዊት በኦምዱርማን በፈጸመው የአየር ጥቃት ቢያንስ ህፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ 22 ሰዎች ሲገደሉ፣ በርካቶች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በሱዳን ያለውን አስከፊ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲያገኝ አሜሪካ እና ሱዑዲ አረቢያ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካም። ተፋላሚዎቹ የተኩስ አቁም ለማድረግ ይስማሙና በሰዓታት ውስጥ ግጭቱን እንደሚቀጥሉ ከዚህ ቀደም በተዳጋጋሚ ታይቷል።

አሁን ላይ ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) በሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች መካከል የሚደረግ የሰላም ስምምነት እዚህ አዲስ አበባ ላይ ሰኞ  ለመጀመር ጥረት እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል።

ነገር ግን የሱዳን ጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል አል ቡርሐን በሰላም ንግግሩ ላይ " አልመጣም " ማለታቸውን ቃል አቀባያቸው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
ዛሬ ከባድ የመኪና አደጋ በጌዴኦ ዞን ይርጋጨፌ ወረዳ " ወቴ ቀበሌ " መከሰቱ ተሰምቷል።

ዛሬ ሐምሌ 02 ቀን 2015 ዓ/ም ከያቤሎ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ የነበረው " ኮድ 3 70303 ኦሮ " የሆነ ባስ #ተገልብጦ እስከአሁን ድረስ የ8 ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን ቀላል እና ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው በርካታ ተሳፋሪዎች ወደ ዲላ ሆስፒታል ተወስደዋል።

መረጃውን ከጌዴኦ ዞን ነው ያገኘነው።

@tikvahethiopia
' 140.2 ቢለየን ብር '

አዲስ አበባ ከተማ የ2016 ዓ/ም በጀት 140.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ፀድቋል።

በጀቱ ትላንትና ዛሬ በተካሄደ የም/ቤቱ 2ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ እና የበጀት ዓመቱ ማጠቃለያ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው።

በዚህም በበጀት አመቱ ፦
👉 ለመደበኛ በጀት ወጪዎች ብር 23,498,446,197.00
👉 ለካፒታል ወጪዎች 69,336,835,072.00
👉 ለመጠባበቂያ በጀት 5,300,000,000.00

ለክፍለ ከተሞች:-
👉 መደበኛ በጀት ወጪዎች ብር 33,498,495,001.00
👉 ለካፒታል ወጪዎች 8,657,773,794.00 የመደበ ሲሆን፣
በጥቅሉ ለከተማ አስተዳደሩ የ140,291,550,064.00 ብር በጀት ለመደበኛ ፣ ካፒታልና መጠባበቂያ በጀት አፅድቋል፡፡

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ዛሬ ጥዋት ከያቤሎ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ በነበረው ባስ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ እስካሁን የሟቾች ቁጥር 9 መሆኑ ተሰምቷል።

በአደጋው 12 ከባድና 19 ቀላል ጉዳት መድረሱም ተሰምቷል።

ከባድ እና ቀላል ጉዳት የደረሰባቸዉ ወደ ዲላ ሪፈራል ሆስፒታል ተወስደዋል።

ከሟቾች ዉስጥ ሶስት ሴቶችና ሁለት ወንዶች የቦረና ዩኒቨርስቲ የሬሜዲያል መርሀግብር ተማሪዎች መሆናቸዉን የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ህብረት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

የተማሪዎች ህብረቱ ፤ በመኪናው ውስጥ ከነበሩት ተጓዦች መካከል ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲመለሱ የነበሩ ተማሪዎች እንደነበሩ ጠቁሟል።

ከፖሊስ በተገኘ መረጃ በመኪና ውስጥ 60 ተጓዦች ነበሩ።

ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እያጣራ እንደሚገኝ ታውቋል።

@tikvahethiopia
ለተወዳጇ ድምጻዊት እጅጋየሁ ሽባባው (#ጂጂ) ፣ ለጌትነት እንየው እና ለአበበ ብርሃኔ የዕውቅና ሽልማት ተበረከተ።

የዕውቅና ሽልማቱ የተበረከተው ዛሬ ለ15ኛ ጊዜ በተካሄደው የአማራ ክልል ባሕልና ኪነ ጥበባት ፌስቲቫል ላይ ነው።

#ጂጂ

እጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ) ለሀገር ባቀነቀነቻቸው ዘፈኖቿ ብዙዎችን ማስተሳሰሯ ተገልጿል።

የሀገር በቀል ሥራዎቿ በእጅጉ የሚወደዱላት ፣ #ኢትዮያዊነትን የምታስተጋባ ፣ በኢትዮጵያዊነት ፍቅር የተንቀለቀለች፣ ሀገርን ያስቀደመች፣ ሕዝብ የሚያስፈልገውን ሁሉ የምታቀነቅን ድንቅ የጥበብ ሰው ነች ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ የራሷን አሻራ ያሳረፈች፣ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ እያለች የተሰማች፣ ትንቢት የሚመስል ቃል አስቀድማ የተናገረች በሳል ድምጻዊት መኾኗም ተገልጿል።

#ጌትነት_እንየው

ጸሐፈ ተውኔት ፣ ገጣሚ ፣ ተዋናይ እና አዘጋጅ ጌትነት እንየው በጥበቡ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋፆ ማደረጉ ተገልጿል።

በሳንሱር ሳቢያ በርካታ ፈተናዎች ቢገጥሙትም ለጥበብ ራሱን በመስጠት አስተዋጽዖ እያደረገ የመጣ አሁንም እያደረገ ያለ መኾኑ ተመላክቷል፡፡

ሁለገቡ የጥበብ ሰው ጌትነት እንየው የቀደመውን እና የአሁኑን ትውልድ የሚያገናኝ ድልድይ ነውም ተብሏል፡፡

በበሳል ብዕሩ እየነቀሰ የሚያወጣቸው ማኅበራዊ ጉዳዮች ድንቆች መኾናቸውም ተመላክቷል፡፡

#አበበ_ብርሃኔ

የዜማና የግጥም ደራሲው አበበ ብርሃኔም ዘመኑን ሙሉ ለጥበብ አስተዋጽዖ ማድረጉ ተገልጿል።

ልብን በሚመስጡ ዜማዎቹ፣ ሰምና ወርቅን በተሞሉ ግጥሞቹ ለጥበብ ብዙ ዋጋ መክፈሉ ተነግሯል።

ከቀደሙት አርቲስቶች እስከ ዘመኑ ድምጻውያን ድረስ ያልተቋረጠው የዜማና የግጥም ድርሰቱ ለጥበብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ተብሏል።

ባልተቋረጠው ጥበቡ የኢትዮጵያን ሙዚቃ ከፍ አድርጓል፣ ከፍም እያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

ለሀገር ጥሩ በሙያው ቀዳሚ መኾኑን ተነግሯል፡፡

Via AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ቦዴፓ

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቦዴፓ) በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ልኮልናል።

ፓርቲው በላከልን መግለጫ እስካሁን ትጥቃቸውን ያልፈቱ የጉህዴን ታጣቂዎች በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ ግልገል በለስ ከተማ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ/ም በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ንፁኃን ዜጎች መገደላቸውና በርካቶች መቁሰላቸውን ገልጿል።

ድረጊቱ በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለለው አስነዋሪና አሳፋሪ መሆኑን በመግለፅ አውግዟል።

በንፁሀን ዜጎች  ላይ ይህን የመሰለ ወንጀል የፈጸሙ አካላት በአፋጣኝ ለህግ እንዲቀርቡ ፓርቲው አጥብቆ ጠይቋል።
 
ከዚህ በተጨማሪ እነዚህ የታጣቂ  ቡድን አባላት በመተከል እና ከማሽ ዞኖች  ትጥቅ ሳይፈቱ በከተሞችና በገጠር ቀበሌዎች በመንግስት ሎጀስትክስ  እየተንቀሳቀሱ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ስጋት እየፈጠሩ ይገኛሉ ሲል አሳውቋል።

ፓርቲው ወቅታዊ የሆነውን ክልላዊ ሁኔታን በማስመልከት ፦

- የመተከልን ህዝብ ማህበራዊ  እረፍት በመንሳት ቀጠናውን የጦረነት ማዕከል ለማድረግ የሚሰሩ አካላት ከድርጊታቸው እንድቆጠቡ ፤ አረሶ አደሩን ለማስራብ በማለም የእርሻና የምርት ወቅት በመጠበቅ የሚደረግ አመራር ፈጠር  ግድያ በእጅጉ እንደሚያወግዝ ገልጿል።

- ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ/ም ከጉህዴን ጋር የክልሉ መንግስት በደረሰው ስምምነት መሰረት የታጠቁ የጉህዴን ኃይሎች ተሃድሶ ስልጠና ከወሰዱ በኃላ ትጥቅ ፈተው ወደ ህብረተሰቡ ይቀላቀላሉ ቢባልም ትጥቅ ሳይፈቱ ማህበረሰቡ ውስጥ የሚያደረጉት እንቅስቃሴ በተለይም የመንግስት የፀጥታ አካላትን ሚና #ተክተው የሚያደረጉት እንቅስቀሴ በአስቸኳይ እንዲቆምና ትጥቅ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አሳስቧል።

- በመተከል ዞን ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ አጀንዳቸውን በኃይል ለማስፈጸም የሚታትሩ #የውስጥ እና #የውጭ ሃይሎች ከድረጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳስቧል።

- ሰሞኑን በግልገል በለስ ከተማ በዜጎች ላይ የተፈፀመውን ዘግናኝ ግድያና ከድርጊቱ ጀርባ ያሉ አካላትን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ የክልሉና  የፌደራል ፖሊስ በማጣራት አጥፊዎችን ለህግ እንዲያቀርቡና ለህዝቡ ይፋ እንዲያደረጉ ጠይቋል።

- የክልሉ መንግስት በሰላም ውስጥ ልማትን ማሰብና መፈፀም የማይችሉ፣ በግጭት ውስጥ በህዝብ ደም በስልጣን ላይ ለመኖር የሚፈልጉ ሀሳብና ውጤት አልባ ጊዜ ያለፈባቸው አመራሮችን በአስቸኴይ በማጥራት እንዲያስተካክል ፓርቲው አሳስቧል።

(ከቦዴፓ የተላከው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ይነበብ

ትምህርት ሚኒስቴር በሀገሪቱ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከነገ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ/ም ይጀምራል።

በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እና ከፈታኞች ምን እጠበቃል ?

[ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ]

- ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍላቸው ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

- ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው።

- ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

- ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

- ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

- ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

- በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገርም ሆነ ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

- ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

- ተፈታኞች በምንም አይነት ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

- ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች ለፈተናው ፈታኝ መምህራን እና ለአስተባባሪዎች መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

NB. ሁሉም ተፈታኞች ወደ ፈተና መፈተኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

[ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ]

- የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

- ፈታኝ መምራህን የተፈታኝ ተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

- በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

- የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

- በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከመተኛ ክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

- ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

- ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

- ሲኮርጅ ወይም ሲያስኮርጅ የተገኘ ማንኛውም ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ፈተናው ከጀመረ ከ15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

- የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ ይጠብቅባቸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ነው የሰበሰበው።

ለመላው ተፈታኞች መልካም ፈተና ይሆን ዘንድ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይመኛል !

@tikvahethiopia