TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ 13 አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ሐምሌ…
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ የትግራይ ህዝብን ይቅርታ ጠየቀ።

በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ፦

- ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠቷ፣

- በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው #ሕዝበ_ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣

- ጦርነቱ ቁሞ በአገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

@tikvahethiopia