TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle በዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑክ መቐለ ገባ። በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ዛሬ መቐለ ገብቷል። ልዑኩ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገር ይጠበቃል። ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ @tikvahethiopia
" ጉዳቱ የሚያሳምም ቢሆንም ተባብረን ወደነበረበት እንመልሰዋለን " - ዶ/ር ሊያ ታደሰ

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው ልዑክ በትግራይ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

በትግራይ ያሉ የጤና ተቋማት የሰረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም የሚያሳዝን እና ከፍተኛ ነው።

ዶ/ር ሊያ ፤ ጉዳቱ የሚያሳምም ቢሆንም ተባብረን ወደነበረበት እንመልሰዋለን። መመለስም ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ሊያ እና የመሩት ልዑክ በመቐለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታልም ጉብኝት ማድረጉና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መነጋገሩ ተሰምቷል።

ፎቶ ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia