TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ደጀን የደጀን ከተማ ኮሚኒኬሽን ላለፉት ቀናት ተዘግቶ የነበረው የደጀን መንገድ ዛሬ ጠዋት ከሁለት ሰዓት ገደማ ጀምሮ መከፈቱን አሳውቋል። መንገዱ መከፈቱን ተከትሎ ቆመው የነበሩ ተሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ጀምረዋል። የከተማው ኮሚዩኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ሞኙ ሆዴ አሳየ ለ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ድረገፅ በሰጡት ቃል መንገዱ የተከፈተው፤ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ዛሬ ጠዋት ወደ ከተማዋ መግባታቸውን…
ፖሊስ ስለ " ደጀን መንገድ " መከፈት ምን አለ ?

የደጀን ወረዳ ፖሊስ፤ ተዘግቶ የነበረው የአዲስ አበባ - ደጀን አገር አቋራጭ መንገድ ለትራፊክ ክፍት መሆኑን አሳውቋል።

የደጀን ፖሊስ ፤ " በደጀን ወረዳ እና በደጀን ከተማ በፀጥታ ችግር ምክንያት ተዘግቶ የነበረው የፌደራል መንገድ በመከላከያ ድጋፍ እና በሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ትብብር ከዛሬ 03/08/15 ዓ.ም ከረፋዱ 3:30 ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል " ብሏል።

የወረዳው ፖሊስ " በየትኛውም መንገድ ቢሆን የአገር አቋራጭ መንገድ በመዝጋት ለውጥ ማምጣት ይቻላል ወይ ? " ሲል የጠየቀ ሲሆን " እባካችሁ ህዝባችንን ወደ ድህነት እና ስቃይ ህይወት አንክተተው ! የሚመለከተው ሁሉ ለህግ መከበር የድርሻውን ይወጣ እንላለን ! " ሲል መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#EOMMarket

ህይወትዎን ቀላልና ዘመናዊ የሚያደርጉ ጥራት ያላቸው እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያገኙበት ትልቁ ገበያ 👇
https://publielectoral.lat/EOMMarket
- የመረጡትን እቃ ይዘዙን፤ያሉበት ድረስ በነፃ  እናደርሳለን
𝗣𝗵𝗼𝗻𝗲  ☞ 0929181818 / 0909868788

ይምጡ የሽያጭ ማእከሎቻችን ይጎብኙ፤ ተደስተው ይመለሳሉ !
አድራሻችን፦

ቁጥር 1:- መገናኛ, ቤተልሄም ፕላዛ  የሱቅ ቁጥር  G-10 ግራውንድ [ እንደገቡ በስተቀኝ በኩል ]
ቁጥር 2:- ሜክሲኮ, ኬኬር ህንፃ የሱቅ ቁጥር #338

𝕵𝖔𝖎𝖓 𝖔𝖚𝖗 𝖈𝖍𝖆𝖓𝖓𝖊𝖑  : @EOMmarket
     
#ExodusPhysiotherapy

በኤክሶደስ የፊዚዮቴራፒ ስፔሻሊቲ ክሊኒክ የምንሰጣቸው የህክምና አገልግሎቶች ፦ ለአንገት ፣ ለትክሻ ፣ ለወገብ ህመም ፣ ከዲስክ መንሸራተት ጋር በተያያዘ ለሚመጣ ችግር ፣ ለማዞር ወይንም ሚዛን የመጠበቅ ችግር ፣ ለፊት መጣመም፣ ከስትሮክ በኋላ ለሚመጣ ግማሽ የሰውነት ክፍል መዛል ፣ ለስፖርታዊ ጉዳቶች፣  ከህፃናት የእድገት ውስንነት ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ የእንቅስቃሴ ችግሮች ፣ በአጠቃላይ ከነርቭ ፣ ከጡንቻ ፣ ከመገጣጠሚያ ጋር በተገናኘ ለሚከሰቱ ችግሮች መፍትሄ ያግኙ ይዳኑ !

የስራ ሰዓት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ     #ከጠዋቱ 2:30 እስከ #ምሽት 1:00 ሰዓት

አድራሻችን ፦ 22 ከመክሊት ህንፃ ፊት ለፊት ባሮ ህንፃ ላይ እንገኛለን፤ ስልክ 0979099909/ 0911039377

በቴሌግራም ቻናላችን ጠቃሚ መረጃ ያግኙ
https://publielectoral.lat/ExodPhysioClinic
#ችሎት

ዶ/ር ሙሉቀን ሃፍቱን ጨምሮ 5 ገለሰቦች ነፃ ተባሉ።

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱን ጨምሮ፥ ከኮንዶሚኒዬም ዕጣ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ " ከባድ የሙስና ወንጀል " ክስ የተመሰረተባቸው 5 ግለሰቦች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነጻ ተብለዋል።

በዚሁ መዝገብ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንድ ተከሳሽ በሌሉበት ጥፋተኛ ሲባሉ፥ ቀሪ አምስት ተከሳሾች ደግሞ የተከሰሱበት ድንጋጌ ተቀይሮ እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ በይኗል።

ችሎቱ አምስት ተከሳሾችን በነጻ ያሰናበተው ፥ " ዐቃቤ ህግ ባቀረበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ፥ ወንጀሉን በበቂ ሁኔታ ባለማስረዳቱ "መሆኑን ገልጿል።

በነጻ ከተሰናበቱት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያና ስልጠና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ የነበሩት አቶ አብርሃም ሰርሞሎ እና የከተማይቱ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ቢሮ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬይትን ሲመሩ የነበሩት አቶ ኩምሳ ቶላ ይገኙበታል።

#ኢትዮጵያኢንሳይደር

@tikvahethiopia
#Update

ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአዲስ መልክ ፍቃድ ሊሰጥ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳውቋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በአዲስ መልክ ፍቃድ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

ባለሥልጣኑ ከህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ አዲስ ለሚከፈቱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃድ መስጠት ማቆሙ ይታወቃል።

ባለሥልጣኑ አዲስ ፈቃድ የሚያገኙ ተቋማት ማሟላት የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች የሚደነግጉ መመሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

የተሻሻሉት መመሪያዎቹ ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም ፈቃድ የነበራቸውን ጨምሮ ሁሉም የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሙሉ እንደ አዲስ ምዝገባ መፈጸም እንደሚጠበቅባቸውም አሳስበዋል።

ምዝገባው በዘንድሮ ዓመት የሚጠናቀቅ ሲሆን በ2016 ዓ.ም አዲስ ፍቃድና የእድሳት አገልግሎት መስጠት ሊጀመር እንደሚችል ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ 360 የሚጠጉ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚገኙ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን መረጃ ያሳያል። #ENA

MORE : @tikvahuniversity
#Amhara

ልዩ ኃይሉን ምን አስቆጣው ?

መንግሥት በአማራ ክልል የልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት እንቅስቃሴ ውስጥ ምን ስህተቶችን ፈፀመ ?


የአማራ ክልል ብልፅግና ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ ትላንት ምሽት በክልሉ ቴሌቪዥን ቃለምልልስ አድርገዋል።

በዚሁ ቃለምልልስ ወቅት በአማራ ክልል ከልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተፈፀመዋል ስላሉት ስህተቶች አብራርተዋል።

በተጨማሪ በክልሉ ህዝብ ዘንድ ስለሚነሱት ስጋቶች፣ጥያቄዎች ቅሬታዎች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ግርማ የሺጥላ አተገባበሩንና የተፈፀሙ ስህተቶችን፣ እና ያጋጠሙ ችግሮችን በተመለከተ ምን አሉ ?

" ...በተገባበር በኩል በአማራ ክልል ሁኔታ ለየት ያሉ ችግሮች ገጥመዋል። ውሳኔው ሀገራዊ ውሳኔ ነው፤የሁሉንም ይሁንታ ያገኘ ነው። ይልቁንም በውሳኔ ደረጃ ከተመለከት ነው ይህ ጉዳይ መፍጠን ነበረበት ተብሎ የሚወሰድ ነው።

አሁንም ቢሆን አልመሸም ነበርና ከተወሰነ በኃላ አፈፃፀሙ ዝርዝር እቅድ ወጥቶለት እንዲከናወን ሲደረግ በአማራ ክልል የገጠመ ችግር አለ።

የገጠመው ችግር አንደኛው እና ዋነኛው ስራውን እንዲካከናውን የተደጋጀው ኃይል የተከተለው መንገድ ብዙ እቅዱን የተመረኮዙ ስራዎች ቢሆንም የተፈፀሙ ስህተቶች አሉ።

የመጀመሪያው የተፈፀመው ስህተት የቅድመ እውነቶች፤ፖለቲካ ስራዎች ቀድመውናል። አንደኛው ልዩ ኃይሉን መልሰን እናደራጃለን የሚል እቅድ ይዘን ለመንቀሳቀስ ስራ ስንሰራ 'ልዩ ኃይሉን ለማፍረስ መንግሥት ወሰነ' የሚል የፖለቲካ ስራ በስፋት ተሰራጨ።

2ኛው ልዩ ኃይሉ እየተጠቀማቸው ያሉ የጦር መሳሪያዎች እና ተተኳሾች እንዲሁም ልዩ ልዩ ግብአቶችን በተመለከተ በእቅዱ ላይ የተመላከተው በዋነኛነት ክልሉን ለማጠናከር፣ ይሄን ኃይል ይዞ ለማጠናከር እንደሚውሉና ተነግሮት አውቆ አምኖበት በወታደራዊ ዲሲፕሊን ለየሚፈለግበት ስራ እንደሚያውል ተደርጎ የተቀመጠውን ትጥቅ ' ሊፈታ ነው ' እና የአማራን ክብር እና ሞገስ የሚያዛባ አይነት ስራ እንደሚሰራ ተደርጎ ተገለፀ።

3ኛው ይሄ ኃይል ሪፎርም ሲደረግ በዋነኛነት የክልሎችን የፀጥታ ተቋም እንደሚያጠናክር ሳይሆን ወደ መከላከያ ግባ እንደተባለና የመከላከያ ኃይል በጉልበት እንደሚያደርገው ተደርጎ ተቀነቀነ።

በዚህ ምክንያት የአማራ ክልል የስራው ባለቤቶች ስራው ወደ ክልል መጥቶ ሲጀመር ስርዓት ባለው መንገድ በአግባቡ ውይይት፣ ንግግር ሲደረግ በመሃል ከስራ አስፈፃሚዎች መካከል 'ትጥቅ እንዲያወርድ' የሚል ደብዳቤ የመንግስት መሪዎች፣ የፖለቲካ መሪዎች ባላወቅነው መንገድ ሾልኮ ይልቁንም ሰራዊቱ ሳያውቀው በማህበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር ተመለከትን።

በዚህ በእጅጉ አዝነናል፤ አንደኛ የሰራዊቱንም የህዝቡንም ክብር ይነካል። ሁለተኛ ለቆምንለት አላማና ለምንሰራው ስራ በፍፁም የሚመጥን ደብዳቤ አይደለም።

ያለው የፖለቲካ ሴራ እንዲህ አይነት ነዳጅ ሲያገኝ የበለጠ ተጋጋለ በመጋጋሉ ምክንያት ልዩ ኃይሉ ሊወያይ ካለበት ቀን በፊት ለምንድነው የተበደልኩት? ለምንድነው ላደረኩት አስተዋፅኦ እንዲህ አይነት ደብዳቤ ሳይነገረኝ ሳልወያይ የከፈልኩት መስእዋትነት ደሙ ሳይደርቅ እንዲህ አይነት በደል ለምን ይሰርስብኛል ብሎ ተቆጣ፤ መቆጣቱ ትክክል ነው።

የእሱ (የልዩ ኃይሉ) አመራሮች ግን ተወያይተዋል። እኔ እራሴ ባለሁበት፣ ክቡር ምክትል ፕሬዜዳንቱ ባሉበት፣ የሀገሪቱ ምክትል ኢታማዦር ሹም ባሉበትና ሌሎች አካላት ባሉበት የሁሉም የአማራ ክልል የ21ዱ ዞንና ከተማ አስተዳደሮች የመንግሥት እና ፖለቲካ አመራሮች፣ የፀጥታ ' ሚኒ ካቢኔ ' በተለምዶ ይሄ አካል በተሳተፈበት ውይይት ተካሂዷል። "

(ሙሉ ቃለምልልሱ ከላይ ተያይዟል)

Video:AMC (196 MB)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle በዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑክ መቐለ ገባ። በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ዛሬ መቐለ ገብቷል። ልዑኩ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገር ይጠበቃል። ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ @tikvahethiopia
" ጉዳቱ የሚያሳምም ቢሆንም ተባብረን ወደነበረበት እንመልሰዋለን " - ዶ/ር ሊያ ታደሰ

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው ልዑክ በትግራይ ጉዳት የደረሰባቸውን የጤና ተቋማት ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

በትግራይ ያሉ የጤና ተቋማት የሰረሰባቸው ጉዳት እጅግ በጣም የሚያሳዝን እና ከፍተኛ ነው።

ዶ/ር ሊያ ፤ ጉዳቱ የሚያሳምም ቢሆንም ተባብረን ወደነበረበት እንመልሰዋለን። መመለስም ይችላል ሲሉ ተናግረዋል።

ዶ/ር ሊያ እና የመሩት ልዑክ በመቐለ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታልም ጉብኝት ማድረጉና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መነጋገሩ ተሰምቷል።

ፎቶ ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለግብይትዎ የብርሃን ኤቲኤም ካርድን በመጠቀም ጊዜዎን ይቆጥቡ፤ ድካምዎን ያቅልሉ!

አዳዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች የሚገኙትን ሊንኮች በመጫን የማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችንን ይቀላቀሉ !

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://publielectoral.lat/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
Twitter: https://twitter.com/berhanbanksc
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/76151001
YouTube: https://www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
#Oromia

" የልዩ ኃይል ስምሪት አቁመናል ፤ ... በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራ የአገር መከላከያ ሠራዊት ተረክቧል " - የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የልዩ ኃይል አደረጃጀት ስምሪት ማቆሙን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ከዶይቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለመጠይቅ ነው ይህንን ያሳውቁት።

ዋና ኮሚሽነሩ ለሬድዮ ጣቢያው በሰጡት ቃል ፤  የፌዴራሉ መንግሥት ባስተላለፈው መሠረት የልዩ ኃይል አደረጃጀት መዋቅርን በተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች መልሶ የማደራጀቱ ተግባር እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በክልሉ ያለውን የፀጥታ ማስከበር ሥራንም #የአገር_መከላከያ_ሠራዊት መረከቡን ገልጸዋል።

" የልዩ ኃይል አደረጃጀት ቀድሞውኑም ለጊዜያዊ የፀጥታ ችግር ያለ ሕገ መንግስታዊ መርህ ነው " የተመሰረተው የሚሉት ጄኔራል አራርሳ መርዳሳ ለሁሉም ክልሎች በወጥነት ተላልፏል ያሉትን መዋቅሩን በሌላ ፀጥታ ተቋማት የማደራጀቱ ሥራ እየተተገበረ ነው ብለዋል።

" ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት የሚፈርስ የሚለው መልሶ ለመገንባት በሚል መወሰድ አለበት። እንደ ወንጀለኛ ፈርሶ የሚሳደድ አካል የለም። አደረጃጀቱ ስህተት ስለነበረበት በዚህ መደራጀት አለበት የሚል ነው መወሰድ ያለበት። አንድ ሕጋዊ ክፍተት መኖሩ ሲሆን ሌላው የሚገዳደር የተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች በአንድ አገር ውስጥ አያስፈልግም በሚል የፀጥታ ችግሮች በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልሎች መደበኛ ፖሊስ በየደረጃው እንዲሠራ በሁሉም ውይይት ተደርጎበት የተወሰነው። " ሲሉ ተናግረዋል።

ውሳኔው ሁሉንም ክልሎች የሚመለከት እንደሆነ የገለፁት ኮሚሽነር አራርሳ በተደረገው ውይይትና በተደረሰበት ስምምነትም አተገባበሩም በአንድ ላይ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ሂደቱን የአገር መከላከያ እንደሚያስፈጽም መወሰኑንም አመልክተዋል።

" የፌዴራል መንግሥት ውሳኔውን ያስተላለፈው ሁሉም ክልሎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ ነው። ከዚያ ውስጥ ኦሮሚያ አንዱ እንደመሆኑ መመሪያውን ተቀብለን በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እያደራጀን ነው። ኦሮሚያ አላፈረሰም ለአንዳንድ ክልል ብቻ የተላለፈ ነው ሚለው እውነት አይደለም ብቻ ሳይሆን በሬ ወለደ እንደ ማለት ነው። ይሄ የሚደበቅም ስላልሆነ ምንም የተለየ ማብራሪያ አያሻውም። ንጹሑ ህዝብ ግን እንዳይደናገር ውሳኔው ማንንም የሚመለከት መሆኑን ቢገነዘሙ መልካም ነው። " ብለዋል።

አሁን በክልሉ የሚሰማራ የልዩ ኃይል አደረጃጀት የለም ያሉት ኮሚሽነር አራርሳ በመከላከያ፣ በፌዴራል ፖሊስ እና በክልል መደበኛ ፖሊስ እንደየሚያስፈልገው መስፈርት እየተደራጁ ለስልጠና እየተሰማሩመሆኑንም ተናግረዋል።

" በሁሉም የፀጥታ መዋቅሮች አልደራጅም ያለ አሊያም በጡረታ መገለልም ያለበት በደንቡ መሰረት የመሸኘቱ ሥራ እየተተገበረ " ነው ብለዋል።

#ዶቼቨለ_ሬድዮ

@tikvahethiopia