TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ እና ነገ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማእከላት / ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ። ይህ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጥብቅ በሆነ ህግ መሰጠት ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ ፈተናቸውን ጨርሰው የወጡት " የማህበራዊ ሳይንስ " ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የተመለከቱትን እና በቀጣዩ " የተፈጥሮ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ሊስተካከለ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር…
#NationalExam

የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል።

ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል።

ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር  ሴት ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ በቀን ሆነ በማታ ምንም አይነት ትንኮሳ እንዳይደርስ እና ፈተናውን ተረጋግተው እንዳይወስዱ የሚያደርጉ ጫናዎች እንዳይፈጠሩ እንዲሁም ምቾታቸውን ሆነ ደህንነታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ እንዳይኖር ጥብቅ ቁጥጥር ማደረግ ይኖርበታል።

የፀጥታ ኃይሎች የግቢ መውጫ እና መግቢያ ላይ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ዙርያ ገባው ላይ ቁጥጥራቸውን ማጠንከር እንዳለባቸው የከዚህ ቀደም ተፈታኝ ተማሪዎች ጠቁመዋል። (በአጥር የተከለከሉ ነገሮች እንዳይገቡ)

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ የ2014  የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ሁሉንም የፈተና ህጎችን በማክበር በመረጋጋት፣ በከፍተኛ የራስ መተማመን እንዲሁም በብሩህ ተስፋ ፈተናችሁን እንድትወስዱ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ደግሞ እነዚህ ታዳጊዎች አሁን ለተተገበረው የፈተና ስርዓት/ለዩኒቨርሲቲም  አዲስ በመሆናቸው ማበረታታ እና መደገፍ እንጂ ባልተረጋገጠ መረጃ እንዲረበሹ፣ ተስፋ እንዲቆርጡ፣ በራሳቸውን እንዳይተማመኑ ማድረግ የለባችሁምና ስለምታጋሩት መልዕክት ጥንቃቄ አድርጉ እንላለን።

ተማፅኖ፦ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ ፈተና ማዕከል በማጓጓዝ ላይ አሽከርካሪዎች በእርጋታ እና በጥንቃቄ ማሸከርከር እንዳትዘነጉ እንማፀናለን።

መልካም ፈተና!
Tikvah Family!

@tikvahethiopia