TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UN

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሃፊና የአስቸኳይ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ በሽሬ ያሉ ሲቪሎች እና የሰብዓዊ እርዳታ ሰራተኞች ደህንነት ያሳስበኛል ብለዋል።

ግሪፊትስ ፤ በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ እየተባባሰ መምጣቱን ገልፀው ፤ " ትላንት ሁለት የፊት መስመር ሰራተኞች መቁሰላቸውን ሰምቼ ደንግጫለሁ " ብለዋል።

" ጦርነቱ እነሱ ወዳሉበት እየቀረበ መሆኑን ተከትሎ ያደረባቸውን ጭንቀት እጋራለሁ " ያሉት ግሪፊትስ ፤ " ሁሉም ወገኖች ወደ ውይይት እንዲመጡ እስከዚያው ድረስ ግን ሲቪሎችን እና የረድኤት ሰራተኞችን እንዲጠብቁ በድጋሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#USA

አሜሪካ ትላንት ምሽት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አንቶኒ ብሊንከን አማካኝነት በሰሜን ኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው ጦርነት ዙሪያ መግለጫ አውጥታለች።

በዚህ መግለጫ ምንድነው ያለችው ?

- በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል " በሽሬ ዙሪያ " ግጭት እየጨመረ መምጣቱ፣  የሰው ህይወት እያለፈ መሆኑ፣ ሰላማዊ ሰዎችን ያለየ ጥቃት እና ውድመት መከሰቱ  በጣም ያሳስበናል ብላለች።

- " የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት በጋራ የሚያካሂዱትን ወታደራዊ ጥቃት በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና ኤርትራ ደግሞ ጦሯን ከሰሜን ኢትዮጵያ እንድታወጣ እንጠይቃለን " ብላለች።

- የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ከፀብ አጫሪነት ተግባራቸው እንዲታቀቡ አሳስባለች።

- ባለፈው ዓመት ነሃሴ ወር ላይ የትግራይ ክልል ኃይሎች በአማራ ክልል " ቆቦ " አቅራቢያ ያካሄዱት ዘመቻ ዳግም ግጭት እንዲቀሰቀስ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ይህም ለተጨማሪ የሰብአዊ መብት ረገጣ እና ግፎች ተጋላጭነት ከፍ እንዳደረገ ገልጻለች።

- ሁሉም የታጠቁ ኃይሎች ሲቪሎችን እንዲጠብቁ ፤ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ያለ ምንም እንቅፋት ሰብአዊ ድጋፍ እንዲደርስ እንዲያደርጉ ጠይቃለች።

- የኢትዮጵያ መንግስት እና የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በአስቸኳይ ግጭት እንዲያቆሙ እና በአፍሪካ ህብረት መሪነት ለሚካሄደው የሰላም ድርድር ላይ በቁም ነገር እንዲሳተፉ ደግመን ጥሪ እናቀርባለን ብላለች።

- አሜሪካ በተቻለ ፍጥነት የሰላም ንግግሮችን ለማደራጀት እና ለማሸማገል ከአፍሪካ ህብረት፣ ከኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ መንግስታት እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ አጋሮች ጋር ሙሉ በሙሉ እሰራለሁ ብላለች።

@tikvahethiopia
#TanaForum

ዛሬ በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር የጣና ፎረም መካሄድ ጀምሯል።

10ኛው የ " ጣና ፎረም " ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም ፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን እስከ ጥምቅት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።

በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው የጣና ፎረም ጉባኤ ላይ ፦

- የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ፣

- የሶማሊያ ጠ/ሚ ሀምዛ አብዲ ባሬ ፣

- የሱዳን የሉዓላዊ ም/ቤት ሊቀመንበር ፤ ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን እና ሌሎችም እየተካፈሉ ይገኛሉ።

ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ ፤ የጣና ፎረም አፍሪካውያን መሪዎችን እና ባለ ድርሻ አካላትን በአሕጉራዊ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ በማወያየት ዘላቂ መፍትሔዎችን ለመቀየስ አልሞ ሚካሄድ ውይይት መሆኑን ገልፀው 10ኛው የጣና ፎረም ፤ " በአፍሪካውያን ለአፍሪካውያን የሚጠቅሙ መፍትሔዎች የሚወጡበት ውጤታማ የውይይት ጊዜ እንደሚሆንልን እምነቴ ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን የሽግግር መንግስት ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ከሆኑት ሌተናል ጀነራል አል ቡርሃን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል ፤ ከዚህ በተጨማሪ ዓባይ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ያለውን ግዙፍ የድልድይ ግንባታ ስራ ጎብኝተዋል።

ፎቶ ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ እና ነገ የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማእከላት / ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ። ይህ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ጥብቅ በሆነ ህግ መሰጠት ከመጀመሩ ጋር በተያያዘ ፈተናቸውን ጨርሰው የወጡት " የማህበራዊ ሳይንስ " ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የተመለከቱትን እና በቀጣዩ " የተፈጥሮ ሳይንስ " ፈተና ወቅት ሊስተካከለ ይገባል ያሏቸውን ጉዳዮች በዝርዝር…
#NationalExam

የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል።

ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል።

ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር  ሴት ተፈታኝ ተማሪዎች ላይ በቀን ሆነ በማታ ምንም አይነት ትንኮሳ እንዳይደርስ እና ፈተናውን ተረጋግተው እንዳይወስዱ የሚያደርጉ ጫናዎች እንዳይፈጠሩ እንዲሁም ምቾታቸውን ሆነ ደህንነታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል እንቅስቃሴ እንዳይኖር ጥብቅ ቁጥጥር ማደረግ ይኖርበታል።

የፀጥታ ኃይሎች የግቢ መውጫ እና መግቢያ ላይ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ዙርያ ገባው ላይ ቁጥጥራቸውን ማጠንከር እንዳለባቸው የከዚህ ቀደም ተፈታኝ ተማሪዎች ጠቁመዋል። (በአጥር የተከለከሉ ነገሮች እንዳይገቡ)

ውድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የሆናችሁ የ2014  የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ሁሉንም የፈተና ህጎችን በማክበር በመረጋጋት፣ በከፍተኛ የራስ መተማመን እንዲሁም በብሩህ ተስፋ ፈተናችሁን እንድትወስዱ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ደግሞ እነዚህ ታዳጊዎች አሁን ለተተገበረው የፈተና ስርዓት/ለዩኒቨርሲቲም  አዲስ በመሆናቸው ማበረታታ እና መደገፍ እንጂ ባልተረጋገጠ መረጃ እንዲረበሹ፣ ተስፋ እንዲቆርጡ፣ በራሳቸውን እንዳይተማመኑ ማድረግ የለባችሁምና ስለምታጋሩት መልዕክት ጥንቃቄ አድርጉ እንላለን።

ተማፅኖ፦ ተፈታኝ ተማሪዎችን ወደ ፈተና ማዕከል በማጓጓዝ ላይ አሽከርካሪዎች በእርጋታ እና በጥንቃቄ ማሸከርከር እንዳትዘነጉ እንማፀናለን።

መልካም ፈተና!
Tikvah Family!

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል። ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል። ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ። ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር  ሴት ተፈታኝ…
#ማስታወሻ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ " የፈተና ስርቆት እና ኩረጃ ከፍተኛ የደንብ ጥሰትና #ወንጀል " መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን እንዲህ ያለው ድርጊት በህግ እንደሚያስጠይቅ ያስገነዝባል።

የማህበረሰብ የጋራ ሀብት በሆነው ፈተና ላይ ሚፈጸም ማንኛውንም አይነት ወንጀል በጋራ መከላከል ይገባል ይላል አገልግሎቱ።

የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የብሔራዊ ፈተና ከማክሰኞ ጥቅምት 8 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ እስከ አርብ ጥቅምት 11 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TanaForum ዛሬ በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር የጣና ፎረም መካሄድ ጀምሯል። 10ኛው የ " ጣና ፎረም " ጉባኤ በአፍሪካ የሰላም ፣ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ዙሪያ የሚመክር ሲሆን እስከ ጥምቅት 6 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይቆያል። በባህር ዳር እየተካሄደ ባለው የጣና ፎረም ጉባኤ ላይ ፦ - የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ምክትል ጠ/ሚ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን…
#TanaForum

በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የነበረው 10ኛው ጣና ፎረም ዛሬ ተጠናቋል።

ፎረሙ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም የተዘጋጀ ሲሆን ለ3 ቀናት ሲካሄድ ነበር።

በዛሬ መርሃ ግብር " የአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ስነ ምህዳር እና ምላሾች" በሚል ርዕስ ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዶ ነበር በውይይት አፍሪካዊያን ምሁራን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር አቴ ዌበር፣ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሀመር፣ የተመድ የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር ሀና ቴተህ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ተገኝተው ነበር።

በወቅቱም ኬኒያዊው የህግና ፖለቲካ ተንታኙ ፕ/ር ፓትሪክ ሉሙምባን ጨምሮ ሌሎች አፍሪካዊያን ምሁራን ለሐመር ጥያቄ አቅርበዋል።

ምሁራኑ ለአምባሳደር ሐመር ካቀረቧቸው ጥያቄዎች መካከል አንዱ አፍሪካ የራሷን ችግር በራሷ እንድትፈታ ለምን አትተዋትም? የሚል ሲሆን አሜሪካ በአፍሪካ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እየገባች ነው፤ ቻይና ለአፍሪካ ከአሜሪካ በተሻለ መንገድ እየሰራች ነው የሚሉና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተዋል።

አምባሳደር ማይክ ሐመር ፦

" አፍሪካ በራሷ ችግሯን መፍታት ትችላለች ?  እንደዛ ማድረግ የምትችል አይመስለኝም።

እኔ ባህርዳር የተገኘሁት ምን ማድረግ እንዳለባችሁ ለመንገር አይደለም። አፍሪካም ሆነች አሜሪካ ችግራቸውን ለመፍታት በጋራ መስራት ግን አለባቸው።

በአፍሪካ እንደ አሜሪካ ብዙ ገንዘብ ኢንቨስት ያደረገ ሀገር ወይም ተቋም የለም፣ የአፍሪካዊያንን ህይወት በመታደግ ከአሜሪካ በላይ የሰራ ሀገር የለም፣ ፍጹም ላንሆን እንችላለን።

አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለባትን ሀላፊነት ታውቃለች ነገር ግን በብዙ መንገድ ለአፍሪካ ድጋፍ እያደረግን እንገኛለን። " ሲሉ መልሰዋል።

#አልዓይን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#TanaForum በባሕር ዳር ከተማ ሲካሄድ የነበረው 10ኛው ጣና ፎረም ዛሬ ተጠናቋል። ፎረሙ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም የተዘጋጀ ሲሆን ለ3 ቀናት ሲካሄድ ነበር። በዛሬ መርሃ ግብር " የአፍሪካ የሰላምና ደህንነት ስነ ምህዳር እና ምላሾች" በሚል ርዕስ ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሂዶ ነበር በውይይት አፍሪካዊያን ምሁራን ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ አምባሳደር አቴ…
#TanaForum

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በጣና ፎረም የተናገሩት ፦

" ያለፈው ታሪካችን ሊያስተምረን ይገባል፤ ስለችግሮቻችን ማንንም አንወቅስም መውቀስ ካለብን ራሳችንን ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ በአክሱም ዘመን የነበረንን ስልጣኔ ተመልከቱ፤ በግብጽ የነበረንን የቀደመ ስልጣኔ አስቡ፤ ችግራችን የነበረንን ጥንታዊ ስልጣኔ እና ታሪክ በተገቢው መንገድ ለልጆቻችን አለማስተማራችን ነበር። አሁን ግን ለልጆቻችን ከማስተማራችን በፊት ስለራሳችን የተሳሳተውን እይታችን ማረም ይገባናል።

አዎ ! ላለፉት 40 እና 50 ዓመታት #አሜሪካ ለሀገሬ ኢትዮጵያ በመቶ ሚሊየኖች የሚቆጠር ዶላር አውጥታ ምግብ እረድታ ይሆናል፤ ነገር ግን አሜሪካ የረዳችን ከችግራችን በምንወጣበት መንገድ አልነበረም።

ግብርናችን እንዲሻሻል፣ ቴክኖሎጂ እንድንጠቀም እና የተሻሻለ አሰራርን እንድንተገብር ተደጋጋሚ ድጋፍ የጠየቅናት አሜሪካ በፖሊሲ ሰበብ ፈቃደኛ አልነበረችም።

ኢትዮጵያዊቷ ንግስት ሳባ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ተሻግራ እንደ ሀገር ንጉስ ሰለሞንን ስትጎበኝ አሜሪካ እንደ አህጉርም እንደ ሀገርም አትታወቅም ነበር።

ከኋላ እየመጡ ለሚቀድሙን ሁሉ እርግጥ ነው ኅላፊነቱን መውሰድ ያለብን ራሳችን ነን።

የጣና ፎረም መንፈስም ችግርን በግልፅ ተናግሮ በጋራ እና በትብብር መፍትሔ መፈለግ ነው። "

Credit : AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NationalExam የ12ኛ ክፍል " የተፈጥሮ ሳይንስ " ተማሪዎች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባት ጀምረዋል። ተማሪዎች ነገ ተጠቃለው የሚገቡ ሲሆን ጥቅምት 07/2015 ዓ.ም ገለጻ (ኦሬንቴሽን) ይሰጣቸዋል። ከጥቅምት 08 እስከ 11 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ። ከዚሁ ከሁለተኛ ዙር ፈተና ጋር በተያያዘ የባለፉት ክፍተቶች መታረም ያለባቸው ሲሆን፤ ትምህርት ሚኒስቴር  ሴት ተፈታኝ…
#Update

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ማዕከላት መግባታቸውን ማምሻውን አሳውቋል።

አገልግሎቱ ተማሪዎቹ ነገ በ7/02/ 2015 ገለጻ እንደሚደረግላቸው እና 08-11/02/2015 ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልጿል።

" በራስ ጥረት፣ በብርቱ ድካምና በፈጣሪ እርዳታ የሚገኝ ውጤት መጨረሻው ያማረ ነው። " ያለው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት " የፈተና ስርቆትንና ኩረጃን በጋራ እንከላከል " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia