#ETHIOPIA

በኤሌክትሪክ ሞተር ከሚሰሩት #በስተቀር የተገጣጠሙ የቤት አውቶሞቢሎች፣ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪዎች እና የተገጣጠሙ ሞተር ሳይክሎችን ጨምሮ " ቅድሚያ የማይሰጣቸው " ተብለው የተለዩ 38 ዓይነት ምርቶች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ እግድ ተጥሏል።

እግዱ መጣሉን ያሳወቀው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነው።

ይኸው እግድ የተላለፈው የህገወጥ የምንዛሬ ገበያውን ይበልጥ ለማውረድ በማሰብ መሆኑ ተገልጿል።

የእግዱ መተግበር በአማካኝ ግማሽ ያህል የውጭ ምንዛሬን ሊያስቀር ይችላል ተብሏል።

#ከሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው እገዳ የሚቆየው ላልተወሰነ ጊዜ  ሲሆን እገዳ የተጣለባቸውን ምርቶች ለማስገባት የውጭ ምንዛሬ መጠየቅ እንደማይቻል የብሄራዊ ባንክ አሳውቋል።

ወደ አገር እንዳይገቡ አገዳ የተጣለባቸው ምርቶች ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia