TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት በአዲስ አበባ ከተማ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ። ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ፦ - የቴክኒክ ሙያ ስልጠና አይሲቲ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሐም ሰርሞሌ - የቤቶች ልማት ዳታ ቤዝ ቡድን መሪ አቶ ስመኘው አባተ - የሶፍትዌር ባለሙያዎች ፦ • ሀብታሙ…
#ችሎት #Update

ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ጋር በተያያዘ ከሁለት ሳምንት በፊት በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ላይ በድጋሚ ለፖሊስ 14 የምርመራ ቀናት ተሰጠ።

ለፖሊስ የምርመራ ጊዜውን የሰጠው ዛሬ አርብ ሐምሌ 22/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው።

የምርመራ ጊዜ የተፈቀደባቸው ተጠርጣሪዎቹ የአዲስ አበባ ከተማ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ እና የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ሰራተኞች የነበሩ ናቸው።

ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ የአዲስ አበባ የቴክኒክ ሙያ ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምከትል ኃላፊ አቶ አብርሃም ሰርሞሎ ይገኙበታል።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት በዛሬው ውሎው " ከፖሊስ የምርመራ መዝገብ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተገንዝበናል " ብሏል።

" የወንጀሉ ውስብስብነት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለመስጠት ምክንያታዊ ነው " ያለው የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ፤ በዚህም መሰረት 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ለመርማሪ ፖሊስ መፈቀዱን ማስታወቁን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

@tikvahethiopia