TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ3ኛ ቀን ውድድር ዛሬ ይካሄዳል። የሀገራችን ልጆች የሚካፈሉበት ውድድር የሚከተሉት ናቸው። 🏟️ በማራቶን የወንዶች ፍፃሜ ፦ 🇪🇹 ሌሊሳ ዴሲሳ 🇪🇹 ሙስነት ገረመው 🇪🇹 ሰይፉ ቱራ 🇪🇹 ታምራት ቶላ (ሰዓት - ቀን 10:15) 🏟️ 10 ሺህ ሜትር የወንዶች #ፍፃሜ 🇪🇹 በሪሁ አረጋዊ 🇪🇹 ሰለሞን ባረጋ 🇪🇹 ታደሰ ወርቁ (ሰዓት - ምሽት 5:00)…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

እጅግ ተጠባቂው የወንዶች 10 ሺ ሜትር የፍፃሜ ውድድር መካሄድ ጀምሯል።

🇪🇹 በሪሁ አረጋዊ
🇪🇹 ሰለሞን ባረጋ
🇪🇹 ታደሰ ወርቁ #ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ ሲሆን ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያ ታገኝበታለች ተብሎ ከሚታሰብበት ውድድር አንዱ ይኸው የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ነው።

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹❤️ !!

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 እጅግ ተጠባቂው የወንዶች 10 ሺ ሜትር የፍፃሜ ውድድር መካሄድ ጀምሯል። 🇪🇹 በሪሁ አረጋዊ 🇪🇹 ሰለሞን ባረጋ 🇪🇹 ታደሰ ወርቁ #ኢትዮጵያን ወክለው የሚወዳደሩ ሲሆን ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያ ታገኝበታለች ተብሎ ከሚታሰብበት ውድድር አንዱ ይኸው የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ነው። ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹❤️ !! @tikvahethiopia
#Update

በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ድል ሳይቀናን ቀርቷል።

ዩጋንዳ የወርቅ ሜዳሊያውን ወስዳለች።

የሀገራችን አትሌቶች በውድድሩ ከፍተኛ ትንቅንቅ ቢያደርጉም ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ መያዝ ሳንችሉ ቀርተዋል ።

ሰለሞን ባረጋ 5ኛ ፣ በሪሁ አረጋዊ 7ኛ ፣ ታደሰ ወርቁ 14ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

ውድድሩ እጅግ በጣም ከፍተኛ ፉክክር የታየበት ነበር።

@tikvahethiopia
#ZHAddis

እጆላይ ያለው ካሜራ ጊዜ በሄደ ቁጥር የሚሰጠው ጥቅም ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ዝቅ እንደሚል ያቃሉ ከማይፈለግ እቃጋ ሳይመደብ አሁኑኑ እኛ ዘንድ ይዘው ይምጡ እንዳይቆጩ አርገን በጥሩ ዋጋ እንገዞታለን።

ይደውሉልን : 091115 6257 ከታች ያለውንlink በመጫን የቴሌግራም አባል ይሁኑ https://publielectoral.lat/joinchat/AAAAAEUTeB3LSYVFukiuQw

ቦሌ ወሎሰፈር HMM ህንፃ 2ኛ ፍቅ205
TIKVAH-ETHIOPIA
#Sudan በጎረቤት ሀገር ሱዳን ፤ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር በሚቀርበው ብሉናይል ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት በትንሹ 31 ሰዎች ሲገደሉ 39 ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸው በርካቶችም ሰላም ፍለጋ መሸሻቸው ተሰምቷል። ግጭቱ የጎሳ ግጭት እንደሆነ ተገልጿል። በበርቲ እና ሃውሳ ጎሳዎች መካከል በተነሳ የመሬት ውዝግብ ምክንያት በሮሰሪስ ከተማ ውስጥ ከትናንት በስቲያ በተፈጠረው ግጭት ቢያንስ 31 ሰዎች ሲገደሉ፣…
#Update #SUDAN

ለኢትዮጵያ ድንበር በሚቀርበው የሱዳን ብሉናይል ግዛት ውስጥ በተቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ የጎሳ ግጭት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 70 መደረሱ ሪፖርት ተደርጓል።

በበርቲ እና ሃውሳ ጎሳዎች መካከል በተነሳው የመሬት ውዝግብ ምክንያት በተፈጠረው ግጭት ቢያንስ 70 ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ ሰዎች ቆስለዋል (አብዛኞቹ በጥይት እና በስለት የቆሰሉ ናቸው) በርካታ ሱቆች ተቃጥለዋል ፤ 150 ሰዎች ተፈናቅለዋል።

በሁለት ግለሰቦች መካከል የተነሳ አለመግባባት ሳቢያ አንድ ሰው (በግብርና ስራ የሚተዳደር) ከተገደለ በኃላ ግጭቱ ወደ ጎሳ ግጭት ተቀይሮ ነው የበርካቶችን ህይወት የቀጠፈው ተብሏል።

Photo Credit : Darfur Monitors

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #Ethiopia #Sudan " መረጃው ውሸት ነው " - ዶ/ር ለገሰ ቱሉ " በእግረኛ የሚመጡ ከሆነ የአካባቢው ታጣቂ በተጠንቀቅ ቆሟል " - አቶ አብራራው ተስፋ " ሱዳን ትሪቡን " የተባለው የሱዳን ሚዲያ የሱዳን ጦር ሰራዊት ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ኃይሎች ተወሰደብኝ ያለውን እርምጃ ለመበቀል የይገባኛል ጥያቄ በሚናሳበት የአልፋሽጋ አካባቢ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ስር የነበሩ " ካላ…
#Update

ከ1 ወር በፊት ተዘግቶ የነበረው የጋላባት ድንበር ተከፈተ።

ሱዳን ከ1 ወር በፊት ዘግታው የነበረውን እና ከኢትዮጵያ የሚያዋስናትን ቁልፍ የድንበር በረ ከፍታለች።

ሱዳን ድንበሩ የተከፈተው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ገንቢ የሆነ ውይይት ከተደረገ በኋላ ነው ብላለች።

ከአንድ ወር በፊት ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በሚያወስነኝ አካባቢ በተፈጸመ ጥቃት የጦር አባላቶቼ ተገድለውበኛል ስትል ክስ ማሰማቷ ይታወሳል።

ሱዳን በኢትዮጵያ ጦር ሠራዊት ተፈጽሟል ባለችው ጥቃት 6 ወታደሮቿ እና አንድ ሲቪል መገደሉን ገልጻ ነበር።

የኢትዮጵያ መንግሥት/የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሰዎች ህይወት መጥፋት ሀዘን እንደተሰማው ገልጾ ነገር ግን በሱዳን የተሰራጨው መረጃ ትክክል እንዳልነበር መግለፁ ይታወሳል።

በመጀመሪያ ደረጃ በቦታው በነበረው ግጭት የአገር መከላከያ ሠራዊት ተሳትፎ እንዳልነበረው የተገለፀ ሲሆን ጉዳቱ ያጋጠመው ደግሞ እራሳቸው የሱዳን ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሠው አልፈው ከገቡ በኋላ ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር በተደረገ ግጭት ነው።

አሁን የገላባት ድንበር በር እንዲከፈት የተወሰነው ድንበር ላይ ያጋጠመውን ችግር የሁለቱ አገራት መሪዎች ለመፍታት ከተስማሙ በኋላ መሆኑን ሱና የሱዳን ደኅንነት እና መከላከያ ምክር ቤት ቴክኒክ ኮሚቴን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

በድንበር አካባቢ የታጠቁ ኃይሎችን ለመቆጣጠር "በኢትዮጵያ በኩል የታየው በጎ ፍቃድ" የድንበር በሩ እንዲከፈት ምክንያት ከሆኑት መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሱዳኑ መሪ ሌ/ጄኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን ከሳምንታት በፊት ለኢጋድ ስብሰባ በኬንያ በተገኙበት ወቅት ስለሁለቱ ሀገራት እና ቀጠናዊ ጉዳዮች የጎንዮሽ ውይይት ማድረጋቸው አይዘነጋም። #ሱና #ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#ችሎት

በአዲስ አበባ ከተማ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ።

ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ፦
- የቴክኒክ ሙያ ስልጠና አይሲቲ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሐም ሰርሞሌ
- የቤቶች ልማት ዳታ ቤዝ ቡድን መሪ አቶ ስመኘው አባተ
- የሶፍትዌር ባለሙያዎች ፦
• ሀብታሙ ከበደ
• ዮሴፍ ሙላት
• ጌታቸው በሪሁን
• ቃሲም ከድር
- የቤቶች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ሚኪያስ ቶሌራ
- የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ICT ኃላፊ አቶ ኩምሳ ቶላ ላይ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤት ተፈቅዷል።

የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 11/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። 

ችሎቱ የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የፌደራል ፖሊስ እና የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 8/2014 ያደረጉትን ክርክር ከመረመረ በኋላ ነው።

የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ በዛሬ ውሎው የተጠርጣሪዎቹ በዋስትና መውጣት “ምርመራው የተፈለገውን ውጤት እንዳያስገኝ ሊያደርግ ስለሚችል” በሚል ጠበቆች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#እቪኤላስ_ፈርኒቸር

በዘመናዊ መንገድና ጥራት የቤትና የቢሮ እቃዎችን እንደፍላጎትዎ የሚያመርተዉ አቪኤላስ የቤትና ቢሮ እቃ ማምረቻ ባዳዲስ ዲዛይን ቤትና ቢሮዎን ያስዉባል።

ኪችን፣ ቁምሳጥ፣ ቲቪ ስታንድ፣ በሮች፣ ፓርቲሽኖችና የተለያዩ የእንጨት ስራዎች ሲፈልጉ ይደውሉልን።

ቴሌግራም ቻናል ጆይንና ሼር በማድረግ አዲስ ምርት ማዬት ይችላሉ 👉 https://publielectoral.lat/furnituremakers

ስልክ 0118220767 / 0911427052 /0985931325 /

እድራሻ : ቦሌ ቡልቡላ 93 ማዞሪያ
ቅዱስ ቡዙአየሁ ኮሜርሻል ሴንተር 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ 24
#SFP

የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዚያዊ የምዝገባ ፈቃድ ማግኘቱን አመልክቷል።

አስተባባሪ ኮሚቴው በላከው መግለጫ ክልሉ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ ፣በባህላዊና በፍትህ ዘርፎች ትክክለኛ መስመር አለመያዙን ተገንዝቢያለሁኝ ያለ ሲሆን በተለይ ምክንያታዊ ያልሆኑ የስራ አጥነት ቀውስ፣ ፍትህ እጦት፣ ሙስና፣ ጎሰኝነት፣ አድሎአዊ አሰራር፣ ጥሎ የማለፍ ፖለቲካ ስርዓታዊ (systemic) እየሆነ መጥቷል ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በክልሉ ውስጥ ህዝቡን አደራጅቶ የሚታገል ጠንካራ ተፎካካሪ ፖርቲ እንደሌለ መገንዘቡን ገልጾ ፦
- ሁሉን የህብረተሰብ ክፍል ያቀፈ ፣
- የሲዳማ እሴቶችን መርህ ያደረገ፣
- በዴሞክራሲያዊና የህዝብ ስልጣን ባለቤትነትን ተግባራዊ እንዲሆን የሚታገል፣
- በሀሳብ ብዙሃነትና በመነጋገር የሚያምን፣
- እውነተኛ የሆነ ህብረብሔራዊ ፌደራሊዝም የሚከተልና እውን ለማድረግ ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ሀገራዊ ፖርቲዎች ጋር የሚሰራ ክልላዊ የፖለቲካ ፖርቲ ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጊዜያዊ ፈቃድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አግኝቶ የማቋቋሙን ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በአሁኑ ጊዜ ኮሚቴው ሙሉ ፈቃድ ለማግኘት የሚያስፈልጉ ስራዎች እያጠናቀቀ እንደግሚገኝና የአባላት ምዝገባ እያካሄደ መሆኑን አመልክቷል።

በዚህ ሂደት ሚመዘግቡ ወጣቶችና አስተባባሪዎች ላይ የማስፈራሪያ ዘመቻ እየተካሄደ ነው ያለው ሲፌፓ ለድርጊቱን የክልሉን መንግስት አመራሮችን ወቅሷል፤ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#አቶ_ተወልደ_ገብረማርያም

አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የህይወት ዘመን ሽልማት ተበረከተላቸው።

የቀድሞ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ላሳዩት የላቀ አመራር ፍላይት ግሎባል የተሰኘ የእንግሊዝ ኩባንያ የህይወት ዘመን ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

ፍላይት ግሎባል " ኤርላይን ቢዝነስ " የተሰኘ ዓለምአቀፍ የአቪዬሽን መጽሔት አሳታሚ ኩባንያ ሲሆን እ.ኤ.አ 2002 ዓ.ም ጀምሮ " ኤርላይን ስትራቴጂ አዋርድ " በየአመቱ በማዘጋጀት ለአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦች እና ኩባንያዎች እውቅና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

አቶ ተወልደ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት እሑድ ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ለንደን በተዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም ላይ በመታደም ተቀብለዋል፡፡

አቶ ተወልደ እውቅናውን በማግኘታቸው ደስ እንደተሰኙ ገልፀው በአገልግሎት ዘመናቸው አብረው ለደከሙ ሁሉ ባልደረቦቻቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ፍላይት ግሎባል ባወጣው መግለጫ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የተሸለሙት የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ባገለገሉባቸው 11 አመታት ላሳዩት የረጅም ጊዜ መርሀ ግብር እቅድ ዝግጅት እና ቀውስን የመቆጣጠር ክህሎት እውቅና ለመስጠት እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በእርሳቸው አመራር አየርመንገዱ በአራት እጥፍ ማደጉን ፍላይት ግሎባል ጠቅሷል፡፡

የኢትዮጲያ አየርመንገድ የአውሮፕላን ብዛት ከ33 ወደ 130 ፤ የመንገደኞች ቁጥር ከ3 ሚሊዮን ወደ 12 ሚሊዮን እንዳደገ ኩባንያው ጠቁሟል፡፡

አቶ ተወልደ አየርመንገዱን ለ37 አመታት ካገለገሉ በኋላ ባለፈው የካቲት ወር ከጤና ጋር በተያያዘ ከሃላፊነታቸው መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡

መረጃው የኢትዮ ንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ነው።

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ4ኛ ቀን ውድድር ዛሬ ይካሄዳል። የሀገራችን ልጆች የሚካፈሉበት ውድድር የሚከተሉት ናቸው።

🏟️ በማራቶን የሴቶች ፍፃሜ ፦

🇪🇹 ጎይቶቶም ገ/ስላሴ
🇪🇹 አባበል የሻነህ
🇪🇹 አሸቴ በክሬ

(ሰዓት - ቀን 10:15)

🏟️ 3,000 ሜትር መሰናክል የወንዶች ፍፃሜ ፦

🇪🇹 ለሜቻ ግርማ
🇪🇹 ሀይለማርያም አማረ
🇪🇹 ጌትነት ዋለ

(ሰዓት - ለሊት 11:20)

🏟️ 1,500 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ

🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ሂሩት መሸሻ
🇪🇹 ፍሬወይኒ ሀይሉ

(ሰዓት - ለሊት 11:50)

ድል ለሀገራችን🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia