በእንሳሮ ወረዳ በ2.2 ቢሊዮን ዶላር ኢንዱስትሪ ሊገነባ ነው !

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እሳሮ ወረዳ ዲረሙ ቀበሌ ሰሊላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ2.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የብሄራዊ ሲሚንቶ አክሲዎን ማህበር ለሚ የግንባታ ቁሳቁስ ኢንዱስትሪ ሊገነባ መሆኑ ተሰማ።

ዛሬ ለዚህ ግዙፍ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ይጣላል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

አጭር መረጃ ስለ እንሳሮ ፦

- እንሳሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ካሉት 23 ወረዳዎች እና 4 ከተማ አስተዳደሮች መካከል አንደኛ ዋ ወረዳ ስትሆን ለሚ የወረዳዋ ዋና ከተማ ናት፡፡

- ከአዲስ አበባ 130 ከ.ሜ፣ ከባህር ዳር 513 ኪ.ሜ ከደብረ ብርሃን ደግሞ 83 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

- እንሳሮን ከምስራቅ የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ፣ ከሰሜን የሞረትና ጅሩ እንዲሁም የመርሃቤቴ ወረዳ፣ ከምዕራብ ኦሮሚያ ክልል ግራር ጃርሶ ወረዳ፣ ከደቡብ ኦሮሚያ ክልል ውጫሌ ወረዳ ያዋስናታል፡፡

- ወረዳዋ በ13 የገጠር ቀበሌዎችና በ1 የከተማ ቀበሌ አስተዳደር የተከፋፈለች ናት፡፡

- ከ75 ሺህ በላይ ህዝብ የሚኖርባት እንሳሮ 41 ሺህ 27 ሄክታር ያህል የቆዳ ስፍት አላት፡፡

- አየር ንብረቷ 46 በመቶ ቆላ፣ 33 በመቶ ወይና ደጋ እንዲሁም 21 በመቶ ደጋ የሚሸፍን ሲሆን ለኑሮ እጅግ ተስማሚ የሆነ አየር ያላት ናት፡፡

- የህዝቦቿ ዋነኛ መተዳደሪያ ግብርና ነው፡ ከአጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ 21,465 ሄክታር መሬት ያህሉ ለእርሻ የዋለ ነው፡፡

ምንጭ : እንሳሮ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia