TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጭር ቁጥራዊ መረጃ ፦

ከሐምሌ 1/2012 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30/ 2013 ዓ.ም ድረስ ባለው 6 ወር ጊዜ ምን ያህል የመንገድ የትራፊክ አደጋ እንደደረሰ የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት የወንጀል ትራፊክ መረጃ ትምበያ ዛሬ አስታውቋል።

በዚህም በሀገር ደረጃ ፦

- 20,672 የመንገድ የትራፊክ አደጋ ደርሷል።

- 1,849 ዜጎች ህይወታቸውን አጥተዋል።

- በ2,646 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

- 2,565 የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ ለቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል።

- 495 ሚሊየን 240 ሺህ 473 የሚገመት ንብረት በመንገድ ትራፊክ አደጋው ወድሟል።

* መረጃው ከትግራይ ክልል ውጪ ከሁሉም ክልሎች የተሰበሰበ መሆኑ ተጠቅሷል።

በ6 ወራት ውስጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው የትራፊክ አደጋ በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ፦

- 15 ሺህ 844 የትራፊክ አደጋ መድርሷል
- 192 ሰዎች በአደጋው ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል
- በ846 ሰዎች ላይ ከባድ፣ በ512 ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ዜጎቿን ከሳዐዲ አረቢያ ማስወጣቷን ቀጥላለች።

ኢትዮጵያ ሳዐዲ አረቢያ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎቿን በተከታታይ በማስወጣት ላይ መሆኗ ይታወቃል።

ዛሬ የካቲት 24/2013 ዓ.ም 338 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረብያ ሪያድ ከተማ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።

@tikvahethiopia
#AtoAgenewTeshager

የአማራ ክልል ፕሬዘዳንት የውስጥ እንዲሁም የውጭ ሀይሎች በአማራ ክልል መንግስትና የፀጥታ ሀይል ላይ የሚያሰራጩት የሀሰት መረጃ የክህደት ጥግ ነው ሲሉ ኮነኑ።

ፕሬዜዳንቱ ይህን ያሉት በማህበራዊ ሚዲያ ዛሬ ባሰራጩት መልዕክት ነው።

በመልዕክታቸው የውጭ እና የሀገር ውስጥ ኃይሎች ያሏቸውን አካላት በግልፅ አላስቀመጧቸውም።

አቶ አገኘው ፥ "ዛሬም እንደትናንቱ የሚደርስብንን ሁሉ ጫና ተቋቁመን ወደ ፊት እንዘልቃለን" ሲሉም ነው የፃፉት።

ፕሬዜዳንቱ የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ እና መላው የአማራ ክልል ህዝብ በህግ ማስከበር ዘመቻው አበርክቶው የጎላ ነው ሲሉም ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና ወረቀት እስከ አርብ ድረስ ተጓጉዞ ይጠናቀቃል።

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከየካቲት 29 ቀን 2013 ጀምሮ የሚሰጠዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወረቀት በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እስከ መጪዉ አርብ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ተጓጉዞ እንደሚጠናቀቅ አስታወቀ።

የፈተናዎች ኤጀንሲ ከኢትዮጲያ አየር መንገድ ጋር ባደረገዉ ስምምነት መሰረት ፈተናዎቹ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተጓጓዙ መሆናቸዉን የኤጀንሲዉ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዲላሞ ቱሬ ተናግረዋል፡፡

በጥብቅ ቁጥጥር በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በፌደራል ፖሊስ አጃቢነት በተቀመጠዉ አቅጣጫ እና የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተጓጓዘ ነዉ ብለዋል፡፡

አያይዘዉም ፈተናዎቹ ወደ ክልል ከተሞች ሲደርሱ የየክልሎቹ ፖሊስ እና ልዩ ሀይል ጥብቅ ቁጥጥር እና እጀባ አድርገዉ ወደ ዞኖች እንደሚያደርሱም ተናግረዋል፡፡

እስካሁን እየተደረገ ያለዉ የማጓጓዝ ሂደትም ሰላማዊ ነዉ ፤ ምንም አይነት ችግር አልገጠመም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የጸጥታ ስጋት አለባቸዉ የተባሉ ቦታዎች ላይም ከፍተኛ ቁጥጥር በማድረግ በመከላካያ ሰራዊት እና በፌደራል ፖሊስ ታጅቦ እንደሚጓጓዝ ገልጸዋል፡፡

በመላዉ ሀገሪቱ ፈተናዉ እስከ መጪዉ አርብ የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ/ም ተጓጉዞ እንደሚጠናቀቅ ዶክትር ዲላሞ ማረጋገጣቸውን አሃዱ ሬድዮ ጣቢያ 94.3 (Ahadu FM RADIO) ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Attention😷

በኮቪድ-19 የሚያዘው ሰው ቁጥር እየጨመረ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት 6,282 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1,161 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

በተመሳሳይ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ5 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ 364 አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን 161,974 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከነዚህ መካከል 2,391 ህይወታቸው አልፏል ፤ 136,443 ከበሽታው አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 398 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OromoFederalistCongress የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ባወጣው መግለጫ : የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ባወጣው መግለጫ መንግስት በኃይል ዘጋብኝ ያላቸው ጽህፈት ቤቶቹ ተከፍተውና የታሰሩ አባሎቹ እንዲፈቱ በድጋሚ ጠይቋል። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አስፈላጊ ከሆነ የምርጫ መርሐ ግብሩ ተሻሽሎ እና የፖለቲካ ምህዳሩ ለሁሉም ዜጎች ተመቻችቶ ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የተሳካ ብሔራዊ…
ኦፌኮ በምርጫ 2013 ላለመሳተፍ መወሰኑን አሳወቀ።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) በ6ኛ ብሄራዊ ምርጫ እንደማይወዳደር ውሳኔ ላይ መድረሱን አስታወቀ።

ቲክቫህ ይህን ከአቶ ጥሩነህ ገምታ (የኦፌኮ ፅ/ቤት ኃላፊ) ማረጋገጥ ችሏል።

አቶ ጥሩነህ የኦፌኮ በምርጫው አለመሳተፍ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውሳኔ ላይ መድረሱን ገልፀውልናል።

የእጩዎች ጊዜ ቢራዘም ለኦፌኮ ፋይዳ ቢስ ነው ያሉት አቶ ጥሩነህ ፥ የተዘጉ ፅ/ቤቶቻችን ሊከፈቱ ፣ እስር ቤት ውስጥ የታጎሩ አባላት ሊፈቱ ፣ በአጠቃላይ የፖለቲካ ምህዳሩ ሊሰፋ ይገባል ብለዋል።

አቶ ጥሩነህ በፓርቲው ምርጫ 2013 እንዲያስተባብሩ ከተመደቡት 5 አባላት አራቱ አቶ በቀለ ገርባ ፣ አቶ ጃዋር መሃመድ ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ ፣ አቶ ሃምዛ አዳነ በእስር ላይ እንደሚገኙ በመግለፅ ይህ እርምጃ ሆን ተብሎ ምርጫ እንዳንወዳደር ለማድረግ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ስለቀጣይ የኦፌኮ የፖለቲካ ተሳትፎ ያነሳንላቸው አቶ ጥሩነህ ፓርቲው አቋሙን ትላንት ባወጣው መግለጫው ላይ በዝርዝር ማሳወቁን ገልፀውልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጄነራል ዮሐንስ ገ/መስቀል ከዛሬ ጀምሮ የትግራይ አስቸኳይ ጊዜ ግብረኃይልን ይመራሉ።

ከዛሬ ጀምሮ የትግራይ አስቸኳይ ጊዜ ግብረ ኃይል በጄኔራል ዮሐንስ ገብረመስቀል ተስፋማርያም አመራር እንደሚመራ እና ትግራይን የማረጋጋት እንዲሁም መልሶ የመገንባት ሥራ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አሳወቁ።

ጠ/ሚሩ ዛሬ ከሰዓት ከትግራይ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ ግብረ ኃይል እና ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት እንዳደረጉ ገልፀዋል።

ውይይቱ ነበረው በትግራይ ክልል የተከናወኑ ሥራዎችንና ቀጣይ ርምጃዎችን አስመልክቶ መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...የእጩዎች ምዝገባ ጊዜ በድጋሚ አይራዘምም" - ምርጫ ቦርድ

የፖለቲካ ፓርቲዎች የእጩዎች ምዝገባ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ጠየቁ።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ ምዝገባው እንደማይራዘም ገልጾ ፓርቲዎቹ ያለውን ጊዜ በአግባቡ እንዲጠቀሙበት አሳስቧል።

ይህ የተባለው ዛሬ 6ኛውን አገራዊ ምርጫ በማስመልከት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የእጩዎች ምዝገባ ያለበት ሁኔታ፣ የቦርዱ የመረጃ ማዕከል አሰራርና በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ውይይት ባካሄደባት ወቅት ነው።

ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የእጩዎች ምዝገባ ጊዜ ከየካቲት 8 እስከ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ የሚካሄድ የነበረ ሲሆን ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባ ሂደት በተገመገመበት ወቅት የምርጫ ክልል ቢሮዎች ለመከፈት በመዘግየታቸውና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች የእጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንዲራዘም ማድረጉ ይታወሳል።

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ዛሬ በተካሄደው መድረክ አሁንም በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በተለያዩ ምክንያቶች የእጩዎች ምዝገባ ያልጀመሩ እንዳሉ አመልክተዋል።

በመሆኑም አሁንም የተጨመረው ቀን የሚያንስ በመሆኑ እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ የእጩዎች ምዝገባ ጊዜ በድጋሚ እንዲራዘም ጠይቀዋል።

ምርጫ ቦርድ ጊዜ የእጩዎች ምዝገባ ጊዜ በድጋሚ አይራዘምም ብሏል።

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በአብዛኛው የአገሪቱ አካባቢዎች የእጩዎች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰው ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎችን ለማስመዝገብ ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ ማሳሰባቸውን ኢዜአ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ምርጫ ቦርድ ተጨማሪ የሰው ኃይል ይፈልጋል ፦

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ለማስፈጸም 140 ሺህ በላይ አስፈጻሚ ለመሆን የሚችሉ ሰዎቸን ምልመላ የሚያከናውንበት ሂደት በማጠናቀቅ የአስፈጻሚዎችን ፍቃደኝነትን፣ ገለልተኝነትን እና ብቃትን በማረጋገጥ ስራ ላይ ነው።

ምርጫ አስፈጻሚዎች የምርጫ ሂደቱ ዋና አካል መሆናቸውን በመረዳት እና ስራውም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ በመሆኑ እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የሰው ሃይል እጥረት እነዳይፈጠር በማሰብ ተጨማሪ የሰው ሃይል ምልመላ ማከናወን እንዳለበት አምኗል።

በዚህም መሰረት ፦

- ለምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት አገራችሁን ለማገልገል የምትፈልጉ
- ምንም አይነት ፓርቲ አባልነት፣ የዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች ላይ ሰርታችሁ የማታውቁ
- ከሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጪ በሌሎች የቀድሞ ምርጫ የማስፈጻም ተግባራት ላይ ተሳትፋችሁ የማታውቁ
- የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ረጅም አመት የስራ ልምድ ያላችሁ

በዚህ https://nebe.org.et/pworkers/ ፎርም በመጠቀም በሚቀጥሉት አራት ቀናት እስከ የካቲት 27 ድረስ ብቻ ማመልከት ትችላላችሁ።

የስራው ቆይታ ለ4 ወራት ሲሆን ፣ የቀን አበል ፣ አስፈላጊ የሆኑ ቦታዎች / ሁኔታዎች ላይ ጥበቃ ፣ እንዲሁም ስራውን ለማከናወን የሚያስፈልጉ ማንኛውንም ነገሮች ቦርዱ ያሟላል።

የስራ ልምድ ሰርተፍኬት፣ የድጋፍ ደብዳቤ ቦርዱ እንደሚሰጥ ገልጿል።

#ለሌሎችም_እንዲደርስ_ሼር_ያድርጉ!

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በእንሳሮ ወረዳ በ2.2 ቢሊዮን ዶላር ኢንዱስትሪ ሊገነባ ነው !

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እሳሮ ወረዳ ዲረሙ ቀበሌ ሰሊላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ2.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የብሄራዊ ሲሚንቶ አክሲዎን ማህበር ለሚ የግንባታ ቁሳቁስ ኢንዱስትሪ ሊገነባ መሆኑ ተሰማ።

ዛሬ ለዚህ ግዙፍ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ይጣላል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

አጭር መረጃ ስለ እንሳሮ ፦

- እንሳሮ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ካሉት 23 ወረዳዎች እና 4 ከተማ አስተዳደሮች መካከል አንደኛ ዋ ወረዳ ስትሆን ለሚ የወረዳዋ ዋና ከተማ ናት፡፡

- ከአዲስ አበባ 130 ከ.ሜ፣ ከባህር ዳር 513 ኪ.ሜ ከደብረ ብርሃን ደግሞ 83 ኪ.ሜትር ርቀት ላይ ትገኛለች።

- እንሳሮን ከምስራቅ የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ፣ ከሰሜን የሞረትና ጅሩ እንዲሁም የመርሃቤቴ ወረዳ፣ ከምዕራብ ኦሮሚያ ክልል ግራር ጃርሶ ወረዳ፣ ከደቡብ ኦሮሚያ ክልል ውጫሌ ወረዳ ያዋስናታል፡፡

- ወረዳዋ በ13 የገጠር ቀበሌዎችና በ1 የከተማ ቀበሌ አስተዳደር የተከፋፈለች ናት፡፡

- ከ75 ሺህ በላይ ህዝብ የሚኖርባት እንሳሮ 41 ሺህ 27 ሄክታር ያህል የቆዳ ስፍት አላት፡፡

- አየር ንብረቷ 46 በመቶ ቆላ፣ 33 በመቶ ወይና ደጋ እንዲሁም 21 በመቶ ደጋ የሚሸፍን ሲሆን ለኑሮ እጅግ ተስማሚ የሆነ አየር ያላት ናት፡፡

- የህዝቦቿ ዋነኛ መተዳደሪያ ግብርና ነው፡ ከአጠቃላይ የቆዳ ስፋቷ 21,465 ሄክታር መሬት ያህሉ ለእርሻ የዋለ ነው፡፡

ምንጭ : እንሳሮ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Ethiopian Electric Power vacancy announcement .pdf
1.3 MB
ክፍት የስራ ቦታዎች በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፦

በPDF በተያያዘው ፋይል ዝርዝር የስራ ቅጥር መረጃዎችን ታገኛችላችሁ።

* የመመዝገቢያው ቀን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት
* መስፈርቱም የምታሟሉ ከታች ባሉት ሊንኮች በመጠቀም በተዘጋጀው ቅፅ በኦንላይን ሞልቶ መመዝገብ ያስፈልጋል
* በኦንላይን የተመዘገባችሁ አመልካቾች የት/ትና የስራ ልምድ ማስረጃ ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ ማስገባት ትችላላችሁ፤ በአካል መገኘት ማትችሉ በፖስታ ቤት (DMS/EMS,Electric Power, Human Resource Hiring head, Mexico K.Kare New Building)
* ተዛማጅነት የሌለው የትምህርትና ስራ ልምድ ማስረጃ ተቀባይነት የለውም።
* ከስር የተጠቀሰው ሊንክ ካልተሞላ መረጃው ተቀባይነት የለውም።

https://forms.gle/ovkF61wSxxtVeyFX6

Or

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeFaxKfOdbtcD6IQF36NPKmUzfXu17U_I2_agr8JPWTRxXFqA/viewform?usp=sf_link

መልካም ዕድል !
#TikvahFamily

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በሀገራችን ኢትዮጵያ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው ኮቪድ-19 ፦

ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኅብረተሰቡ ዘንድ እየተስተዋለ ባለው ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ዛሬ በሰጡት መግለጫ አሳወቁ።

በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ መምጣቱን የገለጹት ዶ/ር ሊያ ባለፉት 10 ቀናት ብቻ 120 ሰዎች በበሽታው መሞታቸውን ተናግረዋል።

የፅኑ ሕሙማን ቁጥር ከአቅም በላይ መሆኑ እና በዚሁ ምክንያት የሕክምና ማዕከል እጥረት ማጋጠሙ ገልፀዋል።

ኅብረተሰቡ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል በአግባቡ እንዲያደርግ እና የሕግ አካላትም ቁጥጥር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። (ኢብኮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በእንሳሮ ወረዳ በ2.2 ቢሊዮን ዶላር ኢንዱስትሪ ሊገነባ ነው ! በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እሳሮ ወረዳ ዲረሙ ቀበሌ ሰሊላ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በ2.2 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የብሄራዊ ሲሚንቶ አክሲዎን ማህበር ለሚ የግንባታ ቁሳቁስ ኢንዱስትሪ ሊገነባ መሆኑ ተሰማ። ዛሬ ለዚህ ግዙፍ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ይጣላል ተብሎ እየተጠበቀ ነው። አጭር መረጃ ስለ እንሳሮ ፦ - እንሳሮ በአማራ ክልል…
#Ensaro #እንሳሮ

ዛሬ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አ.ማ. ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ በኢፌዴሪ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተቀምጧል። በስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም፣ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘው ተገኝተው ነበር።

አጭር መረጃ ስለ ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ፦

- የሚገነባው በ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ነው።

- ፋብሪካው በለሚ ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ የሚገነባ ነው።

- 270 ሄክታር መሬት ይሸፍናል፡፡

- በመጀመሪያው ዙር ግንባታው 10 ሺህ ቶን ሲሚንቶ ያመርታል።

- ፋብሪካው በኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና በቻይናው ዌስት ቻይና ሲሜንት ኩባንያዎች ሽርክና የሚገነባ ሲሆን ነው።

- ግንባታው በ18 ወራት ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

- ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክሱ ከሲሚንቶ ፋብሪካው በተጨማሪ የመስታወት ፣ የጂፕሰም ቦርድ እንዲሁም ሌሎች ምርቶችን የሚያመርቱ ግዙፍ ፋብሪካዎችን ያካትታል።

- የፋብሪካዎቹ ግንባታ እስከ 10 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ይታሰባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የነዋሪዎች ሰላም የነሱት የምሽት ጭፈራ ቤቶች ፦

ዮናስ በአዲስ አበባ ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት አከባቢ ነዋሪ ነው። አንድ ቀን ምሽት እናቱ እንደታመሙ የሚገልፅ የስልክ ጥሪ ይደርሰዋል። በቻለውን ፍጥነትም እንዲመጣ ይነገረዋል።

በድንጋጤ ከቤቱ ሊወጣ ሲል ከደጃፉ ጀምሮ እስከ ዋናው መንገድ ድረስ በመኪና ተሞልቷል።

መኪናውን አስነስቶ ለመሄድም መውጫ አላገኘም። 

በሩ ላይ የቆሙ መኪና ባለቤቶችን ለማስጠራት ቢሞክርም የትኛው የምሽት ክለብ እንደገቡ ማወቅ አልተቻለም።

የሜትር ታክሲ ለመጠቀም ስልክ ቢደውልም በ4ቱም አቅጣጫ መኪናዎች ስለተደረደሩ የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎች ሊያገኙት ስለማይችሉ በእግሩ የተወሰነ መንገድ እንዲጓዝ ይነግሩታል።

ይህ ሂደት በአጠቃላይ ከ45 ደቂቃ በላይ ፈጅቷል።

በዚህ ምክንያት ዮናስ በፍጥነት መድረስ ሳይችል ቀርቶ የእናቱን አይን ሳያይ አርፈው አገኛቸው።

ዮናስ የእናቱን አይን እንዳያይ ያደረጉት በአካባቢው መንገድ የዘጉ መኪኖች ባለቤቶቹ የት ውስጥ እንዳሉ የማይታወቁና በእኩለ ለሊት ጭፈራ ላይ የነበሩ ናቸው።

ዮናስ የኔስ ወደውጭ የሚያስኬድ ነበር፤ ቤት ውስጥ ሰው ድንገት ቢታመም፣ እሳት ቢነሳ ምን ሊሆን ነው ? በመንደራችን ከምሽት አንድ ሰዓት ጀምሮ ነው መንደሩ በሁሉም አቅጣጫ የሚዘጋው ብሏል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር መፍትሄ ይስጠን የሚለው ዮናስ የምንጠይቀው ቅንጦት አይደለም ፤ እንደ ኢትዮጵያዊ ፤ እንደ ዜጋ የመኖር ክብር ዋስትና እንዲከበርልን እንፈልጋለን ሲል ጠይቋል።

https://telegra.ph/Addis-Ababa-03-04
"... ፈተናውን እወስዳለሁ የሚል ተማሪ ይፈተናል፤ አልፈተንም የሚል ደግሞ ለቀጣይ ዓመት ይፈተናል" - ኢንጂነር አስቴር ይትባረክ

በትግራይ ክልል በሚገኙ 4ቱም ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚሰጥ የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር አስቴር ይትባረክ ገልፀዋል።

ኢ/ር አስቴር እንደገለፁት ፤ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ሁሉም የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች በትግራይ ውስጥ በሚገኙ መቐለ ፣ ዓዲግራት ፣ ራያ እና ኣክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ይፈተናሉ፡፡

ከፈተናው በፊት ለተፈታኞቹ ለፈተና ዝግጁነት የሚረዳ ስልጠና በዩኒቨርሲቲዎቹ እንደሚሰጥ የጠቆሙት ኢንጅነር አስቴር፤ የመፈተን ምርጫው የተማሪዎች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

አብዛኛው ተማሪዎች ከ18 ዓመት በላይ ስለሆኑ በፍላጎታቸውና በወላጆቻቸው ፍላጎት ፈተናው መውሰድ እንደሚችሉ የገለፁት ምክትል ኃላፊዋ ፤ ፈተናውን እወስዳለሁ የሚል ተማሪ እንደሚፈተንና አልፈተንም የሚል ደግሞ ለቀጣይ ዓመት እንደሚፈተን አስታውቀዋል፡፡

መምህራን የካቲት 8 ጀምሮ ስራ እንዲጀምሩ መመሪያ መውረዱን ያስታወሱት ኃላፊዋ፤ ከጸጥታና በትምህርት መሰረተ ልማቶች ላይ ከደረሰው ውድመት ጋር በተያያዘ ሁኔታዎች ፈታኝ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡

የአስተማሪዎች ደመወዝ ሌላው ችግር መሆኑን ያመለከቱት ኃላፊዋ ፤ በተለይ የግል ትምህርት ቤቶች በችግር ውስጥ እንደሚገኙና መንግስት ይሁን ሌሎች ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ምንጭ፦ ወጋሕታ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦

- ትግራይ ነባር እና አዳዲስ ፖሊሶችን እያሰለጠነች ነው። ከፌዴራል ፖሊስ የሄዱ #ተጋሩ የፖሊስ አባላት ተደራጅተው በ6 ዞኖች መደበኛ 15 መሃል ወረዳዎች በመምረጥ ተመድበው የሚሰሩበት ሁኔታም እየተመቻቸ ነው።

- ለትግራይ አዳዲስና ነባር ፖሊሶች ወንጀል ለመከላከል የሚሆን አስፈላጊ ትጥቅ መፈቀዱ።

- የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚሸል ባሽሌት የዛሩ መግለጫ።

- የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት የዛሬ ቀጠሮ።

- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፅ/ቤት የኤርትራ ሠራዊት ከትግራይ ክልል እንዲወጣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አንድ አይነት አቋም መያዙ።

- ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ከዶ/ር አብይ ጋር መወያየታቸው።

- የሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ዛሬ ከተባበሩት መንግስታት ተቋማት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ የግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸው።

- የWFP ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢስሊ በትግራይ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለፃቸው።

(ለቲክቫህ አባላት የተዘጋጀ)
የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ/ም

https://telegra.ph/Tikvah-Tigray-Report-03-04
የቦሎ ክፍያ በንግድ ባንክ በኩል ሊፈፀም ነው፡፡

ዛሬ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓመታዊ የተሸከርካሪ ፈቃድ ማደሻ ክፍያ ለመሰብሰብ ከመንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት ጋር ስምምነት አድርጓል፡፡

ስምምነቱ በኢትዮጵያ የሚገኙ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ተሸከርካሪዎች ባለቤቶችን የዘመናዊ ክፍያ አሠራር ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል፡፡

የክፍያ አገልግሎቱን በባንኩ ቅርንጫፎች ፣ በፖስታ ቤት በሚገኙ የፖስ (POS) ማሽኖች እንዲሁም በኢንተርኔት የባንክ አገልግሎት በኩል በፍጥነት ያለእንግልት ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ፦

• የተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ - 5,557
• በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ - 980
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 760

* 392 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ውድ አባላት በየትኛውም ቦታ ማስካችሁን ማድረግ እንዳትዘነጉ፣ ከሰዎች ጋር ያላችሁን አካላዊ ርቀት ጠብቁ ፤ የእጆቻችሁን ንፅህና መጠበቅ እንዳትዘነጉ።

#Purpose #Tikvah

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia