#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱን ተናገሩ። ለዚህም የማኅበረሰቡ መዘናጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሐምሌ ወር ላይ ከነበረው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል የመጠቀም 78 በመቶ ምጣኔ አሁን ወደ 52 በመቶ መውረዱን ገልፀዋል።

ዶክተር ሊያ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ያለው የጽኑ ህሙማን ክፍል ማከሚያ ማዕከላት መጨናነቃቸውን ተናግረዋል።

በዚህም የፅኑ ህሙማን ክፍል የመጨረሻ የመቀበል አቅም ላይ እየደረሰ ነው ብለዋል።

የፅኑ ህክምና ክትትል ከገቡት 59 በመቶ ህይወታቸው እንዳለፈም አሳውቀዋል።

ዶ/ር ሊያ ፥ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ ትኩረቱን ካላጠናከረ ከባድ የህይወት መስዋትነት ሊያስከፍል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገኙት ክትባቶች በዚህ ዓመት ከሚያዝያ ወር በፊት እንደማይደርሱ ተናግረዋል። ክትባቱን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለማቅረብ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ #AMMA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia