TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tigray

እስከ እሁድ ድረስ የኤሌክትሪክ ኃይል የተቋረጠባቸው የትግራይ ክልል አካባቢዎች መብራት እንደሚያገኙ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዛሬ ለኢዜአ አሳውቋል።

እስካሁን የሁመራ ፣ አላማጣ እና መሆኒ ማከፋፈያ ጣቢያዎች በመጠገን በአካባቢው ከተሞች ሙሉ በሙሉ የሃይል ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለ ተነገሯል።

መቐለን ጨምሮ ሌሎች የማከፋፊያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና እየተከናወነላቸው መሆኑን ተገልጿል።

* ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ብ/ ጀነራል አዳምነህ መንገስቴን ጨምሮ 1 ሺህ ያክል የእዙ የመስመራዊ እና ከፍተኛ መኮንኖች ከእገታ መለቀቃቸውን የሀገር መከላከያ ዛሬ አሳወቀ።

ከእገታ የተለቀቁት የመከላከያ ሰራዊት እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሰሩት የጋራ አሰሳ ስራ እንደሆነ ተገልጿል።

ሰራዊቱ የህወሃት ቡድን ጥቅምት 24 ለግብዣ በሚል ጠርቶ እንዳገታቸው አስታውሷል።

የህወሓት ኃይል መስመራዊ እና ከፍተኛ መኮንኖችን በሸሸበት ቦታ ሁሉ ይዟቸው ሲጓዝ ቆይቶ በቀድሞው የትጥቅ ትግል ወቅት የማዘዣ ቤዝ በነበረው 'አዴት' በሚባል ቦታ አግቷቸው እንደነበርና የህወሓት ታጣቂ ኃይል መደበቁ በአሰሳና በጥናት ተደርሶበታል።

በዚሁ መሰረት የመከላከያ ሰራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ባደረጉት የጋራ አሰሳ እና እርምጃ መስመራዊና ከፍተኛ መኮንኖቹ ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከህወሓት ቡድን አስለቅቀዋል።

ሰራዊቱ ያስለቀቃቸው 1 ሺህ ያክል የመስመራዊ እና ከፍተኛ መኮንኖች አሁን ላይ ሰራዊቱን መቀላቀላቸውን ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#NationalLottery

ልዩ ዕድል ሎተሪ ዛሬ ምሽት ወጣ።

• 20,000,000 ብር የሚያሸልመው የ1ኛ የአሸናፊ ዕጣ ቁጥር - 1705090

• 10,000,000 ብር የሚያሸልመው የ2ኛ የአሸናፊ ዕጣ ቁጥር - 0729356

• 5,000,000 ብር የሚያሸልመው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር - 1206064

• 3,000,000 ብር የሚያሸልመው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር - 0923071

• 1,500,000 ብር የሚያሸልመው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር - 1877734

የሌሎች የዕጣ ቁጥሮችን በዚህ ይመልከቱ : t.me/tikvahethmagazine/9143

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,313
• በበሽታው የተያዙ - 568
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 2,296

አጠቃላይ 114,834 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,769 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 87,244 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

326 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Mekelle

የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ስንዴ ወደ ትግራይ ክልል እየተጓጓዘ መሆኑን አስታውቋል።

በዛሬው እለት ከ12 ሺህ ኩንታል በላይ #ስንዴ የጫኑ 30 ተሽከርካሪዎች መቐለ ከተማ መግባታቸውን ኮሚሽኑ ገልጿል።

አሁን የቀረበው የዕለት ድጋፍ ስንዴ ሲሆን ተጨማሪ 20 መኪኖች በቀጣይ ሳምንታት ይገባሉ ተብሏል፡፡

በአዳማ እና ኮምቦልቻ ከሚገኙ መጋዘኖች የተጫነው ስንዴ በዕለት ደራሽ ድጋፍ ትራንስፖርት በኩል ነው እያጓጓዘ ያለው።

ድጋፉን ያጓጓዙት መኪናዎች በጉዟቸው ወቅይ ምንም አይነት ችግር እንዳላገጠማቸው የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገልጿል።

(የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Mekelle

ዛሬ መቐለ የደረሰው ደጋፍ 12 ሺህ 400 ኩንታል ስንዴ ነው።

በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ የሚሆን 7 ሺህ ኩንታል ዱቄት ከአዳማ ከተማ እየተጫነ እንደሆነ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳውቋል።

በተጨማሪም 15,000 ሜትሪክ ቶን የድጋፍ እህል ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የኮቪድ-19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ መምጣቱን ተናገሩ። ለዚህም የማኅበረሰቡ መዘናጋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሐምሌ ወር ላይ ከነበረው የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል የመጠቀም 78 በመቶ ምጣኔ አሁን ወደ 52 በመቶ መውረዱን ገልፀዋል።

ዶክተር ሊያ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ያለው የጽኑ ህሙማን ክፍል ማከሚያ ማዕከላት መጨናነቃቸውን ተናግረዋል።

በዚህም የፅኑ ህሙማን ክፍል የመጨረሻ የመቀበል አቅም ላይ እየደረሰ ነው ብለዋል።

የፅኑ ህክምና ክትትል ከገቡት 59 በመቶ ህይወታቸው እንዳለፈም አሳውቀዋል።

ዶ/ር ሊያ ፥ ህብረተሰቡ የጥንቃቄ ትኩረቱን ካላጠናከረ ከባድ የህይወት መስዋትነት ሊያስከፍል እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ የተገኙት ክትባቶች በዚህ ዓመት ከሚያዝያ ወር በፊት እንደማይደርሱ ተናግረዋል። ክትባቱን ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር በመሆን ለማቅረብ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ #AMMA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#SHARE #ሼር

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ለሚፈልጉ የማህበረሰብ ክፍሎች ከላይ በተዘረዘሩት ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ከክፍያ ነፃ ናሙና በመስጠት ምርመራ ማድረግ እንደሚቻል አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'የቤት ለቤት ፍተሻ በማይጨው'

በትግራይ ክልል በደቡባዊ ዞን በህግ ማስከበር ስራ ላይ የተሰማራው ደቡብ ዕዝ በሚያከናውናቸው የቤት ለቤት ፍትሻ ስራዎች በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች መያዙን አስታወቀ።

በማይጨው ከተማ በተደረገው 'የቤት ለቤት ፍተሻ' ከ426 ሺህ በላይ የክላሽ ጥይት ፣ ከ 3,500 በላይ የብሬን ጥይት ፣  በርካታ ቁጥር ያላቸው ክላሽንኮቭ እና ሽጉጦች ፣ ከ 1,100 በላይ ልዩ ልዩ የእጅ ቦንቦች መገኘታቸውን ሰራዊቱ አሳውቋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከሚያከናውናቸው የሰላም ጥበቃ ስራዎች ጎን ለጎን የህዝባዊ የድጋፍ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ገልጿል።

በሌላ መረጃ ፦

በማይጨው ከተማ ተቋርጠው የቆዩት የመብራት እና የውሃ አገልግሎቶች የተጀመሩ ሲሆን ህዝቦቿም ወደ ተለመደው የየዕለት እንስቃሴያቸው መመለሳቸውን ሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : telegra.ph/ENDF-12-10

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_አይለያችሁ😷

የኮሮና ቫይረስ ክትባት ጉዳይ ለዓለማችን ተስፋ ሰጪ ቢሆንም በየዕለቱ በኮቪድ-19 የሚያዙ እንዲሁም በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው።

ለምሳሌ ትላንት ብቻ ፦

• በአሜሪካ 3,265 ሰዎች ሲሞቱ 226,953 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል።

• ብራዚል ውስጥ 848 ሰዎች ሲሞቱ 54,203 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• ሜክሲኮ ውስጥ 800 ሰዎች ሲሞቱ 11,006 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ታውቋል።

እንዲሁም ሩሲያ 559 ፣ ጀርመን 543 ፣ ፖላንድ 568 ፣ ጣልያን 499 ፣ UK 533 ሰዎች ሞተውባቸዋል።

በአጠቃላይ በአሁን ሰዓት በዓለማችን በኮቪድ - 19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር ወደ 70 ሚሊዮን ተጠግቷል ፤ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሞተዋል ፤ ከ48 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

* የቁጥራዊ መረጃ ምንጭ (worldometers)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia