ሰበር ዜና! ሰሞኑን በቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ቻይና የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ #አሰብ ወደብን ጎበኙ።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሰብ ወደብ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሰብ ወደብ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ያለውን መንገድም ጎብኝተዋል።

በወቅቱም ወደቡ ላይ የተወሰኑ የማስተካከያ ስራዎች ከተከናወኑ በኋላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

ዛሬ ከሰዓት በኋላም #የምጽዋን ወደብን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethopia