TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ⬆️ደቡብ ፖሊስ የ2010 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ቻምፒዮን ሆኗል። በስፍራው የነበረው የቻናላችን ቤተሰብ ከላይ የምትመለከቷቸውን ፎቶዎች አጋርቶናል።

©ቴዲ ከአዳማ(TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️የቀድሞው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዘዳንት #ጁነዲን_ሳዶ ትላንት ነሀሴ 28/2010 ኢትዮጵያ ገብተዋል።
.
.
.
የቻናላችን ቤተሰብ አባል የሆነች ስሟን የማልገልፀው ወዳጃችን #ከሳምንታት ቀደም ብላ አቶ ጁነዲን ሳዶ ወደ ሀገር እንደሚገቡ አሳውቃን ነበር⬇️

*****************************
#update የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ጁነዲን ሳዶ ነሀሴ 28 ከቀኑ 7:30 ወደ ሀገሩ ይገባል።

©ከቤተሰቡ የቅርብ ሰው(መ)
*****************************

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የተሰጠን እድሜ እንኳን ለጠብ ለፍቅርም አይበቃም ተፋቅሮ መኖርን የመሰለ ምንም ነገር የለም።

💚💛❤️ሰላም እደሩ💚💛❤️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ⬆️

"ፕ/ር ብርሐኑ ነጋን የግንቦት 7 ዋና ሊቀመንበር እና አባላቱ ወደውዲቷ ሀገራቸው ኢትዬጵያ የሚገቡበትን ቀን በናፍቆት በመጠባበቅ ላይ በአቃቂ የሚገኙ ወጣቶችና እንዲሁም ደጋፊዎች ከሦስት መቶ በላይ እየተሰባሰቡ ናቸው በተለያዩ ቦታዎችም ላይ እዚያው አቃቂ ላይ ትልቅ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል ኢትዬጵያን እግዚአብሔር ይባርክ (ይቺን እናታችንን ኢትዬጵያን በጋራ እንከባከባት ) መልካም ዘመን ለህዝባችን"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሲቪል ሠርቪስ ሠራተኞች የብቃት ማረጋገጫ #ፈተና ሊሰጥ ነው፡፡ የቀድሞው አስተዳደር በሀሰተኛ ሠነድ የተቀጠሩ ሠራተኞች ራሳቸውን እንዲያጋልጡ ማስታወቂያ አስነግሮ የነበረ ቢሆንም፣ ይሕ ግን እምብዛም አዋጪ አልሆነም፡፡ አዲሱ አስተዳዳር በስሩ የሚገኙ አንድ መቶ አምስት ሺህ ሠራተኞች እንዳስፈላጊነቱ ፈተና ተሰጥቷቸው፣ በሚመጥናቸው ሥራ እንዲመደቡ ይደረጋል ብሏል፡፡

©ዋዜማ ሬድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update

📌የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ገና #አልተወሰነም፡፡
📌የ10ኛ ክፍል ማለፊያ ዉጤት እስከ ዓርብ ጳጉሜን 2/13/2010 ዓ.ም #ይፋ ይደረጋል፡፡

@tsegawolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! ሰሞኑን በቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም ቻይና የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐቢይ_አህመድ #አሰብ ወደብን ጎበኙ።

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሰብ ወደብ ሲደርሱ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሰብ ወደብ እስከ ኢትዮጵያ ድንበር ያለውን መንገድም ጎብኝተዋል።

በወቅቱም ወደቡ ላይ የተወሰኑ የማስተካከያ ስራዎች ከተከናወኑ በኋላ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ስራ ይገባል ብለዋል።

ዛሬ ከሰዓት በኋላም #የምጽዋን ወደብን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethopia
#update ዶክተር #አብይ_አህመድ ኤርትራ ናቸው። ዛሬ የአሰብ ወደብን ጎብኝተዋል። የምፅዋን ወደብም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

📌ዶክተር አብይ አሰብ ወደብ ሲደርሱ በኤርትራው ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ፎቶ፦ ከምስል ክምችት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update⬆️ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በአጭር የጽሑፍ መልዕክት አገልግሎት ከሚሰጡ ከ180 በላይ ኩባንያዎች ውስጥ 40ዎቹ #መታገዳቸውን ኩባንያው ይፋ አደርጓል፡፡ ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ ያለአግባብ ከቴሌኮም ደንበኞች ተቆርጧል። ያለአግባብ ከደንበኞች ገንዘብ የቆረጡ ኩባንያዎችን በፍርድ ቤት ጭምር የወሰዱትን ገንዘብ #እንደሚያስመልስ ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አፋር⬆️

በቅርቡ ከስደት ወደ አገር ቤት የተመለሱት የአፋሩ ሱልጣን ሐንፍሬ ዓሊሚራህ ሰመራ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ሱልጣን ሐንፍሬ ወደ አፋር ያቀኑ ከማህበረሰባቸውና ከክልሉ የስራ ኃላፊዎች ጋር ተገናኝቶ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነው፡፡

📌 #ሱልጣን_ሐንፍሬ ለስደት ከመዳረጋቸው በፊት የአፋር ክልላዊ መንግስት የሽሽግር ጊዜ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው አገልግለዋል፡፡

©etv
ፎቶ፦ዱኮ ሂና
@tsegabwolde @tikvahethiopia