TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የሌሎች ትምህርቶች የፈተና ውጤትም ሊፈተሽ ይገባዋል!

የስኮላስቲክ አፕቲቲዩድ የፈተና #ውጤት ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የትምህርት አይነቶች በአግባቡ ሊፈተሹ እንደሚገባ አስተያየታቸውን ለTIKVAH-ETH የሰጡ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ገልፀዋል። በአንዳንድ የትምህርት አይነቶች ላይ የተመዘገቡ ተመሳሳይነት ያላቸውና ከፍተኛ ውጤቶች ጥርጣሬን የሚያጭሩ በመሆናቸው ኤጀንሲው ዳግም #ሊፈትሸው ይገባል ብለዋል። በሌላ በኩል ደግሞ ፍፁም ከሚጠበቀው በታች የወረዱ ውጤቶችም እንዳሉ አንስተው፤ ይህ በትውልድ ላይ ታልቅ አሻራ የሚያሳርፍ ስለሆነ ኤጀንሲው ጊዜ ወስዶ ፈተናዎቹን መመልከት አለበት ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ፎቶ፡ Bexo/TikvahEthiopiaFamily
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ለተማሪዎች

📎የ10ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና #ውጤት ይፋ ማድረጊያ ቀንን እንዲሁም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ #መቁረጫ ነጥብ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት የምንሰማው መረጃ ካለ ወዲያው የምናሳውቃችሁ ይሆነል። ነገር ግን በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የ10ኛ ክፍል ውጤትን እንዲሁም የመቁረጫ ነጥብን በሚመለከት የሚናፈሰው ወሬ #ሀሰተኛ መሆኑን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደረገ። ተማሪዎች ውጤታቸውን ፦ • በዌብ ሳይት https://eaes.edu.et/ ወይም • በ6284 አጭር የጽሑፍ መልዕክት መላኪያ ላይ የምዝግባ ቁጥራቸውን (Registration Number) ብቻ በመላክ ወይም • በቴሌግራም ላይ  https://publielectoral.lat/eaesbot ማየት ይችላሉ። የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሆኑ ውጤታቸውን የተመለከቱ ተማሪዎች ውጤት…
#ውጤት

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጎ ተማሪዎች እና የተማሪዎች ወላጆች ውጤት እየተመለከቱ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ እስካሁን ባደረገው ምልከታ እና ከቤተሰቡ አባላት የተላኩት የውጤት መግለጫ መልዕክቶች ከላይ ተያይዘዋል።

የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ እስካሁን ያልተገለፀ ሲሆን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች የመቁረጫው ነጥብ ይፋ እንደተደረገ ተደርጎ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
#EOTC

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ በደብረ ኤልያስ ብሔረ ብፁዓን መልክዓ ሥላሴ አንድነት ገዳም ተፈጸመ የተባለውን ችግር በተመለከተ በዝርዝር  የማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ዛሬ ምሽት አስታወቀች።

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ ቤት ገዳማት አስተዳደር መምሪያ ከሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ጋር በመገናኘት በገዳሙ ተፈጸመ የተባለውን ችግር በተመለከተ በዝርዝር የማጣራት ሥራ እያከናወነ እንደሚገኝ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አሳውቋል።

ፅ/ቤቱ በማዕከል ደረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ላይ እንደሚገኝም ገልጿል።

ዝርዝር ሁኔታው በሚገባ ተጣርቶ የተደረሰበት የማጣራት #ውጤት  እውነታውን በሚገባ በሚያሳይ መልኩ በቤተክርስቲያኗ ማዕከላዊ አስተዳደር የሚገለጽ ይሆናል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፅ/ቤቱ ፤ በአርሲ ሀገረ ስብከት በጢዮ ወረዳ በጨፌ ሚሶማ ቀበሌ ገበሬ ማኀበር በዴራ አማኑኤል አጥቢያ ቤተክርስቲያን ግንቦት 20 ቀን 2015 ዓ.ም ምሽት ላይ በኦርቶዶክሳውያን ላይ ደረሰ ተብሎ በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች የተገለጸውን ጥቃት በተመለከተ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጥልቅ ሐዘን እንደሰተማት ገልጿል።

በሀገረ ስብከቱ በኩል ተጣርቶ በሚቀርቀው መረጃ መሰረት ጉዳዩን  በህግ አግባብ  የምትከታተለው መሆኑን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በፀጥታ ችግርና በሌሎች ምክንያቶች ፈተና ያልወሰዱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ለመፈተን መዘጋጀቱን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አስታውቋል፡፡ የ2015 ዓ.ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሰርተፊኬት (12ኛ ክፍል) ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በሁለት ዙር መሰጠቱን አገልግሎቱ አስታውሷል፡፡ ይሁንና በጎንደርና በጋምቤላ…
የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና #ውጤት በፀጥታ እና በሌሎች ምክንያቶች ፈተናቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከወሰዱ በኃላ ይገለፃል ተብሎ ይጠበቃል።

በፀጥታ ችግር እና ሌሎች ምክንያቶች ፈተናቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ከመስከረም 8 እስከ መስከረም 11 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ፈተናቸውን ይወስዳሉ።

የእነዚህ ተፈታኞች እና የመጀመሪያው ዙር ፈተና ተፈታኞች ውጤት አንድ ላይ እንደሚገለፅ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ከቀናት በፊት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን መስከረም 2016 ዓ/ም አጋማሽ ድረስ ይፋ ለማድረግ እና ጥቅምት ወር 2016 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲ ትምህርት እንዲጀመር እቅድ መያዙን መግለፃቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#NationalExam

በባለፈው አመት በጎንደር ከተማ በነበረው ግጭት ምክንያት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ይሰጥ የነበረውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ  ፈተና ያላጠናቀቁ ተማሪዎች ባለፉት ሁለት ቀናት ወደ ተቋሙ በመግባት ፈተናውን መውሰዳቸው ተገልጿል።

በአጠቃላይ በፀጥታ ችግር ፈተናውን ማጠናቀቅ ሳይችሉ ቀርተው የነበሩ 11 ሺህ 851 ተማሪዎች መስከረም 10/2016 ዓ.ም እና መስከረም 11/2016 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብተው ፈተናውን ወስደዋል።

ተማሪዎቹ የኬሚሰትሪ፣ ባዮሎጂ እና የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር ትምህርት ፈተና እንደወሰዱ ተጠቁሟል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ለክልሉ ሚዲያ (አሚኮ) በሰጡት ቃል ፤ ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናው በፍጥነት አርሞ ውጤቱ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ይፋ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።

በሀገር አቀፍ ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ጣቢያ ኃላፊ ሄነው የተመደቡ አቶ ወንድወሠን ሽፈራው ፤ የተማሪዎች ፈተና ቶሎ ታርሞ ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግ ከትምህርት ሚኒስቴር በኩል መረጃ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትም ፤ የተማሪዎቹ ፈተና በፍጥነት ታርሞ ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግ አሳውቋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና #ውጤት በፀጥታ እና በሌሎች ምክንያቶች ፈተናቸውን ያልወሰዱ ተማሪዎች ፈተናቸውን ከወሰዱ በኃላ እንደሚገለፅ ማሳወቁ ይታወሳል።

አገልግሎቱ ከዚህ ቀደም እንዳሳወቀው ከሆነ አሁን ፈተናቸውን የተፈተኑ ተፈታኞች ከመጀመሪያው ዙር ፈተና ተፈታኞች ጋር አንድ ላይ ውጤታቸው ይገለጻል።

በቅርቡ የአገልግሎቱ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ማንጠግቦሽ አዳምጤ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፈተናውን የማረም ሥራ በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረው ምናልባትም እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" 15 ሺህ 592 ሰራተኞች ፈተና ወስደዋል " - የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመንግስት ሰራተኞች የብቃይ ምዘና ፈተና በዛሬው ዕለት ተሰጥቷል። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ባገኘነው መረጃ ፈተናውን 15 ሺህ 592 ሰራተኞች ፈተናቸውን ወስደዋል። ፈተናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት…
#Update

የሰራተኞች ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች የተሰጠው ፈተና #ውጤት ይፋ ሆኗል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀው እና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረው ፈተናን በሚመለከት በዛሬው ዕለት መግለጫ ተሰጥቷል።

በዚህ መግለጫም ፤ የቴክኒክና ባህሪ ብቃት ፈተናው የወሰዱት የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ሰራተኞች ቁጥር 15 ሺህ 151 መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ውስጥ የአመራሩ ቁጥር 4 ሺህ 213 ሲሆን የፈተውን ማለፊያ ውጤት ያመጡት 1 ሺህ 422 ናቸው። ይህም 34 በመቶው አመራሮች አልፈዋል። አመራሩ ለማለፍ ከ60 በመቶ በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናውን የወሰዱ የሠራተኞች ቁጥር 10 ሺህ 257 ሲሆኑ ያለፉት 5 ሺህ 95 ናቸው ተብሏል። ይህም 50 በመቶ ነው። ሰራተኞች ለማለፍ ከ50 በመቶ በላይ ማምጣት አለባቸው።

ለፈተና ከተቀመጡት አጠቃላይ ቁጥር 681 የሚሆኑት በተለያየ የስነ ምግባር ጥሰት ከፈተና ውጪ መሆናቸውን እና 441 የሚሆኑት ደግሞ በፈተና ስፍራ ያልተገኙ መሆናቸው ተገልጿል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከኢፕድ እና ከአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ልማት ቢሮ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ውጤት : የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይገለጻል።

የትምህርት ሚኒስቴር በውጤቱ ዙሪያ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል።

መግለጫውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ የሚያሰራጭ ይሆናል።

ይጠብቁ !

#TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ውጤት : የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይገለጻል። የትምህርት ሚኒስቴር በውጤቱ ዙሪያ ከደቂቃዎች በኃላ መግለጫ ይሰጣል። መግለጫውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቀጥታ የሚያሰራጭ ይሆናል። ይጠብቁ ! #TikvahEthiopiaFamilyAddisAbaba @tikvahethiopia
#ውጤት : የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።

ሚኒስትሩ የፈተናው ውጤት ለሊት 6 ሰዓት ላይ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

መግለጫውን ከላይ በቀጥታ ይከታተሉ።

@tikvahethiopia
#ውጤት

የ2016 የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን አስመልክቶ የትምህርት ሚኒስቴር የሰጠው ሙሉ መግለጫ #1

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia