TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
🇪🇹 የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹 “ ... ያለፉትን ዘመናት እኮ #እንደ_ቅንጦት እንድናይ የተገደድንበት ጊዜ ነው ” - ጎጎት ፓርቲ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ' #የፖለቲካ_ፓርቲዎች_ምን_ይላሉ ? ' በሚል በህጋዊ መንገድ ተመዝገበው ለሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች እያቀረበ ያለውን ወቅታዊ ሀገራዊ ጥያቄዎች በመቀጠል ጎጎት ፓርቲን አነጋግሯል። የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊው አቶ ጀሚል ሳኒ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ…
🇪🇹 የፓለቲካ ፓርቲዎች ምን ይላሉ ? 🇪🇹

“ ሰው በጣም እየተሰቃዬ ነው ያለው መንግስት ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ” - ወህዴግ

የወላይታ የህዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ወህዴግ) ፓርቲ አመራር አባል አቶ ተክሌ ቦረና ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

Q. በተለይ የእርስዎ ፓርቲ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ ከደመወዝ አለመከፈልና መቆራረጥ ጋ በተያያዘ ሠራተኞች ተማረዋል። ችግሩ በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ? ያላችሁ ግምገማስ ምንድን ነው ?

አቶ ተክሌ፦

“ የደመወዝ ቅሬታ ቅሬታ ሆኖ እስከሚቀርብ መጠበቅ የሌለበት አግባብነት የሌለው ጉዳይ ነው።

ምክንያቱም በዓመቱ መጀመሪያ የደመወዝ በጀት በሠራተኞች ልክ ተሰልቶ ይመደባል በመንግስት።

ግን አዲስ የሰው ኃይል ሳይጨመር በነበረው ሆኖም የተወሰነ ርቀት እንደተሄደ ‘ ደመወዝ የለም ’ የሚያሰኝ ነገር ምን እንደሆ አሳማኝ ነጥብ የለም።

ምናልባት ከደቡብ የክልል አከላለል ጋር ተያይዞ ሠራተኞች ከቦታ ቦታ ይዘዋወራሉና ደመወዝ ከፋዮቹ በዚያ ለማሳበብ ይሞክሩ ይሆናል። 

እሱም ቢሆን ሠራተኞች የሚያገኙትን ደመወዝ ይዘው ይሄዳሉ እንጂ አዲስ ስጡን ብለው አይጠይቁም።

በመሆኑም እንዲህ አይነት ችግር የሚያስከትሉ ሰዎች ምክንያታቸው አጥጋቢ አይደለም።

አንዳንዴ ‘ ከማዳበሪያ ዋጋ ጋር ተገናኝቶ ’ የሚባል ነገር አለ። በምንም ተዓምር የደመወዝ በጀት ቆርሶ ለሌላ ጥቅም ማዋል አይገባም በአገሪቱ ህግ መሠረት። 

ለምን እንደዚህ እንደሚደረግ አይገባንም። ”

Q. የደመወዝ መቆራረጥ ድሮውንም የናረውን የኑሮ ውድነት ለሠራተኞቹ ይበልጥ ፈታኝ እንዳደረገው ስሞታ ይቀርባል። የፓርቲዎ ግምገማና መልዕክት ምንድን ነው ?

አቶ ተክሌ፦

“ በህጉ መሠረት ሠራተኛው ሳይስማማ፣ ፈርሞ ሳያጸድቅ ከደመወዙ አንድ ሳንቲም አይነካም። ደመወዝ ከፋይ እኔ ነኝ እንደፈለኩ አደርጋለሁ የሚል ኃይል አይኖርም።

ያለ ፈቃድ የሚደረግ ነገር በሙሉ ህገወጥ፤ እንደ ወንጀል የሚቆጠር ነው። የሰውን ገንዘብ ቀምቶ እንደመውሰድ ነው።

ደመወዝ ባይቆረጥም የኑሮ ውድነቱ ከደመወዝ ጋር የሚመጣጠን ባለመሆኑ ሠራተኛው ሊቋቋመው አልቻለም። በየሰዓቱ የዋጋ ጭማሪ አለ።

ሰው በጣም ተቸግሮ ነው ያለው። በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ፍላጎቶች በማሟላት ብቻ እያብቃቃ ነው የሚኖረው። 

የዋጋ ንረትና የደመወዝ ሁኔታ በምንም ተዓምር ለጎን ለጎን የሚሄዱና ንግግር ውስጥ የሚገቡ ነገሮች አይደሉም። ሰው በጣም እየተሰቃዬ ነው ያለው መንግስት ኃላፊነቱን መወጣት አለበት። ”

Q. ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል አለመወሰን ለኑሮ ውድነቱ መባባስ እንደ መንስኤ ይነሳል። ፓርቲዎስ ያለው ምልከታ ምንድን ነው ?

አቶ ተክሌ ፦

“ ይሄ የመኖርና ያለመኖር ጥያቄ ነው። መንግስት በጣም በተለዬ ሁኔታ ትኩረት ሊሰጠው፣ ሊጸድቅ ይገባል።

ከዚህም ባሻገር መንግስት ምርት መጋዘን እያከማቹ በአንድ ወቅት በማውጣት ዋጋ የሚጨምሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰድ አለበት።

ችግሩ የ120 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ስለሆነ መንግስት በዬአካባቢው የራሱን ሱቅና መጋዘን ሊከፍት ይገባል። ያኔ ተመጣጣኝ ዋጋ ይኖራል። ”

Q. የተሟላ መሠረተ ልማት አለመኖር ፈታኝ እንደሆነባቸው ነዋሪዎች ሲገልጹ ይስተዋላል። የፓርቲዎ ግምገማ ምን ይመስላል ?

አቶ ተክሌ፦

“ መሠረተ ልማት ይጀመርና ይተዋል። እንደገና 5፣ 6 ዓመታት ከበሰበሰ በኋላ ብዙ ሲገለጽ ይሰማል።

እንዲህ አይነት ችግር በመንገድ፣ በህንፃ ግንባታ በብዙ ቦታዎች  ይስተዋላል።

የመሠረተ ልማት ግንባታ እየተስተጓጎለ ነው። በጀትም በትክክል ሥራ ላይ አይውልም። ስለዚህ ቆምና አሰብ አድርጎ ማስኬድ ያስፈልጋል። ”

Q. እንደ ፓርቲ የሚደርስባችሁ ጫና አለ? ካለ ምንድን ነው?

አቶ ተክሌ፦

“ ጫናው አለ። ለምን ኖረ? የሚለውን ስናይ በተለይ ታች ያሉት የመንግስት ካድሬዎች የሰለጠኑ አይደሉም። 

የመድብለ ፓርቲ ሥርዓት መኖር ለዴሞክራሲ ስርዓት መዳበር ፋይዳ እንዳለው አያውቁም። ተፎካካሪ ፓርቲዎችን እንደ ጠላት እያዩ ችግር ይፈጥራሉ።

ችግር የሆነብን ይሄ ነው። ስለዚህ መንግስት ታች ወርዶ ከወረዳ እስከ ዞን መስራት አለበት።”

Q. ስለሙስና የፓርቲዎ ግምገማ ቢያጋሩ?

አቶ ተክሌ፦

“ የሙስና ጉዳይ በጣም እድሜ ያስቆጠረ ነው። 
በኢትዮጵያ በኮሚሽን ደረጃ ተቋም ተደራጅቶ ኃላፊነት ወስዶ በመስራት ላይ እንዳለ ነው የምንሰማው ነገር ግን ችግሩ አልተቀረፈም።

አሁንም ጠንካራና የተሻለ ሲስተም መዘርጋትና መቆጣጠሮ ያስፈልጋል። በሌላ በኩል የህዝቡ የኑሮ ውድነት ቢቀረፍ ሁሉም ስለሚዋጋ ችግሩ እየሟሸሸ ይሄዳል ” ብለዋል።

#የፓለቲካፓርቲዎችምንይላሉ? #ወህዴግ

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia