TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
NATO ሩስያ ላይ ዛተ። የNATO ዋና ፀሀፊው ጄንስ ስቶልተንበርግ ፤ የጥምረቱ ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ በሚያቀርቡበት መስመር ላይ ሩስያ ጥቃት እንዳትፈፅም አጥብቀው አስጠንቅቀዋል። ሩስያ ለዩክሬን የጦር መሳሪያዎች ድጋፍ በሚቀርብበት መስመር ላይ ጥቃት ከሰነዘረች ጦርነቱ በአደገኛ ሁኔታ እንደሚባባስ አስገንዝበዋል። ስቶልተንበርግ ፤ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጡት እሳቸው ፣ የካንዳ ጠ/ሚ…
አሜሪካ ሩስያን አስጠነቀቀች።

የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ሩስያ በNATO አባል ሀገር በሆነችው #ፖላንድ ላይ ጥቃት ከሰነዘረች NATO ምላሽ እንደሚሰጥ አስጠንቅቀዋል።

የደህንነት አማካሪው ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጡት ዛሬ ሩስያ በፖላንድ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ የዩክሬን የጦር ሰፈር ላይ የአየር ድብደባ ከፈፀመች በኃላ ነው ፤ በጥቃቱ 35 ሰዎች መገደላቸው እና 134 ሰዎች መቁሰላቸው ተነግሯል።

የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫን ለCBS በሰጡት ቃል በNATO ግዛት ላይ አንዳች ወታደራዊ ጥቃት ቢሰነዘር አንቀፅ 5 ወደ ትግበራ እንደሚገባና የNATO ሙሉ ኃይል ምላሽ እንደሚሰጥ አስጠንቅቀዋል።

ዛሬ ሩስያ በፖላንድ ድንበር በሚገኝ የዩክሬን ጦር ሰፈር ላይ የፈፀመችው ጥቃት ምዕራባውያን ለዩክሬን የሚያደርጉትን ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያቆሙ ካስጠነቀቀች ከአንድ ቀን በኃላ ነው።

ምንም እንኳን ሩስያ ምዕራባውያን " አርፋችሁ ቁጭ በሉ ዩክሬንን በወታደራዊ ትጥቅ አትደግፉ " ብትልም የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሱሊቫን ሀገራቸው አሜሪካ የዩክሬን ኃይሎችን በወታደራዊ እርዳታ መደገፏን እንደምትቀጥል ዛሬ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ፤ አሜሪካ እና አጋሮቿ የNATO ግዛትን እያንዳንዱን ኢንች እንደሚከላከሉ ገልፀው " ሩሲያ በአጋጣሚ ወይም ሳታስበው ጥቃት ብታደርስ እራሱ NATO ምላሽ ይሰጣል " ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ሱሊቫን ፥ " የምለው ነገር ቢኖር ... ሩስያ በNATO ግዛት ላይ ጥቃት ብትከፍት፣ አንዲት ጥይት ብትተኩስ የNATO ጥምረት ምላሽ ይሰጣል " ሲሉ ነው የተናገሩት።

NB : ፖላንድ የNATO አባል ሀገር ናት።

@tikvahethiopia
#ዓለምአቀፍ #ፖላንድ

በፖላንድ ፤ እ.አ.አ. ከ2011 ጀምሮ ለቪዛ ያመለከቱ ሰዎች ዝርዝር ላይ #ኦዲት ሊደረግ ነው ተባለ።

በፖላንድ ለአፍሪካውያን በክፍያ ቪዛ እየተሰጠ ነው በሚል መንግሥት ላይ ጥያቄ ማስነሳቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

የፖላንድ የላይኛው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ቶማዝ ግሮዲዚ በአገሪቱ ገንዘብ እየተቀበሉ ቪዛ የመስጠት አካሄድ ተባብሷል ብለዋል።

መንግሥት ስለ ጉዳዩ ምን መረጃ እንዳለው ይፋ እንዲያደርግም ጠይቀዋል። ነገሩ የአገሪቱን ስም እያጠለሸ ነው ብለዋል።

መንግሥት የተወሰነ መረጃ ይፋ ያደረገ ሲሆን ፤ እንደ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ ግን ስደተኞች እስከ 5,000 ዶላር እየከፈሉ የሥራ ቪዛ የማግኘት ሂደቱን ያፋጥናሉ ተብሏል።

እስካሁን ሰባት ሰዎች ላይ ክስ ቢመሠረትም ከመካከላቸው የመንግሥት ባለሥልጣን እንደሌለ ታውቋል።

የአገሪቱ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፒዮር ዋውዚክ ፤ ባለፈው ሳምንት ክሶችን ተከትሎ ከሥራ ተነስተዋል። የፖላንድ ፀረ ሙስና ኮሚሽን መሥሪያ ቤቱ ላይ ምርመራ ካደረገ በኋላ ነው የተባረሩት።

የሕግ ክፍሉ ዳይሬክተርም ተባረዋል።

እ.አ.አ. ከ2011 ጀምሮ ለቪዛ ያመለከቱ ሰዎች ዝርዝር ላይ ኦዲት እንደሚደረግ ተገልጿል።

ተቃዋሚ የምክር ቤት አባል ፤ እስከ 250,000 ቪዛዎች ሕግ ሳይከተሉ ለእስያ እና አፍሪካ አመልካቾች ተሰጥተዋል ሲሉ ገልጸዋል።

መንግሥት ግን ቁጥሩ በጥቂት መቶዎች ብቻ የሚቆጠር ነው ሲል አስተባብሏል።

የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶናልድ ተስክ ፤ " ከአፍሪካ ፖላንድ መምጣት የፈለገ ሁላ ከኤምባሲያችን ቪዛ ገዝቶ አገራችን በቀላሉ ይገባል " ብለዋል።

የፖላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን ይህ ንግግር ቀውስ እንደሚያስከትል ገልጸው ችግሩ የተባለውን ያህል እንዳልሆነ ተናግረዋል።

" አገራችን ኃላፊነት የሚሰማት ዴሞክራሲያዊ አገር ሆና ሳለ የነጻውን ዓለም ደኅንነት አደጋ ውስጥ የምትከት ሆና እንድትታይ የሚያደርግ አካሄድ ስለሆነ በጥልቀት ሊብራራ ይገባል። ይህ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ትልቁ ቅሌት ነው። ሙስና በመንግሥታችን ተንሰራፍቷል " ሲሉ የላይኛው ምክር ቤት አባል አሳስበዋል።

የፍትሕ ሚኒስተሩ ዚግኒው ዚዎብሮ ፤ ይህ አባባል የተጋነነ ነው ሲሉ ለብሔራዊ ቴሌቭዥን ጣቢያ ተናግረዋል።

ይህ ጉዳይ ከስደተኞች ጉዳይ ጋር በተያያ በቀጣዩ የፓርላማ ምርጫ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር መገለፁን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia