TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Peace

የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ከሃይማኖት ተቋማት እና ሲቪክ ማህበራት ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

በዚህ ውይይት ላይ ምን አሉ ?

- የሰላም ስምምነቱ #የህዝብ ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ነው ብለዋል።

- የሰላም ስምምነቱ ፤ ከፍተኛ የሆነ ችግር ላይ ያለውን ህዝብ ለማዳንና ህዝቡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዲጠቀም ሰላም እንዲያገኝ ለማድረግ የተደረሰ መሆኑን ገልፀው ሌሎች ጉዳዮች በህገመንግስት መሰረት ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚፈለግላቸው መሆኑን ገልፀዋል። ስምምነቱ ከምንም በላይ ተኩስ የማቆም ጉዳይ ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

- የተደረሰው  የሰላም  ስምምነት  ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ ባለበት በዚህ ወቅት ላይ አሁንም የኤርትራው ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ ኃይል በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ግፍ እየፈፀመ፣ ንብረት እየዘረፈ ፣ እያወደመ መሆኑና ስምምነቱ እንዲደናቀፍ እየሰራ እንደሆነ ገልፀው የፌዴራል መንግስት የህዝቡን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነበት ስላለበት ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

- በስምምነቱ መሰረት ሰብዓዊ እርዳታ እና መድሃኒት እየገባ መሆኑን ተናግረዋል። " ስምምነቱ ላይ ድጋፍ በአቸኳይ እንዲገባ የሚል ነገር ነበር በወቅቱ ወዲያው የገባ ድጋፍ አልነበረም አሁን ግን ቀስ በቀስ የሚገባው ሰብዓዊ ድጋፍ እየጨመረ ነው " ብለዋል። እህል እና መድሃኒት ይዘው የሚገቡ ተሽከርካሪዎች እየጨመሩ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ደብረፅዮን ፤ ዓለም አቀፍ እርዳታ አቅራቢዎች በሙሉ ወደ እንቅስቃሴ ገብተዋል ብለዋል።

- ወደ ክልሉ ከሚገባው የሰብዓዊ እርዳታ ጋር በተያያዘ በስምምነቱ መጀመሪያ ሰሞን ላይ አስፈላጊው ስራ በጊዜ ስላላለቀ እና ባለመዘጋጀቱ ወደ ትግበራ እንዳልተገባ አሁን ላይ ግን ሁሉም ዝግጁ መሆኑን ፣ የሚያደናቅፍ ነገር እንደሌለው ፣ በመንገድ ላይ የነበረው በርካታ ፍተሻና የቁጥጥር ጣቢያዎች አሁን መስተካከሉን ተናግረዋል።

- ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ፤ " የተቋረጡት መሰረታዊ አገልግሎቶች መልሰው አልተከፈቱም " ያሉ ሲሆን " በኛ በኩል ሙሉ ዝግጅት አድርገናል #ባንክ#ቴሌኮም እንዲጀምር ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል ባለን አነስተኛ አቅም እየተጠቀምን ብንቆይም መስተካከል ያለባቸው ነገሮች መስተካከል አለባቸው። በፌዴራል አገልግሎት ሲሰጡ የነበሩ እያንዳንዳቸው ተፈትሸው ስራ ለመጀመር ምን ያስፈልጋቸዋል  ?  የሚለው ተጠንቷል። አገልግሎት ወደ ነበረበት ለመመለስ ሙሉ ዝግጅት ተደርጓል ፤ አሁን የሚቀረው ስርዓት አስይዞ ከፌዴራል አገልግሎት ሰጪ አካላት ጋር በመነጋገር በቅደም ተከተል ማስፈፀም ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
" ይህ የተለየ የቪፒኤን አይነት ነው " - ኢትዮ ቴሌኮም

ኢትዮ ቴሌኮም በሞባይል ቪ.ፒ.ኤን (VPN) ጥቅል አገልግሎቱ ላይ የዋጋ ማሻሻያ በማድረግ እንዲሁም ያለተገደበ አማራጭን አካቶ ማቅረቡን ገለፀ።

ድርጅቱ ፤ በቪ.ፒ.ኤን (VPN) አገልግሎቱ ደህንነቱ በተጠበቀ የዳታ አገልግሎት #የድርጅት አገልግሎት ማሳለጥ፣ #ቢሮዎችን እርስበእርስ ማገናኘት እንዲሁም በየትኛውም ቦታ የድርጅት መረጃ እና መሳሪያዎች በመጠቀም ቢዝነስ ማከናወን የሚያስችል ነው ብሏል።

ደንበኞቹ ፤ አገልግሎቱን ለማግኘት በአቅራቢያቸው የሚገኝ የድርጅት አገልግሎት መስጫ ማዕከሎችን መጎብኘት እንደሚችሉ ጠቁሟል።

ነገር ግን ድርጅቱ የዋጋ ማሻሻያውን በሚመለከተ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቹ ያሰራጨው መረጃ በርካቶችን ጋር ያጋባና " VPN ምንድነው ? " ብለው እንዲጠይቁ አድርጓል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ወራትን ካስቆጠረው የማህበራዊ ሚዲያዎች #ገደብ ጋር የሚገናኝ የመሰላቸውም ብዙ ናቸው።

ለመሆኑ ቪ.ፒ.ኤን (VPN) ምንድነው ?

(ኢትዮ ቴሌኮም)

ቪ.ፒኤ.ን (VPN) ማለት የግል እና የመንግስት ተቋማት ከተለያዩ ቅርንጫፎቻቸው ጋር እንዲገናኙ የሚያደርግ ነው።

ተቋማቱ የራሳቸውን የግል ኔትወርክ እንዲያደራጁ ያስችላቸዋል፤ መረጃን ለማጋራት እንዲሁም በቅርንጫፎች ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የመረጃ ቴክኖሎጂ ስርዓቶችን በመደበኛ ወይም በተንቀሻቃሽ አማራጮች መተግበር ያስችላል።

አገልግሎቱ የሞባይል ኔትዎርክ ሽፋን ተደራሽ በሆነባቸው እና የዳታ አገልግሎትን በሚሰጡ በሁሉም ኢትዮጵያ ክፍሎች ይገኛል።

ኢትዮ-ቴሌኮም የቪፒኤን አገልግሎቶች በሁለት አማራጭ የሚያቀርብ ሲሆን እነዚህም " የሞባይል ብሮድባንድ ቪፒኤን " እና " የፊክስድ ብሮድባንድ ቪፒኤን " ናቸዉ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ድርጅቱ " ይህ የተለየ የቪፒኤን አይነት ነው። " ያለ ሲሆን " የተንቀሳቃሽ ስልክ ኔትዎርክ ሽፋን ባለባቸው አካባቢዎች ነገርግን ግን መደበኛ ባለገመድ መስመር ተደራሽነት ባሌለባቸው አካባቢዎች ልክ እንደ #ባንክ ያሉ የድርጅት ደንበኞች ቅርንጫፎቻቸውን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ለማገናኘት የሚረዳ የግል መዳረሻ አውታር ሆኖ እንደ አማራጭ የቀረበ ነው።  " ሲል አስረድቷል

የሞባይል ቪፒኤን / VPN / ጥቅል ዋጋ ማሻሻያ የሚመለከተውም ይሄን ነው ብሏል።

Credit : #EthioTelecom

@tikvahethiopia