TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ምርጫ2013

የቁሳቁስ ስርጭትን በተመለከተ በተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ ሰማያዊ ሳጥኖች ተከፍተው መገኘታቸውን ምርጫ ቦርድ አሳወቀ።

ሳጥኖቹን ከፍተው የተገኙበት ምርጫ ክልሎች ላይ አንዳንዶቹ ወደወንጀል ምርመራ ሲላኩ አንዳንዶቹ #ምርጫ_እንዳይካሄድ ተወስኖባቸዋል።

- ደንቢያ የምርጫ ክልል ሰማያዊ ሳጥኖቹ ተከፍተው ፤ ውስጣቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶችን የሚያሳየው የቡክሌት ተከፍቶ ውስጡ ያለውን ነገር አይተው ተገኝቷል፤ በዚህ ምክንያት 3 አስፈፃሚዎች ላይ ምርመራ እንዲደረግ ለፌዴራል ፖሊስ ደብዳቤ ተፅፏል።

ደምቢያ ምርጫ ክልል የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶችን መነካካት ፣ መክፈት በጥብቅ የተከለከለ የወንጀል ተግባር በመሆኑን አስፈፃሚዎች ምርመራ እንዲደረግባቸው ተልኳል።

በደምቢያ ምርጫ ክልል ምርጫው #አይካሄድም

- ተውለደሬ 1 እና 2 ሰማያዊ ሳጥን ተከፍቶ ውስጡ ያሉእጩዎች እነማን እንደሆኑ ፣ የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ ያሉትን እጩዎች የማየት (ፓርቲዎች ቅሬታ አለን ስላሉ ነው እዩ ተብለን ነው) በሚል ተክፍቶ ታይቷል።

በዚህ ምክንያት ተውለደሬ 1 እና 2 ነገ ድምፅ አይሰጥም፤ ታግዷል።

- ግንደበረት (ኦሮሚያ) ነገ ድምፅ #አይሰጥም ፦ ድምፅ የማይሰጥበት ምክንያት የድምፅ መስጫ ወረቀት እና ቁሳቁስ ስለተከፈተ ሳይሆን የአስፈፃሚዎች እጥረት ነበር። ከዚህ ውጭ ግን ወረዳው አስፈፃሚዎችን አሰልጥኖ ለማስፈፀም ለማሰማራት ሲል በመገኘቱ ገንደበረት ላይ ድምፅ አይሰጥም

- ነገሌ ምርጫ ክልል (ጉጂ-ኦሮሚያ) ፦ በምርጫ ክልሉ የሚወዳደር የግል ተወዳዳሪ በምርጫ መስጫ ወረቀቱ ላይ ዝርዝሩ ባለመካተቱ ባቀረበው ቅሬታ መሰረት ቦርዱ ምርጫውን ወደ ጳጉሜ 1 አዛውሮታል።

#TikvahEthiopia #SolianaShimeles

@tikvahethiopia