TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቀበሮሜዳ

" 97 በመቶ የምንሆነው ሰፈራ እንዲሰጠን ብንጠይቅም ያለፍላጎታችን ወደ ነበርንበት ቦታ እንድንመለስ እየተገደድን ነው " - ቀበሮ ሜዳ የሚገኙ ተፈናቃዮች

" አንመለስም ካሉ ማንም አያስገድዳቸውም እኛ ግን እርዳታ አናቀርብም " - የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ

በጸጥታ ችግር ከኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን አዘዞ ክፍለ ከተማ አካባቢ ቀበሮ ሜዳ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች፣ " 97 በመቶ የምንሆነው ሰፈራ እንዲሰጠን ብንጠይቅም ያለፍላጎታችን ወደ ነበርንበት ቦታ እንድንመለስ እየተገደድን ነው " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል አማረዋል።

የመጠለያ ካምፑ አስተባባሪ አቶ መላሽ ታከለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ገለፃ ፤ " ከኦሮሚያና ከሁመራ፣ ማይካድራ ያሉ ሰዎች ' ትመለሳላችሁ የሚል ነገር አለ ' የሰማነው ውይይትም የለም። ' ስንሄድ መሠረታዊ ፍላጎቶች ቅድሚያ መሟላት አለባቸው ' የሚል ሀሳብ ነው ያለው ከተፈናቃዮቹ " ብለዋል።

የማኅበረሰቡ ፍላጎት ምን እንደሆነ ለማወቅ፦ አይ.ኦ.ኤም (IOM)፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በካምፑ ጥናት አድርገው እንደነበር የገለጹት አስተባባሪው፣ " ማኅበረሰቡ አንድ ቦታ ላይ ሰፍረን ሰርተን እንቀየራለን የሚል ፍላጎት ነበረው፣ እንዲያውም ከ100ው 97 ፐርሰንቱ ሰፈራ ፕሮግራም ነው መርጦ የነበረው " ሲሉ አረጋግጠዋል።

ቀበሮ ሜዳ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች ላነሱት ቅሬታ ምን ምላሽ እንዳላቸው ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የአማራ ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን ለገሰ፣ " እነዚህ ሰዎች እንዲመለሱ ውይይት ጀምረናል፤ አንመለስም ካሉ ማንም አያስገድዳቸውም እኛ ግን እርዳታ አናቀርብም " ብለዋል።

" ምክንያቱም የእነዚህ ሰዎች መሬታቸው፣ ቤታቸው፣ ማኅበራዊ መሠረታቸው ያለው ከተፈናቀሉበት አካባቢ ነው። መንግሥት ጊዜያዊ ድጋፍ ነው የሚያደርገው፣ የትኛውም ድጋፍ ቋሚ አይደለም። ይሄ ተያይዞ ክልሉንም ሰዎቹንም ወደ ድህነት የሚወስድ ስለሆነ በቀጣይ እነዚህ ሰዎች አምነው ወደመጡበት ቄዬ ይመለሳሉ " ሲሉ አክለዋል።

ከትግራይ ክልል ከመቐለ ፣ ከሽሬ ፣ ከዓዲግራት፣ ከዓድዋ የመንግሥት ሠራተኞችን ጨምሮ የተፈናቀሉ አሉ ያሉት አቶ ወንድወሰን፣ " ወደዛ የሚሄዱትን በተመለከተ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር በቀጣይ መነጋገር ይጠይቃል " ነው ያሉት።

ምክትል ኃላፊው አክለው ፣ " ከወልቃይትና  ከሁመራ የተፈናቀሉት በጦርነቱ ወቅት ከሞት የተረፉ ስልሆኑ ችግሩ ዳግም የሚመለስ እየመሰላቸው ወደዛ መሄድ ትንሽ ያዝ ያደርጋቸው ካልሆነ በስተቀር ቀጠናው አስተማማኝ ነው " ብለዋል።

ቀበሮ ሜዳ መጠለያ ካምፕ ያሉ ተፈናቃዮች ያወያያቸው አካል እንደሌለ በገለጹት መሠረት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአቶ ወንድወሰን እውነታው ምንድን ነው ? ሲል ላቀረበው ጥያቄ ፤ ተፈናቃዮች ያሉባቸው ካምፖች ብዙ ከመሆናቸው አንፃር ገና ቀበሮ ሜዳ እንዳልሄዱ፣ በዕቅዱ መሠረት እንደሚሄዱ፣ በደብረ ብርሃን፣ ሰሜን ሸዋ መጠለያ ጣቢያዎች ተፈናቃዮችን ማወያየት እንደጀመሩ፣ ተፈናቃዮችም በአፋጣኝ ለመመለስ ፈቃደኛ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ወደ ኦሮሚያ ክልል ተመለሱ ተብለናል ያሉ ተፈናቃዮችን ቅሬታ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያም፣ ከኦሮሚያ ክልል አኳያ ያለውም እነዚህ ሰዎች የተፈናቀሉበት አካባቢ የጸጥታ ኃይሉ ተጠናክሮ፣ አካባቢው ከሸኔ ጸድቶ ከሆነ፣ ተፈናቃዮቹ እንደሚመለሱ ነው የገለጹት።

መረጃው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተጠናቅሮ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
#ለጥንቃቄ

የተከሰተው ጉንፋን መሰል በሽታ በከፍተኛ ሁኔታ የመሰራጨት ባህሪ ስላለው በመከላከያ መንገዶች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል ሲል የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ አሳስቧል።

ቢሮው ምን አለ ?

- በከተማው በተለይ ከጥቅምት ወር መጀመሪያ ጀምሮ በብዙ ሰዎች ላይ ጉንፋን መሰል በሽታ ተከስቷል።

- ይህ ወቅታዊና በየዓመቱ ከቅዝቃዜ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሲሆን፤ በወረርሽኝ መልክ የሚገለጽ አይደለም።

- የተከሰተውን የቫይረስ አይነት ለመለየት ከትምህርት ቤቶች፣ ጤና ተቋማት እንዲሁም ከፍተኛ መተላለፊያ በሆኑ ቦታዎች ላይ ከሚገኙ ከ178 ሰዎች ናሙና ተወስዶ ምርመራ ተደርጓል። በዚህም 17 በመቶ በላይ የኢንፍሉዌንዛ ቫይረስ እና 3 በመቶ የሚሆነው ከኮቪድ-19 ቫይረስ ጋር የተገናኘ መሆኑ ተረጋግጧል።

- ይህ ህመም በተለይም እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት ላይ የሚከሰት ሲሆን፤ ከመቶ ሰዎች መካከል ሃያ የሚሆኑት ላይ ይስተዋላል።

ምልክቶቹ ፦

° ከፍተኛ ራስ ምታት፣
° ሳል፣
° ከአፍንጫ ብዙ ፈሳሽ መውጣት፣
° ጉሮሮን የማቃጠል ስሜት፣
° ጡንቻ አካባቢ ህመም፣
° የድካም እና የምግብ ፍላጎት መቀነስ የመሳሰሉት ናቸው።

- ምልክቶቹ ሲታዩ ወደ ህክምና ተቋም በመሄድ እራስን ከከባድ ህመም መከላከል ያስፈልጋል።

- በበሽታው የተያዙ ሰዎች አፋቸውን እና አፍንጫቸውን ሳይሸፍኑ ሲያስሉ ወይም ሲያስነጥሱ እንዲሁም ቫይረሱ ያረፈባቸውን ነገሮች ከነኩ በኋላ አፍን፣ አፍንጫ ወይም ዓይንን መንካት ቫይረሱ እንዲሰራጭ የሚያደርጉ መንገዶች ናቸው።

የመከለከያ መንገዶች ምንድናቸው ?

ትምህርት ቤቶች እንዲሁም ሰው በተሰበሰበበት ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ፣

በሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ውስጥ መስኮቶችን መክፈት፣

የእጅን ንፅህና በአግባቡ መጠበቅ

በንክኪ ወቅት እጅን በመታጠብ በሽታውን በቀላሉ መከላከል ይቻላል።

* በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ የመሰራጨት ባህሪ ስላለው በመከላከያ መንገዶች ላይ ትኩረት ማድረግ ያስፈልጋል።

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ምንድነው ?

በበሽታው የተያዙ ሰዎች ህክምናው ከቤት የሚጀምር ሲሆን ህመሙን ለመከላከል እና ለማስታገስ ፦
በቂ እረፍት መውሰድ፣
ፈሳሽና ትኩስ ነገሮች መጠቀም
በአካባቢው በቂ የአየር ዝውውር እንዲኖር ማድረግ ከዚህ በተጨማሪ ተገቢውን ህክምና በማግኘት ስርጭቱ እንዳይስፋፋ ማድረግ ይገባል።

#ማሳሰቢያ ፦ በሽታው ከአንድ ሳምንት በላይ የሚቆይ ከሆነ በአቅራቢያው ወደሚገኝ የህክናምና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን አገልግሎትና የጤና ባለሙያዎች ምክረ ሃሳቦች ማግኘት ይገባል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
እስከ 1 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንዲሁም ከማስያዣ ነጻ እስከ 5 ሚሊየን ብር ለማግኘት ይህ እድል እንዳያመልጥዎ !

የታታሪዎቹ/ቀጠሌዋን የሁለተኛ ዙር የአዋሽ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር በበርካቶች ጥያቄ መሠረት ምዝገባው እስከ ህዳር 30, 2016 ዓ.ም መራዘሙን እየገለጽን በኦንላይን ለማመልከት የታታሪዎቹ ድህረ ገጽ ማስፈንጠሪያን 👉 https://tatariwochu.awashbank.com በመጫን ፣ ወይም በአካል በየትኛውም የአዋሽ ባንክ ቅርንፍ በመሄድ ማመልከት ይችላሉ። በተጨማሪ ከዚህ በታች በአማራጭነት በ3 ቋንቋ የቀረቡትን የመመዝገቢያ ፎርም በቀላሉ በመሙላት ለውድድሩ ማመልከት ይችላሉ፡፡

ለእንግሊዘኛ ማመልከቻ:- https://formfacade.com/sm/4W_WcxfNq
ለአፋን ኦሮሞ ማመልከቻ:- https://formfacade.com/sm/ABVPRxLmh
ለአማርኛ ማመልከቻ:- https://formfacade.com/sm/KWWld-W-v

ሰዓቱ ከማለቁ በፊት በድረ-ገፃችን ላይ ኦንላይን እንድትያመለክቱ መልዕክታችንን እናስተለልፋለን።

(አዋሽ ባንክ)
#SafaricomEthiopia

ካርዳችን አለቀ ብለን አንጨናነቅ! ወደ *711# በመደወል የሳፋሪኮምን የአየር ሰዐት የብድር አገልግሎት እናግኝ ፤ አብሮነታችንን እናጠንክር።

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/SafaricomET
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/safaricomet/
ትዊተር- https://twitter.com/SafaricomET
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/safaricom-ethiopia/ 
ቴሌግራም- https://publielectoral.lat/Safaricom_Ethiopia_PLC
  
#FurtherAheadTogether
#NBE

ብሔራዊ ባንክ " ሪፖርተር ጋዜጣ " ላይ ወጥቷል ባለው አሳሳች ዘገባና አሉባልታ ምክንያት በዋጋ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም ሰው ሠራሽ #ጭማሪ ተቀባይነት የለውም፤ ጥብቅ ክትትልም ይደረጋል ብሏል።

ብሔራዊ ባንክ ምን አለ ?

-  በጋዜጣዊ በህዳር 23/2016 እትም ብሔራዊ ባንክ ባለፈው ሳምንት የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማ የፕላን፤ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ከአንድ የፓርላማ አባል ቀረበ ከተባለ አስተያየት ላይ ተነሥቶ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ተመን ላይ በቅርብ ጊዜና በከፍተኛ ደረጃ ለውጥ ለማድረግ ማቀዱን በማስመልከት የወጣው ዘገባ ፈጽሞ ሐሰተኛና አሳሳች፣ ከጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ያፈነገጠ ድርጊት ነው ብሏል።

- " ለፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ጉዳዮን በተመለከተ የቀረበ ዕቅድ የለም " ሲል ገልጿል።

- እስከ 4 ስዓት በፈጀው ውይይት ወቅት በብሔራዊ ባንክ የተነገረ ነገር እንደሌለ ህብራተሰቡ መረዳት አለበት ብሏል።

- በዚህ አሳሳች ዘገባና አሉባልታ ምክንያት በዋጋ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም ሰው ሠራሽ ጭማሪ ተቀባይነት የለውም ጥብቅ ክትትልም ይደረጋል ብሏል።

በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣው ዘገባ ምን ይላል ?

- ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊውና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን ሰፊ የውጭ ምንዛሪ ተመን ልዩነት #በ95_በመቶ ለማጥበብ ዕቅድ መያዙ መታወቁ ፤ ይህ ዕቅድ ግን መቼና እንዴት እንደሚፈጸም የታወቀ ነገር እንደሌለ ያስረዳል።

- ይህ ባንኩ ዕቅድ የተሰማውም ኅዳር 19 ቀን 2016 ዓ/ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የበጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የብሔራዊ ባንክን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድና የመጀመርያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት ነው ብሏል።

- ብሔራዊ ባንክ ይህንን ዕቅዱን በቋሚ ኮሚቴው የግምገማ መድረክ ላይ #በይፋ_ባያቀርብም፣ ለቋሚ ኮሚቴው የቀረበን #ሰነድ የተመለከቱ አንድ የም/ ቤት አባል፤ ዕቅዱን ከሪፖርቱ ላይ እንደተመለከቱ ጠቅሰው ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

የም/ቤቱ አባሉ ምን አሉ ?

" ብሔራዊ ባንክ በሕጋዊው የውጭ ምንዛሪ ተመንና በጥቁር ገበያው መካከል ያለውን ልዩነት በ95 በመቶ የማቀራረብ ዕቅድ ይዟል።

ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በሕጋዊው የምንዛሪ ተመንና በጥቁር ገበያው መካከል ያለው ልዩነት እጥፍ ነው።

ስለዚህ ልዩነቱን በ95% ለማጥበብ የተያዘው ዕቅድ በተጨባጭ የሚቻል ነው ወይ ? ወይስ ዲቫሉዌሽን ለማድረግ (የብርን የመግዛት አቅም ለማዳከም) አስባችኋል? " ሲሉ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

- የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ አቶ ማሞ ምሕረቱ፤ "እንደየ ሁኔታው እየተመዘኑ የሚወሰዱ ዕርምጃዎች ይኖራሉ እንጂ በዚህ ወቅት ይህ ዕርምጃ ይወሰዳል ብሎ ብሔራዊ ባንክ ሊናገር አይችልም "  የሚል ምላሽ መስጠታቸው በጋዜጣው ላይ ሰፍሯል።

- አቶ ማሞ " የውጭ ምንዛሪ ጉዳይን በተመለከተ ሁሉን ነገር እዚህ መናገር አልችልም። ብሔራዊ ባንክን በሚመለከቱ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ የምናደርገው ውይይት ተገቢ ላልሆነ ስፔኩሌሽን (ግምት) የሚያጋልጥ መሆን የለበትም። ገና ጥናት ያልተደረገበት ጉዳይ ላይ ብንወያይም ትርጉም የለውም። ዋናው ቁልፍ ነገር ዓላማችን ላይ መወያየት ሊሆን ይገባል። የባንኩ ዋና ዓላማ የተረጋጋ የዋጋ ሁኔታና የተረጋጋ የውጭ ምንዛሪ ሥርዓት እንዲኖር ማስቻል ነው " ማለታቸውንም ጋዜጣው አስፍሯል።

ብሔራዊ ባንክ ይህን ዘገባ ነው #አሳሳችና #አሉባልታ ነው ያለው።

$ በአሁኑ ወቅት የዶላር ሕጋዊው የውጭ ምንዛሪ ተመን 55.5 ብር የደረሰ ሲሆን፣ በጥቁር ገበያው ግን አንድ ዶላር እስከ 110 ብር እየተመነዘረ ይገኛል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ድርቅ #ትግራይ

" ከምበላባቸው ቀናት #ጦሜን የማድርባቸው ቀናት ይበዛሉ " - የሰንዓለ ነዋሪ

" በድርቅ ምክንያት 6 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ ... 89 ከመቶ ነዋሪ በከባድ የደርቅ አደጋ ላይ ይገኛል " -  ዒስራ ዓዲ ወጀራት ወረዳ

በትግራይ ደቡባዊ ምስራቅ ዞን ዒስራ ዓዲ ወጀራት ወረዳ ባጋጠመው ድርቅ ምክንያት 6 ሰዎች መሞታቸውን የወረዳው የኢኮኖሚ ዘርፍ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

ፅ/ቤቱ ፤ በወረዳው ቀበሌ ገበሬ ማህበራት ያጋጠመው ድርቅ በጊዜው ካልተገታ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል ሲል አስጠንቅቋል።

ወ/ሮ ኣልጋነሽ ከበደ በወረዳው የሰንዓለ ነዋሪ የእድሜ ባለፀጋ ናቸው።

ወ/ሮ ኣልጋነሽ ፤ ከማሳቸው የሚያገኙት ገቢ ከአመት አመት ስለማይመግባቸው ድሮውኑ በሴፍትኔት እገዛ ሲተዳደሩ ነበር።

በጦርነቱ ምክንያት የሴፍትኔት አገልግሎት በመቆሙ የዘንድሮ ድርቅ መቋቋም አቅቷቸዋል። በዛ ላይ አህታቸው በረሃብ ምክንያት በመሞትዋ ሁለት ልጆችዋን የመንከባከብ ሃላፊነት በእሳቸው ላይ ወድቀዋል።

ወ/ሮ ኣልጋነሽ ችግሩ የሚይዙት የሚጨብጡት አሳጥቷቸው ከሚበሉባቸው ጦማቸው የሚያድሩባቸው ቀናት እንደሚበዙ ተናግረዋል።

ከወረዳዋ ሰንዓለ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ብቻ ድርቅ ባስከተለው ችግር ቄያቸው ጥለው ከተሰደዱ 40 የቤተሰብ አስተዳዳሪዎች አንድዋ ወ/ሮ ፎቴን ኣባዲ ናቸው።

በድርቁ ምክንያት ከማሳቸው ያገኙት ገቢ ባለመኖሩ ፣ በዛ ላይ ከምግባረ ሰናይ ተቋማትና መንግስት የሚሰጥ እርዳታ በመቆሙ ቤታቸው ቆልፈው እግራቸው ወደ መራቸው ተሰደዋል። 

ድርቅ ባስከተለው ረብ አስከአሁን 6 ሰዎች መሞታቸው የሚገልፁት የወረዳው የኢኮኖሚ ዘርፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሃሪፈያ ግደይ ፤ የወረዳው 89 ከመቶ ነዋሪ በከባድ የደርቅ አደጋ ላይ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።  

የምግባረ ሰናይ ድርጀቶች የፌደራልና የክልሉ መንግስታት ችግሩ በመረዳት ቶሎ እንዲደርሱ ጥሪ ያቀረቡት ሃላፊዋ ፣ በተለይ እናቶችና ህፃናት ታሳቢ ያደረገ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲደረግ ማሳሰባቸውን የትግራይ ቴሌቪዥንን ዋቢ በማድረግ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በትግራይ ያጋጠመው ደርቅ የሚመለከት ተከታታይ መረጃዎችን በማቅረብ ላይ ሲሆን ፤ በክልሉ ምስራቃዊ ዞን ሶስት ወረዳዎች ባጋጠመ የድርቅ አደጋ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ የመንግስት አካላት መናገራቸውን መዘገቡ ይታወሳል።
                      
@tikvahethiopia            
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሺርካ ✦ " 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ✦ " ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል " - ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ (ለቪኦኤ) ✦ " ጥቃቱን ያደረሰው አሸባሪው ሸኔ ነው " - የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን (ለቪኦኤ) ✦ " እኛ…
#Update

ቤተክርስቲያኗ ዛሬ ባወጣችው መግለጫ በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን አንዳንድ ወረዳዎች በኦርቶዶክሳውያን ላይ የሚፈጸመውን ጥቃት በጥብቅ እንደምታወግዝና የጸጥታ ተቋማትም ጥቃት እንዲከላለሉ ጥሪ አቀረበች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ፅ/ቤት በአርሲ ዞን በሹርካ ወረዳ፦
- በሶሌ ሚካኤል፣
- በዲገሎ ማርያም፣
- በሮቤ እንደቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም አብያተክርስቲያናት ላይ በተለያዩ ጊዜያት 36 ኦርቶዶክሳዊያን በደረሰባቸው ጥቃት ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ገልጿል።

በዚሁ ጥቃት በሶሌ ዲገሉ እና ጢጆ ለቡ በተባሉ ቀበሌዎች 28 ኦርቶዶክሳዊያን ከየቤታቸው #ተለቅመው መገደላቸውን ፤ ከእነዚህ ውስጥ 7ቱ ሴቶችና 21ዱ ወንዶች መሆናቸው መታወቁን አመልክቷል።

በዚህ ጥቃትም እድሜያቸው ከሰባ ዓመት አዛውንት እስከ ሃያ ስምንት ቀን ጨቅላ ሕጻናት እንደሚገኙበት ገልጿል።

#በዛሬው_ዕለት ደግሞ በዲገሉ ማርያም ቤተክርስቲያን 5 ኦርቶዶክሳዊያን መገደላቸውንና የሦስት ኦርቶዶክሳውያን ቤት መቃጠሉን አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም በሮቤ አንዲቶ ደብረ ምጥማቅ ማርያም ቤተክርስቲያን በዓለ ማርያምን አክብረው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ የነበሩ 3 ኦርቶዶክሳዊያን ጨለማን ተገን ባደረጉ ነፍሰ ገዳዮች መገደላቸውን ፅ/ቤቱ አስታውሷል።

የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በተደጋጋሚና ሆን ተብሎ በሚፈጸመው የኦርቶዶክሳዊያን ጥቃት ዙሪያ በጋራ እየሠሩ እንደሚገኙ የገለፀው ፅ/ቤቱ  " በዚህ ዐይነት የጥቃት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አንዳንድ አካላት ላይ በመንግሥት በኩል የማያዳግም #ርምጃ_እንደተወሰደባቸው ሀገረ ስብከቱ በላከው ሪፖርት ማረጋገጡን አመልክቷል።

ይህ ዐይነት ሃይማኖት ተኮር ጥቃት በምእመናን ላይ መድረሱ አግባብነት የሌለውና እምነትን በነጻነት የማራመድ መንግስታዊ መብትን የሚጥስ ነው ያለው ፅ/ቤቱ ፤ መሰል ሕገ ወጥ ጥቃትን ለመከላከልና ሁሉም የሃይማኖት ተቋማት መብቶቻቸውን ተቋማዊ በሆነ መንገድ ማስከበር እንዲችሉ  ያቋቋሙት የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ድርጊቱን በማውገዝ ችግሩ ከመሠረቱ እንዲፈታ ከሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመነጋገር መፍትሔ መፈለግ ሲገባው በዝምታ በማለፉ ቤተክርስቲያን ከፍተኛ ቅሬታ እንደተሰማት ገልጿል።

" ኦርቶዶክሳዊያን ላይ ያነጣጠረ ግድያ እንዲቆምና የወንጀሉ ፈጻሚዎችም ለፍርድ እንዲቀርቡ በሀገረ ስብከቱ ጥረት እየተደረገ ነው " ያለው ጠቅላይ ጽሕፈት ቤቱ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመሆን ፅ/ቤቱም ጉዳዩን የሚከታተለው መሆኑን አሳውቋል።

በሌሎች ስፍራዎች የሚያጋጥሙ ተመሳሳይ ጥቃቶችን በእንጭጩ ለመቅጨትና ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሔ ማበጀት ይቻል ዘንድ አህጉረ ስብከት ችግሮች በሚያጋጥሙ ወቅት በፍጥነት በማሳወቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

የምስራች ለከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች! አፖሎ የሥራ ዕድል ይዞ መጥቷል፤ የአፖሎ አካውንት ሌሎች እንዲከፍቱ ባደረጉ ቁጥር ኮምሽን ተዘጋጅቷል! ከኮምሽን በተጨማሪም የተለያዩ ጥቅሞች ያገኙበታል። አሁኑኑ ፍጠነው ይመዝገቡ!

የተመዘገባችሁ ተማሪዎች፣ መቼ እንደምትጀምሩ ሪፈራል ኮዳችሁን ጨምሮ በአመለከታችሁበት ስልክ ቁጥር/ በSMS አጭር የስልክ መልዕክት እናሳውቃችኋለን፡፡

ማስፈንጠሪያውን በመጠቀም ይመዝግቡ፦https://apolsup.bankofabyssinia.com/studentAgent/

ከአፖሎ ጋር ተፍ ተፍ በሉ!
ከሥራ በፊት ሥራ ጀምሩ!
ጠቀም ያለ የሪፈራል ኮሚሽንም ያግኙ!
TIKVAH-ETHIOPIA
ኔፓል ሀገሪቱ ላይ " ቲክቶክ " እንዲታገድ ወሰነች። ኔፓል ፤ ማህበራዊ መስተጋብርን የሚረብሹና የቤተሰብን መዋቅር እንዲሁም ማህበራዊ ግንኙነቶችን የሚያውኩ ይዘቶችን ለማጋራት ጥቅም ላይ እየዋለ ነው ያለችውን የቻይናውን " #ቲክቶክ " መተግበሪያ እንዲታገድ ውሳኔ አሳለፈች። ሀገሪቱ ፤ " ቲክቶክ " በማህበራዊ መስተጋብር ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ነው ያለች ሲሆን በመተግበሪያው ላይ የሚለቀቁት…
#ቲክቶክ

ለምንድነው ሀገራት " ቲክቶክ " ን ለማገድ እየተንቀሳቀሱ ያሉት ?

ከቅርብ ወራት ወዲህ አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ ካናዳ ያሉ የህግ አውጪዎች ከፀጥታ እና ደህንነት ስጋት ጋር በማያያዝ ግዙፉን የአጫጭር ቪድዮዎች ማጋሪያ " ቲክቶክ " ን ለማገድ / ለመገደብ የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከራቸውን ኒውዮርክ ታይምስ አስነብቧል።

ዋይትሃውስ እኤአ በፌብሩዋሪ 27 የፌዴራል  ኤጀንሲዎች አፕሊኬሽኑን ከመንግሥት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ላይ እንዲያጠፉ 30 ቀናት ሰጥቷቸው ነበር ፤ እንዲሁም ኒውዮርክን ጨምሮ የተለያዩ ከተሞች የመንግሥት ሰራተኞች " ቲክቶክ " ን እንዳያወርዱ ከልክለዋል።

በተጨማሪም ባይደን በሀገር ደረጃ ከሁሉም መሳሪያዎች ላይ መተግበሪያው እንዲታገድ እንዲያደርጉ የድጋፍ እንቅስቃሴዎች ነበሩ፤ አሁንም አሉ።

ለምንድነው መንግሥታት ቲክቶክን ለማገድ የሚንቀሳቀሱት ?

በተለይ ምእራባውያኑ ቀጥታ ጉዳዩን #ከቻይና ጋር ያገኛኙታል።

የምዕራቡ ዓለም የሕግ አውጪዎች እና ተቆጣጣሪዎች " ቲክቶክ " / ባለንብረቱ የባይትዳንስ የተጠቃሚ መረጃዎችን በቻይና መንግሥት እጅ እንዲገቡ ያደርጋል የሚል አቋም አላቸው።

ለዚህም እንደማያሳያ የሚያደርጉት የቻይና መንግሥት ለደህንነት ጉዳይ መረጃዎችን ለማሰባሰብ በሚስጥር ከቻይና ኩባንያዎች እና ዜጎች መረጃዎችን መውሰድ የሚያስችለው ህግ እንዳለው በመግለፅ ነው።

ቲክቶክ መሰል ክሶችን ለረጅም ጊዜ ውድቅ አድርጓል።

- ህንድ በ2020 ላይ ነው ያገደችው።
- የብሪታኒያ ፣ የፈረንሳይ፣ የኒውዝላንድ ፣ የአውስትራሊያ፣ ካናዳ #ፓርላማዎች ከአባላት ኦፊሴላዊ መሳሪያዎች እንዲታገድ አድርገዋል።
-  የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት በተመሳሳይ ከአባላት ኦፊሴላዊ መሳሪያዎች ላይ አግዷል። የወረደውንም አስጠፍቷል።
- ካናዳ የመንግሥት መሳሪያዎች ላይ እንዳይሰራ፣ የመንግሥት ሰራተኞችም እንዳያወርዱት አድርጋለች።
- የዴንማርክ መከላከያ ሰራዊት ሰራተኞቹ በሙሉ እንዳይጠቀሙ አድርጓል። ስልካቸው ላይ ተጭኖ የነበረውንም አስጠፍቷል።
- ኖርዌይ በመንግሥት ሰራተኞች ስልክ ላይ እንዳይሰራ አድርጋለች።

በተጨማሪ ፦

* አፍጋኒስታን #ወጣቶችን ከአጓጉል ነገር ለመጠበቅ በሚል 2022 ላይ አድግዳለች።

* ኪርጊስታን በዚህ ዓመት የሀገሪቱን ባህል ወግ እና ስርዓት እየበረዘው ፣ ለልጆች፣ ለወጣቶች የአእምሮ ጠንቅ ነው በማለት አድጋለች።

* ኔፓል እና ሶማሊያም እንዲሁ እንዲታገድ ከወሰኑ ሀገራት መካከል ናቸው።

አሜሪካ ለማገድ እያደረገች ያለችው እንቅስቃሴ አለ ?

ካለፈው ዓመት ህዳር ጀምሮ እጅግ በርካታ ግዛቶች " ቲክቶክ " ን  ከመንግስት መሳሪያዎች አግደዋል።

የዩኒቨርሲቲዎች ለምሳሌ ፦ እንደ ቴክሳስ ፣ ኦውበርን ፣ ቦይስ ስቴት ዩኒቨርሲቲዎች አፕሊኬሽኑ #በዋይፋይ እንዳይሰራ አድርገው አግደዋል።

አሜሪካ ውስጥ ከደህንነት ጋር በተያያዘ ብቻ ሳይሆን ቲክቶክ ሱስ የሚያሲዝ እንደሆነና ወጣቶችን እና ህፃናት ልጆችን አሉታዊ ተፅኖ ያሳድራል በሚል የሚከሱ ግዛቶችም አሉ።

ኮንግረሱ ቲክቶክ እንዲታገድ ይፈልጋል ? እንዲታገድ የሚፈልጉ የኮንግረሱ አባላት አሉ። (ከዚህ ቀደም የቀድሞው ፕሬዜዳንት ትራምፕ የማገድ እንቅስቃሴን እንዲቆም መደረጉ ይታወሳል)

ምንም እንኳን አሜሪካ ውስጥ በመንግሥት መሳሪያዎች ላይ እንዲሁም በአንዳንድ ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች ዋይፋይ ቲክቶክ ቢታገድም 150 ሚሊዮን ነው ተብሎ ከሚገመተው ተጠቃሚ ላይ እንዲታገድ ለማድረግ ረጅም ሂደት ሊጠይቅ እንደሚችል በዘርፉ ላይ ያሉ ፀሀፊዎች ይናገራሉ።

" ቲክቶክ " በየጊዜው የሚነሱበትን በተለይም የደህንነት እና የቁጥጥር ክሶች ውድቅ ሲያደርግ ቆይቷል።

@tikvahethiopia