TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሱዳን የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ እና ሱዑዲ አረቢያ አደራዳሪነት የተኩስ ማቆ ስምምነት ላይ ማድረሳቸው ቢነገርም እንደ ከዚህ በፊቶቹ ስምምነቶች ሁሉ ተጥሶ ካርቱም ትላትናም በፍንዳታ ስትናጥ መዋሏን ቪኦኤ ዘግቧል። የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ከሰኞ ምሽት ለአራት ሩብ ጉዳይ ይጀምራል የተባለና ለሰባት ቀናት የሚቆይ ነበር። ተኩስ ኡቅም ላይ ተደረሰ በተባለ በደቂቃዎች ውስጥ…
#Update

" ከዚህ ቀደም የተደረሱ የተኩስ አቁም ስምምነቶችን በተደጋጋሚ ተጥሰዋል " በሚል የሱዳን ጦር ከተኩስ አቁም ውይይቱ #ራሱን_ማግለሉ ተነገረ።

የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን የተኩስ አቁም ስምምነቶችን በመጣስ የከሰሰው የሱዳን ጦር በሰላም ንግግሩ ተሳታፊ አንሆንም ማለታቸውን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም በተደረሰው የአጭር ጊዜ የተኩስ አቁም ስምምነት መሰረት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከሆስፒታሎች እና ከመኖሪያ ህንጻዎች ለቀው እንዲወጡ የሚደነግግ ቢሆንም አንዱንም ተግባራዊ አላደረጉም ሲል ጦሩ ወቅሷል።

የተኩስ አቁም ስምምነቱን በተደጋጋሚ በመጣሳቸው ጦሩ እዚህ ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የመንግሥት ባለስልጣን ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

ሰብዓዊ እርዳታን ተደራሽ ያደርጋል ተብሎ ከነበረው የተኩስ አቁም ስምምነት ጦሩ ራሱን ማግለሉንም ሮይተርስ የሱዳን የዲፕሎማቲክ ምንጭን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

በሱዳን ጦር መሪ መሪ አብደል ፈታህ አል ቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይል (አርኤስኤፍ) መሪ ጄነራል መሃመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄምቲ መካከል ጦርነቱ የተቀሰቀሰው ሚያዝያ 7/ 2015 ዓ.ም ነበር።

ጦርነቱ ከጀመረ ጊዜ አንስቶ በሺዎች የሞቱ ሲሆን እጅግ በርካቶች ወደ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ጨምሮ ወደ ሌሎችም ሀገራት ተሰደዋል።

ምንጭ፦ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ሮይተርስ ፣ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
#TechnoMobile

በዓለም ላይ ግንባር ቀደም ከሆኑ የሞባይል ቴክኖሎጂ ብራንዶች አምራች የሆነው ቴክኖ ሞባይል በዛሬው እለት እጅግ ዘመናዊ የሆነውን የሞባይል ቴክኖሎጂ የደረሰበትን የመጨረሻ ግልጋሎቶችን የያዘውን የፋንተም ቪ ፎልድ (Phantom V fold) ሞዴል በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ባዘጋጀው ልዩ ስነስርዓት  አስተዋውቋል።

ቴክኖ ሞባይል የፋንተም ቪ ፎልድ (Phantom V fold) ሞዴል በኢትዮዽያ ገበያ ከመግባቱ አስቀድሞ ስለዚህ ሞዴል ልዩ ግልጋሎቶች ግንዛቤ እንዲያስጨብጥ እና ይዞኣቸው ስለሚመጣው አዳዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂዎች ለማስተዋወቅ በማሰብ ምርቱን የማስተዋወቅ ዝግጅት የኩባንያው ሀላፊዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በታደሙበት ስነስርዓት ምርቱን አስመርቋል።

#ቴክኖ_ሞባይል
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#MyWishEnterprise

DEVELON (ዲቬሎን) የሚለው አዲሱ የዱሳን ስያሜ የ Develop (“ማደግ”) እና Onward (“ወደፊት”) ቃላቶች ውህድ ሲሆን፤ በኮንስትራክሽን ማሽነሪ ዘርፍ ያሳረፍነዉን ትልቅ አሻራ በማጎልበት በጎ ነገሮችን ይዘን “ወደፊት ለማደግ” ያለንን ምኞት ያንፀባርቃል።

• ከአዲሱ የብራንድ ስያሜ ለዉጥ ውጭ ምንም አይነት ውጫዊ ገፅታም ሆነ ውስጣዊ የማሽኑ አካላት ላይ ለውጥ አልተደረገም።
 
• ኦርጅናል መለዋወጫ፣ አስተማማኝ፣ ቀልጣፋና እና ተደራሽነት ያለው የጥገና አገልግሎት መለያችን ናቸው።

ማይ ዊሽ ኢንተርፕራይዝ ኃላ/የተ/የግ/ማ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ https://publielectoral.lat/MYWISHENT 
+251-913-356384  +251-912-710661  +251-910-626917  +251-928-414395
+251-911-606068  +251-922-475851  +251-935-409319  +251-911-602664
" አሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ በማቆማቸው ሳቢያ የምርት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል " - የካማሺ ዞን ነዋሪዎች

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፤ ካማሺ ዞን በመንገድ መዘጋት ምክንያት ከየካቲት ወር ወዲህ መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶች እየገቡ እንዳልሆነ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ነዋሪዎቹ ምን አሉ ?

- በምዕራብ ወለጋ ነጆ መስመር በነበረው የጸጥታ ችግር ስጋት አሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ ያቆሙት በጥር ወር መጨረሻ ነው።

- አሽከርካሪዎች መንቀሳቀስ በማቆማቸው ሳቢያ የምርት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፤ ይህም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተጎድተዋል።

- የጤፍ ዋጋ ከአብዛኛው ኅብረተሰብ የመግዛት አቅም በላይ ሆኗል።

- ሴዳል በሚባል ወረዳ አማራጭ መንገድ ተከፍቶ ቢቆይም ወንዝ በመሙላቱ እና መኪና መሻገር ባለመቻሉ ህዝቡ ለችግር ተጋልጧል።

- በካማሺ ዞን በመንገድ ችግር ምክንያት በተለያየ ጊዜ የምርት ዋጋ መጨመር እና የመድኃኒት አቅርቦት እጥረት ይስተዋላል።

- በህክምና ተቋማት የመድሀኒት እጥረት  አለ።

- ከየካቲት ወር 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ሸቀጥ በነጆ  መስመር እየገባ አይደለም። ከመሠረታዊ  ፍጆታ ምርቶች በተጨማሪም የሰዎች እንቅቃሴም በስጋት ተገድቦ ቆይቷል።

ነዋሪዎችን መንገዱን ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ያለው ችግር እንዲፈታ ጣይቀዋል።

የካማሺ ዞን የኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽሕፈት ቤት ስለ ጉዳዩ ምን ይላል ?

የፅ/ቤቱ ተወካይ አቶ ጀርሞሳ ተገኘ ፦

" ለወራት መሠረታዊ የፍጆታ ዕቃ በነጆ መስመር ወደ ዞኑ አልገባም ፤ የመጓጓዛ አገልግሎትም ተቋጦ ይገኛል።

ይኽ የሆነው ከዚህ ቀደም በምዕራብ ወለጋ ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት ነው።

መንገድ እንዲከፈትና መሠረታዊ የሆኑ ምርቶች እንዲገቡ ከሚመለከታቸው የክልል እና አጎራባች ወረዳዎች ጋር እየተነጋገርን ነው።

ሰብአዊ ድጋፍ ለሚፈልጉ ወገኖች ከረጅም ጊዜ በኋላ በእጀባ በስፍራው ደርሷል። "

በካማሺ ዞን ውስጥ ፦

👉 በ2013 ዓ.ም በነበረው የጸጥታ ችግር ከ140 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለው ነበር።

👉 በአሁኑ ጊዜ ሁሉም ወደየቀያቸው መመለሳቸው ተነግሯል።

👉 በዞኑ ስር አምስት ወረዳዎች የሚገኙ ሲሆን በአራቱ ወረዳዎች የጸጥታ ችግር ተከስቶ ነበር።

Credit ፦ DW Amharic Service

@tikvahethiopia
#ኤርትራ #ሩስያ

የሩሲያ ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን #የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂን በክሬምሊን ቤተ መንግሥት ተቀብለው አነጋገሩ።

የኤርትራ የማስታወቂያ ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል በትዊተር ገጻቸው ባወጡት ቃል ፤ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ እና ፕሬዚደንት ፑቲን ዛሬ ረቡዕ ከቀትር በኋላ ባደረጉት ቆይታ የአገሮቻቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት፤ ዐለም አቀፍ ጉዳዮች እንዲሁም በጋራ ትኩረት በሚሰጧቸው ሁኔታዎች ዙሪያ በስፋት መወያየታቸውን አስታውቀዋል፡፡

አያያዘውም ፤ “የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳይያስ በሩሲያ ፌዴሬሽን ያደረጉት #የመጀመሪያ ጉብኝት ለሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ፕሬዚደንት ፑቲን አስምረውበታል” ብለዋል፡፡

“የሁለቱ ሀገሮች ግንኙነት ርምጃ ሙሉ በሙሉ አመርቂ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ” ፑቲን መናገራቸው አክለው “በመጪው ሐምሌ ወር ሞስኮ በምታስተናግደው ሁለተኛው የሩሲያ እና የአፍሪካ የመሪዎች ጉባዔ ላይ እንዲገኙ ጋብዘዋቸዋል” ብለዋል፡፡

የኤርትራ ፕሬዚደንት በበኩላቸው ጉብኝታቸው የሁለቱን ሀገሮች ከፍተኛ የአጋርነት እና የምክክር ግንኙነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን መናገራቸውን የማስታወቂያ ሚኒስትሩ የማነ ገብረ መስቀል አመልክተዋል፡፡

#ቪኦኤ
ፎቶ፦ የማነ ገ/መስቀል

@tikvahethiopia
ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያዎን
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እና በሲቢኢ ብር በቀላሉ መክፈል ይችላሉ!
******

የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ተጠቃሚ ካልሆኑ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመቅረብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉ ሲሆን፣ የሲቢኢ ብር አገልግሎት መጠቀም ካልጀመሩ ደግሞ፡

• ወደ *847# በመደወል፣ ወይም
• የሲቢኢ ብር መተግበሪያን ከ Play Store ወይም App Store በማውረድ ተመዝግበው የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ ወደ 951 ነጻ የጥሪ ማዕከል ይደውሉ።

የሲቢኢ ብር መተግበሪን ለማውረድ ወይም ለማዘመን (Update) የሚከተሉትን ማስፈንጠሪያዎች ይጠቀሙ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡
https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr

• ለአፕል ስልኮች፡
https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
#ፀደይ_ባንክ

አማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) በሚል ስያሜ ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ ሰፊ መሠረቱን በገጠር አድርጎ ብዙኃኑን የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽና ተጠቃሚ በማድረግ የቆየውና በያዝነው ዓመት መጀመሪያ ላይ ወደ ግዙፍ ባንክነት ያደገው ፀደይ ባንክ አርቲስት ሰሎሞን ቦጋለን የብራንድ አምባሳደሩ አድርጎ ሰይሟል፡፡

ባንኩ በስካይ ላይት ሆቴል  ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ እንዳስታወቀው፥ በበርካታ ፊልሞችና ድራማዎች ላይ በመተወን ታዋቂነት ያተረፈውና በበጎ አድራጎት ሥራው ጎልቶ የሚጠቀሰው አርቲስት ሰሎሞን ቦጋለ፥ በሁሉም ቦታ፣ ሁሉንም ማኅበረሰብ በቅርበትና በልዩነት ማገልገል መለያው የሆነው ፀደይ ባንክን በትክክል የሚወክል መሆኑንና በመልካም ሥነ ምግባሩና ስብዕናው የባንኩ ብራንድ አምባሳደር እንዲሆን በሙሉ እምነት መመረጡን ገልጿል፡፡

አርቲስት ሰሎሞን ቦጋለ በሕዝብ ዘንድ ታላቅ ተወዳጅነትን ያተረፈ አርቲስት ሲሆን በተሰማራበት የጥበብ ዘርፍ ከ68 በላይ ፊልሞችን፣ ከ16 በላይ የመድረክ ቴአትሮችን፣ ከ8 በላይ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማዎችን እና በርካታ የራድዮ ድራማዎችን የተጫወተ ከመሆኑም በላይ ኅብረት ለበጎ በሚል መርሕ በሚያከናውናቸው የበጎ አድራጎት ሥራዎቹ የሚታወቅና በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት በተለያዩ ዘርፎች በርካታ ሽልማቶችን ያገኘ ነው፡፡

የቀድሞው አማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም(አብቁተ)፥ የዛሬው ፀደይ ባንክ ፦

- በ3 ሚሊዮን ብር ካፒታል ነው ጉዞውን የጀመረው። ዛሬ የተጣራ ካፒታሉ ከ11.6 ቢሊዮን ብር በላይ ሆኖ ጠቅላላ ሀብቱም ከ49.7 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡

- በአሁኑ ወቅት ከ13 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ያፈራ ሲሆን በመላው ሃገሪቱ ከ500 በላይ ቅርንጫፎች አሉት።

- ባንኩ ፤ ከ12,270 በላይ ለሆኑ ዜጎች የሥራ እድል ለመፍጠር ችሏል።

- በአዲስ አበባ ከተማ ሰንጋ ተራ አካባቢ ባለ 39 ወለል የዋና መሥሪያ ቤቱን ትልቅና ዘመናዊ ሕንጻ አስገንብቶ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል።
 
@tikvahethiopia
ፎቶ፦ ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ዱባይ አቀኑ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ወደ ተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ሐዋርያዊ ጉዞ ማድረጋቸው ተሰምቷል።

ቅዱስነታቸው ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመሆን በመካከለኛው ምሥራቅ የንግድ እና የቱሪዝም ማዕከል በመባል በምትታወቀው ዐረብ ኢማራት ፦

- በአገልግሎት እና በስደት የሚገኙትን ውሉደ ክህነት ለመባረክ፡

- በአቡዳቢ መንግሥት ለቤተ ክርስቲያን መሥሪያ በተፈቀደው ቦታ ላይ የተሠራውን መቃረቢያ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ለማክበር፤

- በቀጣይ ለሚገነባው አዲስ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንም የመሠረት ደንጊያ ለማኖር ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ ዱባይ አቅንተዋል።

መረጃው የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ፅ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia