TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" የእኛን ጉዳይ ለእኛ ትተው በርከት ያለ ያልሰሩት ጉዳይ ስላላቸው ስራዎቻቸውን #በምድራቸው ላይ መስራት እንዲችሉ አሳስባለሁ " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፤ በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ እየገቡ መፈትፈት የሚፈልጉ ያሏቸውን ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አሳሰቡ።

ይህንን ማሳሰቢያ ያስተላለፉት ትላንት የ " ኮይሻ ፕሮጀክት " አካል የሆነውን የሃላላ ኬላ ሪዞርት ሲመርቁ ባሰሙት ንግግር ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንድነው ያሉት ?

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" ኮሽ ባለ ቁጥር በኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ እየገቡ መፈትፈት የሚፈልጉ ኃይሎች በተለይም ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች ከድርጊታቸው እንዲሰበሰቡ / እንዲቆጠቡ ለማሳሰብ እወዳለሁ።

ኢትዮጵያን በማበጣበጥ፤ በማባላት የሚገኝ ትርፍ እንደሌለ አውቀው የእኛን ጉዳይ ለእኛ ትተው በርከት ያለ ያልሰሩት ጉዳይ ስላላቸው ስራዎቻቸውን #በምድራቸው ላይ መስራት እንዲችሉ የእኛን ጉዳይ ለእኛ መተው እንዲችሉ ማሳሰብ እፈልጋለሁ። "

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የጠቀሷቸው ኢትዮጵያን የማበጣበጥ እና የማባላት ፍላጎት ያላቸው በተለይ ኢትዮጵያውያን ያልሆኑ ኃይሎች የትኞቹ እንደሆኑ በግልፅ ከመናገር ተቆጥበዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በትላንትናው ንግግራቸው ከሰሞኑን የተገደሉት የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ የሺጥላ በሀሳብ ብልጫ ፍላጎታቸውን ማስፈፀም በተሳናቸው አካላት የተገደሉ መሆኑንም ገልጸዋል።

ድርጊቱን የፈፀሙትን ኃይሎች " ጅግና መሳይ ፈሪዎች " ሲሉ የገለጹት ጠ/ሚኒስትሩ ፥ " ይህን አይነት ልምምድ ለኢትዮጵያ አደገኛ ነው ኖረንበታል ከዚህ ቀደም በቀይ ሽብር በነጭ ሽብር የሆነው ይሄ ነው ፤ ሰው ዝም ብሎ መኪና ውስጥ እየሄደ ገድሎ በሰላም መኖር ይቻላል ብሎ ማሰብ ያስቸግራል ፤ ሰው ገሎ ስልጣን ማግኘት ይቻላል ብሎ ማሰብም ያስቸግራል " ብለዋል።

ስልጣንም ሆነ ሌሎች ፍላጎቶችን ለማሳካት ሀሳብ ማመንጨት ፣ ለብዙሃን መሸጥ ሀሳቡ ተቀባይነት ካገኘ ያንን ማስፈፀም ይቻላል ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " በመገዳደል፣ በመሰዳደብ፣ በመናናቅ ለማሳካት የሚፈልግ የፖለቲካ አላማ የከሰረ ፤ ወደ ድል የማይወስድ ነው " ሲሉ ተደምጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በዚህ ጉዳይ ላይ በስም ያልገለጿቸው ባለሀብቶች ፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም በሀገር ውስጥ ያሉ ወጣቶች እንደሚሳተፉ በመግለፅ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አስጠንቅቀዋል። መንግሥታቸውም ህግን የማስከበር ኃላፊነቱን እንደሚወጣም ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" ከግንቦት 1 ጀምሮ ያለ ዲጂታል መታወቂያ ሞተር ማሽከርከር አይቻልም " - የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ያለ ዲጂታል መታወቂያ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር እንደማይቻል የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡

በከተማዋ የሚንቀሳቀሱ የሞተር ብስክሌት ባለቤቶችና አሽከርካሪዎች የመንቀሳቀሻ ፈቃዳቸውን ጂፒ ኤስ ባስገጠሙበት ተቋም የዲጂታል መታወቂያውን እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2015 ዓ.ም እንዲወስዱ ተጠይቀዋል፡፡

ከግንቦት 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሞተር ብስክሌቶች ላይ በሚደረገው ጥብቅ ቁጥጥር ያለ ዲጂታል መታወቂያ በሚንቀሳቀሱት ላይ እርምጃ ይወሰዳል ሲል ኤጀንሲው አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#ethiotelecom

የቴሌብር ሱፐርአፕ መተግበሪያን ሲጠቀሙ ኢንተርኔት ወይም ዋይፋይ ማገናኘት ቢያስፈልግም ምንም አይነት ክፍያ አያስከፍልም

ምን ይሄ ብቻ መተግበሪያን ከ onelink.to/75zfa5 ሲያወርዱ 100 ሜ.ባ ኢንተርኔት ስጦታም ያገኛሉ!

እናስታውስዎ: መተግበሪያውን ሲጠቀሙ ቪ.ፒ.ኤን (VPN) አብርተዉ ከነበረ እባክዎ አጥፍተው ይጠቀሙ

ቴሌብር - እጅግ ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
#UNinEthiopia

በኢትዮጵያ የሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሀገሪቱ እያከናወነ ባለው ስራዎች ላይ የዳሰሳ ጥናት እያከናወነ እንዳለ ገልጾልናል።

ይህ የዳሰሳ ጥናት የኢትዮጵያ ህዝብ ስለ ድርጅቱ ያለውን ግንዛቤ ለመረዳት ከማገዙም ባሻገር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሀገር አቀፍ የልማት ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ለማገዝና የሚጠቀምበትን ስልቶች ውጤታማነት ለመተንተን እና ለመገምገም ያግዛል ብሏል።

👉https://bit.ly/3S5OOSa
#አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ፤ መንግሥት በአማራ ክልል ካሉ ባለድርሻ አካላት ጋር በቀጥታ በመወያየት ለተፈጠሩት ችግሮች እልባት የመስጠት ግንባር ቀደም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳሰበ።

ፓርቲው ፤ በተለይ ለሀገራቸው ሉዓላዊነትና አንድነት በጋራ ተሰልፈው መስዋዕትነት የከፈሉት የአማራ ልዩ ሀይል፣ ፋኖ እና የመከላከያ ሰራዊት አባላት ቅራኔ ውስጥ እንዳይገቡና ለግጭት እንዳይዳረጉ በከፍተኛ ትኩረትና ጥንቃቄ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ብሏል።

" መንግስት የክፉ ቀን አጋሩ ከነበሩትና በእውነትም ከሕዝብና ከሃገር ፍላጎትና ጥቅም በተፃራሪ የመቆም ተሞክሮ፣ ዝንባሌና ታሪክ ከሌላቸው የአማራ ገበሬዎች፣ ወጣቶችና ፋኖዎች ጋር ያልተገባ ግብግብ ውስጥ መግባት የለበትም " ያለው አብን አሁን ያለው ችግር በውይይት እና ምክክር ሊፈታ የሚችል መሆኑን አስገንዝቧል።

በሌላ በኩል ፓርቲው የተለያዩ የፖለቲካ አጀንዳዎቻቸውን በሸፍጥ ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ አካላት ባልተገባ መልኩ የአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ መስለው እንደሚቀርቡ ሊታወቅ ይገባል ብሏል።

አብን ፤ የአማራ ሕዝብ ድንገተኛ ወዳጅ እና ወኪል በመሆን ግጭት ለማስነሳት እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን አመልክቶ ፤ እነዚህ አካላት ይህን ድርጊታቸውን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ አሳስቧል።

የአማራ ሕዝብ እነዚህ አካላት የሚያደርጓቸውን አደንቋሪ የጥፋት ጥሪዎች ፈፅሞ እንዳይሰማ ሲል ፓርቲው አስገንዝቧል።

በተለይ የአማራ ወጣቶች፣ ፋኖዎች እና የልዩ ሃይል አባላት ፦
- የሕዝቡ ሰላም እና ደህንነት እንዳይናጋ፣
- የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች እንዳይሰተጓጎሉ፣
- የልማት ስራዎች እንዳይኮላሹ፣
- በዋናነት ደግሞ ህዝብ ላይ ምንም አይነት አካላዊ እና የህይወት ጉዳት እንዳይደርስ የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊትም በጊዜያዊ ስሜት ሳይገፋ በሆደ ሰፊነት ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ተመሳሳይ ትጋት እንዲያሳይ አብን ጥሪ አቅርቧል።

አብን በመግለጫው ፥ " ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የአማራ ሕዝብ ያሉትን መሰረታዊ ጥያቄዎች እንዲዘነጋና በምትኩ በደራሽና ስሜታዊነት በተጫናቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ እንዲያተኩር የሚገፋፉ እንቅስቃሴዎች፣ ከውስጥና ከውጭ የሚደረጉ የአፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ቅስቀሳዎች ሰለባ እንዳይሆን ህዝባችንና የህዝባችን ወዳጆች ሁሉ አዎንታዊ እገዛ እንድታደርጉ እንጠይቃለን " ብሏል ።

የአማራ ህዝብ ግራ ቀኙን በአግባቡ መዝኖ በስሙ የሚነግዱ ኃይሎችን ይሁንታ ሊነሳቸው እንደሚገባ አብን ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደረገ።

በአዲስ አበባ ከተማ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የዋጋ ማስተካከያው ከሚያዝያ 24 ቀን 2015 ሌሊት 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ግንቦት 30 ቀን 2015 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

በዚሁ መሠረት፡ -

- ቤንዚን 👉 በሊትር 69 ብር ከ43 ሳንቲም ብር

- ነጭ ናፍጣ 👉 በሊትር 71 ብር ከ08 ሳንቲም

- ኬሮሲን 👉 በሊትር 71 ብር ከ08 ሳንቲም

- የአውሮፕላን ነዳጅ 👉 በሊትር 66 ብር ከ60 ሳንቲም

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 57 ብር ከ84 ሳንቲም

- ከባድ ጥቁር ናፍጣ 👉 በሊትር 56 ብር ከ50 ሳንቲም ተደርጓል።

መረጃው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በዓለም ባንክ ድጋፍ በሚከናወኑ 7 ፕሮጀክቶች ላይ ሙስናና ብልሹ አሠራሮች የሚፈጸሙ ቢሆንም በሪፖርት ውስጥ እንደማይካተቱ፣ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ ይህንን ያስታወቀው ሚያዝያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ በዓለም ባንክ ዕገዛ በሚከናወኑ ሰባት ፕሮጀክቶችን በሚመለከት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በነበረው የውይይት መድረክ ነው፡፡

ኮሚሽኑ ምንድነው ያለው ?

- በዓለም ባንክ ድጋፍ ከሚከናወኑ ፕሮጀክቶች የከተማና መሠረተ ልማት፣ የግብርና ዘርፍ፣ የትምህርት ጥራትን ጨምሮ ሌሎችም ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ፡፡

- ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በዓመት ሁለት ጊዜ ሪፖርት ይቀርባል ፤ በዚህም ከሙስናና ብልሹ አሠራሮች #ነፃ መሆናቸው ተጠቅሶ ለዓለም ባንክ ሪፖርት ይደረጋል።

- ኮሚሽኑ የፕሮጀክቶቹን አፈጻጸም በቅርበት በመከታተል ሪፖርት እንዲያቀርብ ከዓለም ባንክ ጋር ስምምነት አለው ፤ በዓመት ሁለት ጊዜ ከሙስናና ከብልሹ አሠራሮች የፀዱ ስለመሆናቸው የማረጋገጫ ሪፖርት ይቀርባል። ይሁን እንጂ ፕሮጀክቶቹ ክፍተቶች አሉባቸው ፤ ሌሎች ድጋፎች እንዳይቋረጡ በማለት ሪፖርቱ ሙሉ በሙሉ ወይም ከእነ ችግሮቻቸው አይቀርብም።

-  የዓለም ባንክ ብድርና ድጋፎችን የሚሰጠው የኮሚሽኑን ሪፖርት እንደ ቅድመ ሁኔታ በመውሰድ ነው።

- ለዓለም ባንክ ሪፖርት ማቅረብ የስምምነት ማሟያ ብቻ አይደለም፤ ገንዘብ ሚኒስቴርም ከባንኩ ለአገር ኢኮኖሚ የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ለማምጣት ጭምር ነው።

- ዓለም ባንክ የኮሚሽኑን ሪፖርት እንደ መሥፈርትነት ይጠቀሜ ፤ ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ከምታገኝባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ነው።

- ዓለም ባንክ ሰባቱ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንዲሆኑ 3.4 ቢሊዮን ዶላር ከ2004 ዓ.ም. ጀምሮ ድጋፍ ያደረገ ቢሆንም፣ በተለያዩ ምክንያቶች የተራዘሙ ፕሮጀክቶችና ሊጠናቀቁ የደረሱ አሉ።

- ፕሮጀክቶቹን በዋናነት የሚያስፈጽሙ ተቋማት ሙስናና ብልሹ አሠራሮች ጥቆማዎችን ለመቀበልና ሪፖርቱን ለመላክ ይዘገያሉ፡፡

- ሙስና ሳይፈጸም በፊት ጥቆማዎች ሲደርሳቸው ለመቀበል ዝግጁ አለመሆናቸውን፣ ሙስናን ለመከላከል ያለመፈለግና ተፈጽሞ ሲገኝ አስተማሪ ዕርምጃ መውሰድ ላይ ተቋማቱ ክፍተት አለባቸው።

- ሰባቱን ፕሮጀክቶች በበላይነት የሚያሠሩ ተቋማት ሙስናና ተያያዥ ጉዳዮችን ሪፖርት በጊዜው አያቀርቡም።

- ኮሚሽኑ ለዓለም ባንክ ሪፖርት ከማቅረብ በተጨማሪ፣ በሙስናና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ የተሳተፉትን ለሕግ ለማቅረብ በርካታ ሥራዎች እየሰራ ነው።

- ፕሮጀክቶቹ ወደ ታች መዋቅር ሲደርሱ በተለያዩ ምክንያቶች በጀቱ ይሸራረፋል።

- ፕሮጀክቱ በታችኛው መዋቅር ላይ በታሰበለት ጊዜ ያለመፈጸም፣ የካሳ ክፍያ በጊዜ ያለ መክፈል ሙስናና ማጭበርበር ወንጀል ላይ የታዩ ግለሰቦች አሉ።

- በተያዘው በጀት ዓመት በ6 ወራት ሪፖርት አፈጻጸም፣ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች ሙስናና ብልሹ አሠራሮች ምክንያት 357 ጥቆማዎች ለኮሚሽኑ ደርሷል። በዚህ ጥቆማ መሠረት ከ4.9 ሚሊዮን ብር በላይ ሊሸሽ የነበረ ሀብት ወደ መንግሥት ካዝና ተመልሷል። ሕጋዊ ዕርምጃም የተወሰደባቸው አሉ። ከእነዚህ ውስጥ 11 ኃላፊዎች አስተዳደራዊ ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል ፤ ስድስቱ በፍርድ ቤት ጉዳያቸው ተይዟል።

Credit : Reporter Newspaper

@tikvahethiopia
#USA

አሜሪካ የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ለማብቃት በተደረሰው ስምምነት መሠረት ውጤታማ ትጥቅ የማስፈታት እና ተያያዥ ተግባራትን ለማጠናቀቅ ተጨማሪ ተቆጣጣሪዎች እንዲሰማሩ ጠየቀች።

ይህንን የጠየቀችው በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት እና በህወሓት መካከል የተደረሰው ስምምነትን ስድስተኛ ወር ምክንያት በማድረግ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤቷ በኩል ባወጣችው መግለጫ ነው።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምን አለ ?

- የሰላማዊ ሰዎችን ጥበቃ እና ውጤታማ ትጥቅ የማስፈታት፣ ታጣቂዎችን የማሰናበት እና ከኅብረተሰቡ ጋር መልሰው የሚቀላቀሉበትን ሂደት የሚከታተሉ ተቆጣጣሪዎች በማሰማራት በስምምነቱ ላይ የተቀመጡ ሃሳቦች መቋጫ ሊያገኙ ይገባል።

- የኤርትራ ጦር እና ከፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት ውጪ ያሉ ኃይሎች ሙሉ ለሙሉ ከትግራይ እንዲወጡ መደረግ እንዲሁም የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የፈጸሙ እና ተሳታፊዎችን ተጠያቂ ማድረግን ጨምሮ ተአማኒ የሽግግር ፍትሕ ሂደት በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ቁልፍ ጉዳዮች ናቸው።

- ባለፉት ስድስት ወራት በስምምነቱ ትግበራ በርካታ አውንታዊ እርምጃዎች ተወስደዋል።

• በትግራይ ተቋርጠው የቆዩ መሠረታዊ አገልግሎቶች መልሰው ሥራ መጀመራቸው፣

• የሰብአዊ እርዳታ ያለገደብ መቅረቡ፣

• ህወሓት ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ማስረከቡ፣

• እስረኞች መፈታታቸው፣

• ሁሉን አካታች የሽግግር ፍትህ ሂደት መጀመር እና በትግራይ ጊዜያዊ መስተዳደር መቋቋሙ የተወሰዱ አውንታዊ እምርጃዎች ናቸው።

በሌላ በኩል ፥ አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከናወነው ስኬታማ የሰላም ሂደት በኦሮሚያ ክልል ሰላም ለማምጣት ዕድል መፍጠሩን አሳውቃለች።

ሀገሪቱ በመንግሥት እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል የተጀመረውን ንግግር አድንቃለች።

ሁለቱም ወገኖች ለሁሉም ተቀባይነት ያለው ስምምነት ላይ ለመድረስ በቅን ልቦና እንዲደራደሩ አበረታታለሁ ብላለች።

@tikvahethiopia
#USEmabssyAA

" የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው ወይም ኢሜይል / ቴክስት የምንልከው ከሚሉ አጭበርባሪዎች ተጠንቀቁ " - በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ

የአሜሪካ ኤምባሲ የዲቪ (DV) 2024 አሸናፊዎች ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ ይፋ ይደረጋል ብሏል ፤ መመልከቻውም ow.ly/9E7A50O7plm መሆኑን ገልጿል።

በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ፤ ባሳለፍነው ጥቅምት እና ህዳር ወራት ላይ በበይነ መረብ አማካኝነት የተሞላው የ2024 ድቪ (DV) ሎተሪ አሸናፊዎች መታወቃቸው ይፋ አድርጓል።

የዲቪ (DV) 2024 ማመልከቻ የሞሉ ዜጎች መመረጣቸውን እና አለመመረጣቸውን የፊታችን ቅዳሜ ከሚያዚያ 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ ማወቅ እንደሚችሉ አመልክቷል።

በዲቪ (DV) ሎተሪ ድረገጽ ow.ly/9E7A50O7plm ላይ በመግባት አመልካቾች ያመለከቱበትን ልዩ ቁጥር ወይም ኮድ በማስገባት ማወቅ ይችላሉ ተብሏል።

በሌላ በኩል፤ " የዲቪ (DV) ሎተሪ አሸንፋችኋል፣ ከአሜሪካ ኢምባሲ ነው እምንደውለው / ኢሜይል / ቴክስት የምንልከው "  በሚል የሚያጭበረብሩ አካላት ስለሚኖሩ አመልካቾች እንዲጠነቀቁም ኤምባሲው አሳስቧል።

አመልካቾች ለዲቪ (DV) ሎተሪ ደርሷቸው እንደሆነ ወይም እንዳልደረሳው በራሳቸው እጃቸው ላይ ባለው ሚስጢራዊ ቁጥር በዚህ ድረገፅ ow.ly/9E7A50O7plm ማረጋገጥ ብቸኛው መንገድ መሆኑን ገልጿል።

አሜሪካ በየዓመቱ ከአፍሪካ ፣ እስያ ፣ አውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ፣ ደቡብ አሜሪካ እና አውስትራሊያ 50 ሺህ ሰዎችን በድቪ ሎተሪ ወደ ሀገሯ ታስገባለች።

መረጃው የአል አይን ኒውስ እና በአ/አ የአሜሪካ ኤምባሲ ነው።

@tikvahethiopia