TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" አሁን የመሳሪያ ድምጽ ጠፍቷል፤ የህጻናቱን ድምጽ ደግሞ በትምህርት ቤቶች መስማት እንፈልጋለን " - ያንቲ ሶሪፕቶ

የተመድ የሠብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት (ኦቻ) የሰብዓዊ ምላሽ እቅድ እንደሚያመላክተው በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ገልጿል። ከዚህ ውስጥ 161.4 ሚሊዮን የሚሆነው ለትምህርት የሚያስፈልግ ድጋፍ መሆኑን ነው የገለጸው።

በኢትዮጵያ ላለፉት 2 ዓመታት የዘለቀው ጦርነት በኢትዮጵያ በትምህርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ነው።

መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በትግራይ ክልል ብቻ ከ80 - 90 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ የስደተኞች መጠለያ ሆነዋል፤ ንብረታቸው ተዘርፏል/ወድሟል።

Save the Children የተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት ፕሬዚዳንት ያንቲ ሶሪፕቶ ባላፉት ቀናት በኢትዮጵያ በአፋር እንዲሁም በትግራይ ክልል ተገኝተው በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አከባቢዎች ጎብኝተዋል። ከጉብኝቱ በኋላም ፕሬዝዳንቷ በጉብኝቱ ስለነበራቸው ቆይታ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

ፕሬዝዳንቷ ፥ "በተደረገው የሰላም ስምምነት ደስተኞች ነን። አሁን የመሳሪያ ድምጽ ጠፍቷል፤ የህጻናቱን ድምጽ ደግሞ በትምህርት ቤቶች መስማት እንፈልጋለን" ሲሉ ነው የገለጹት።

አክለውም በጉብኝታቸው ወቅት የደረሰው ውድመት አንዳስደነገጣቸውና "ትምህርት ቤቶችን፤ የጤና ተቋማትን፤ የውኃ መጠጥ አገልግሎቶች በፍጥነት ተመልሰው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ መደረግ አለበት። በእነዚህ ተቋማት የሚሰሩ ሠራተኞችም ወደ ሥራቸው ተመልሰው ደሞዝ እንዲከፈላቸው ማድረግና የወደሙ ንብረቶችን መተካት በቅድሚያ መሰራት ያለባቸው ሥራዎች ናቸው" ሲሉ ገልጸዋል።

የድርጅቱ የትግራይ ክልል ምላሽ ሰጪ ቡድን አስተባባሪ አቶ አታክልቲ ገ/ዮሐንስ ለቲክቫህ በሰጡት ማብራሪያ በክልሉ በኮቪድ እንዲሁም በጦርነት ምክንያት ህጻናት ከትምህርት ገበታቸው ለሦስት ዓመታት የራቁ መሆናቸውን ገልጸው ተማሪዎችን ወደ ትምህርት መመለስ ርብርብ የሚጠይቅ ሥራ መሆኑን አስረድተዋል።

ድርጅታቸው ባለፉት ጊዜያት በመቐለ በሚገኙ የስደተኛ ማዕከላት ህጻናት ከትምህርት እንዳይርቁ በማሰብ 850 ህጻናትን በመንግሥት የትምህርት ሥርዓት መሰረት ከ1ኛ - 3ኛ ክፍል ሲያስተምሩ የቆዩ መሆናቸውን አስታውሰዋል።[ በማዕከላቱ ከ3ኛ ክፍል በላይ ማስተማር አይፈቀድም።]

አቶ አታክልቲ ትልቁ ሥጋት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት መመለስ ብቻ ሳይሆን መምህራንንም ወደ ሥራ መመለስ አስቸጋሪ መሆኑን ያነሳሉ። "ቀደም ብለው የነበሩት መምህራን ወደ ጦር ግንባር፤ ከነበሩበት ቦታ ወደ ሌላ ቦታ እንዲሁም ወደ ሌሎች ቢዝነሶች ውስጥ ስለገቡ መምህራኑን መመለስ አስቸጋሪ ያደርገዋል" ሲሉ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልግ ቢገለጽም ድጋፉን በቀላሉ ማግኘት ግን እንደማይቻል ከዚህ ቀደም የነበሩ ሪፖርቶች ገላጭ ናቸው። የፕሬዚዳንቷ ጉብኝትም ድርጅቱ የሚያስፈልገውን ኃብት ለማሰባሰብ ተጽኖ ለመፍጠር የታቀደ ለመሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ኢትዮጵያ ውስጥ የቴሌግራም፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ መሰል የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እስካሁን ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ #ገደብ ከተደረገባቸው አንድ ወር ሊደፍን ነው። የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ " ለምን ገደብ እንደተጣለ " እንዲሁም " ገደቡ መቼ እንደሚነሳ " በየትኛውም አካል በኩል #ለህዝቡ ማብራሪያም ሆነ ገለፃ ያደረገ የለም። ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ…
#ETHIOPIA

ኢትዮጵያ ውስጥ ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ ፣ ዩትዩብ መሰል የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ምክንያቱ ግልፅ ባልተደረገበት ሁኔታ ገደብ ከተደረገባቸው ከአንድ ወር በላይ ተቆጥሯል።

የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ላይ " ለምን ገደብ እንደተጣለ " እንዲሁም " ገደቡ መቼ እንደሚነሳ " በየትኛውም አካል በኩል እስከ ዛሬ ድረስ ለህዝብ ማብራሪያ ሆነ ገለፃ ያደረገ የለም።

ቴሌግራም ፣ ፌስቡክ እና ሌሎችም የማህበራዊ መገናኛዎች በሁለቱም የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢዎች በኩል ተገድበው የሚገኙ ሲሆን ገደቡን በVPN በማለፍ አገልግሎት ማግኘት ይቻላል።

#ትዊተር#ኢንስታግራም መሰል የማህበራዊ መገናኛዎች ገደብ ያልተደረገባቸው ናቸው።

@tikvahethiopia
#ATTENTION

" በድርቅ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተ የፀጥታ ችግር ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ ተጋልጠዋል " - የአማሮ ልዩ ወረዳ

• " ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ ነው " - የቡርጂ ልዩ ወረዳ

በደቡብ ክልል አማሮ እና ቡርጂ ልዩ ወረዳዎች በተከሰተ ድርቅ ምክንያት ከ136 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተገልጿል።

#አማሮ

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የአማሮ ልዩ ወረዳን ዋቢ አድርጎ ባሰራጨው መረጃ ፤ በልዩ ወረዳው ለረጅም ጊዜ ዝናብ ባለመጣሉ በ22 ቀበሌዎች ድርቅ ተከስቷል፡፡

በተከሰተው ድርቅ ምክንያት በልዩ ወረዳው ከ96 ሺህ በላይ ሰዎች አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

በድርቁ ከ3 ሺህ 500 በላይ የቤት እንስሳት በድርቁ ምክንያት መሞታቸው ተገልጿል።

በልዩ ወረዳው የተከሰቱ የፀጥታ ችግሮች የህብረተሰቡን ተጋላጭነት እንዳባባሱት ልዩ ወረዳው አመልክቷል።

በድርቁ እና ለረጅም ጊዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ምክንያት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ በርካት ሰዎች ለአደጋ መጋለጣቸው ተገልጿል።

የክልሉ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በተለያየ ጊዜ እርዳታ ቢያደርግም በልዩ ወረዳው ከከተከሰተው ጉዳት አንፃር ድጋፉ በቂ አለመሆኑን ልዩ ወረዳው አሳውቋል።

#ቡርጂ

የቡርጂ ሶያማ ልዩ ወረዳ በበኩሉ በልዩ ወረዳው በተከሰተው ድርቅ 83 ሺህ 528 ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አሳውቋል።

በልዩ ወረዳው ከ30 ሺህ በላይ እንስሳት መሞታቸውም ተጠቁሟል።

ከምግብ እጥረት ጋር በተያያዘ ህፃናትን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ለረሀብ፣ ለበሽታ እና ለሞት እየተዳረጉ መሆኑ ተገልጿል።

ከክልሉ መንግስት በተጫማሪ የአካባቢው ተወላጆች እና ግለሰቦች እርዳታ ቢያደርጉም በልዩ ወረዳው ከተከሰተው ድርቅ አንፃር የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት በቂ አለመሆኑ ተመላክቷል።

በድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመርዳት እና መልሶ ለማቋቋም ረጂ ድርጅቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው አካላት ትኩረታቸውን ወደ ልዩ ወረዳው እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

#ኮንሶ

በኮንሶ ዞን በተከሰተ ድርቅ ከ800 ሺህ በላይ ዜጎች ለአስቸኳይ ድጋፍ መዳረጋቸውን ዞኑ አሳውቋል።

ለተከታታይ 5 ዓመት የተከሰተው የዝናብ መዘግየት እና እጥረት ባስከተለው ድርቅ ለአስቸኳይ ድጋፍ የተዳረጉት 822 ሺ 526 ዜጎቻችን ናቸው።
 
የተከሰተው ድርቅ ዜጎች ላይ አስከፊ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በችግር ውስጥ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።

Credit : #FBC #SRTA

@tikvahethiopia
#EOTC

ቅዱስ ሲኖዶስ የፊታችን ረቡዕ #አስቸኳይ ጉባኤ ሊያደርግ ነው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ረቡዕ መጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም አስቸኳይ ጉባኤ እንደሚካሄድ ዛሬ አሳውቋል።

በዚህም በአዲስ አበባ አቅራቢያና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት የሚገኙ ሊቃነ ጳጳሳት በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ በቅዱስ ሲኖዶስ አዳራሽ እንዲገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ጥሪ ማስተላለፉን ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopia
#ኤርትራ #ሱዳን

የጎረቤት ሀገር ሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዜዳንት የሆኑት ጄነራል ሞሀመድ ሃምዳን ደጋሎ (ሄመቲ) ዛሬ ሰኞ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ #ኤርትራ፣ አስመራ ማቅናታቸው ተሰምቷል።

ሄሜቲ በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሁሉም መስክ ግንኙነታቸውን ማሳደግና ማጎልበት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ይፋዊ ውይይት ያደርሉ ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #ደቡብ_ሲዳን

የኢፌዴሪ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ዛሬ ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው #ጁባ ሲደርሱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ይፋዊ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ደቡብ ሱዳን የገቡት ለአንድ ቀን የሥራ ጉብኝት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ በዝናብ 🌧 ምክንያት እየተቋረጠ የሚገኘው የሀገራችን ከፍተኛው የእግር ኳስ ውድድር !

የ " ቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ " በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛው የእግር ኳስ ውድድር ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ይህ ውድድር ማዕከሉን በአንድ ስፍራ በማድርግ ነው እየተካሄደ ያለው።

ከሰሞኑን ውድድሩ በ " ድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም " እየተደረገ ይገኛል፤ ነገር ግን ለሶስት ጊዜ ያህል በዝናብ ምክንያት ሜዳው አላጫውት በማለቱ ስለመቋረጡ ታውቋል።

ይሄ ትልቅ ውድድር በDSTV አማካኝነት መላው ዓለም ላይ የሚታይ ነው።

ህዝቧ እግር ኳስ እጅግ በጣም በሚወድባት ሀገር ኢትዮጵያ ያሉት የመጫወቻ ስፍራዎች አብዛኞቹ ደረጃቸውን ያልጠበቁና ለጨዋታ ምቹ ያልሆኑ፣ በተለይ ዝናብ / ክረምት በመጣ ቁጥር የሜዳዎቹ ገፅታ እንደ አንድ ሀገር ዜጋ አንገትን የሚያስደፉ ናቸው።

ተጨማሪ ስፖርታዊ ጉዳዮች ፦ https://publielectoral.lat/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Afar ቀጣይ የአውሳ ሱልጣኔት አልጋወራሽ እንደሚሆኑ የሚጠበቁት ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ በዓለሲመታቸዉን ለመከወን ዛሬ  የአፋር መዲና፣ ሰመራ መግባታቸውን የአፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።     ሱልጣን አህመድ አልሚራህ ሰመራ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመሬሮችና የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የሃይማኖት አባቶች አቀባባል አድርገዉላቸዋል።…
#AFAR

ሱልጣን አህመድ አሊሚራህ 15ኛው የሀውሳ ሱልጣኔት ሱልጣን ሆነው በዓለ ሲመታቸው ዛሬ ተከናወነ።

በበዐለ ሲመቱ ላይ ፦ በርካታ ነዋሪዎች፣ በጅቡቲ እና ኤርትራ የሚኖሩ የአፋር ህዝብ ተወካዮች፣ የአርጎባ ህዝብ አመራሮች ተገኝተው ነበር።

በተጨማሪ ፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ ፣ የአፋር ክልል ርዕሠ መስተዳደር ሀጂ አወል አርባ፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ ከፍተኛ የፌደራል መንግሥት የስራ ሀላፊዎች ፣ አምባሳደሮች በበዓለ ሲመቱ ተገኝተው ነበር።

Photo Credit : Argoba Community Radio

@tikvahethiopia