TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤ በነገው ዕለት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም መካሄድ እንደሚጀምር ተገልጿል። አስቸኳይ ምልዓተ ጉባኤው ከቀናት በፊት በወሊሶ አካባቢ በብፁዕ አባ ሳዊሮስ መሪነት በተፈፀመው ኢ-ቀኖናዊ " የኤጲስ ቆጶሳት " ሢመትን አስመልክቶ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ባደረጉት አስቸኳይ ጥሪ መሠረት የሚካሄድ ነው። በብፁዕነታቸው ጥሪ መሰረት ከእሁድ…
#Update

ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ምእመናን የሦስት ቀናት ጸሎት አውጇል።

ምልዓተ ጉባኤው በነገው ዕለት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የሚሰበሰብ ሲሆን ከቀናት በፊት ቤተክርስቲያን ሕገ ወጥ ስትል በጠራችው ሹመት ዙሪያ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል።

Photo Credit : EOTC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከ / ወደ ትግራይ  የየብስ ትራንስፖርት መቼ ይጀምራል ? ከትግራይ ክልል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች #በቅርቡ የየብስ ትራንስፖርት እንደሚጀምር ከሰሞኑን ተገልጿል። ከአየር ትራንስፖርት በተጨማሪ የየብስ ትራንስፖርት በቅርብ ቀን ለማስጀመር ከፌዴራል መንግስት ጋር በመነጋገር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን የክልል የኮንድትራክሽንና መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በህጋዊ…
#Update

ከ/ወደ ትግራይ የየብስ ትራንስፖርት ለመጀመር የአገር አቋራጭ የሕዝብ ትራንስፖርት ማመላለሻ ማህበራት ዝግጁ እንዲሆኑ መመሪያ መተላለፉ ተሰምቷል።

ሪፖርተር ጋዜጣ ከአገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት ማኅበራት ያገኘሁት ባለው መረጀ ፤ የትራንስፖርት ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ወደ ትግራይ የተለያዩ ከተሞች የሕዝብ ማመላለሻ የትራንስፖርት አገልግሎትን ዳግም ለመጀመር ዝግጁ ሆነው እንዲጠብቁ መመርያ ተላልፎላቸዋል፡፡

በዚሁ የሚኒስቴሩ መመርያ መሠረት ማኅበራቱ ለአባሎቻቸው አገልግሎቱን መልሶ ለማስቀጠል ዝግጁ እንዲሆኑ ያሳወቁ ሲሆን አሁን እየጠበቁ ያሉትም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱን የመጨረሻ ውሳኔ እንደሆነ ለማወቅ መቻሉን #ሪፖርተር_ጋዜጣ ዘግቧል።

ከጥቂት ቀናት በፊት የትግራይ ክልል የኮንስትራክሽንና መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ  ከትግራይ ክልል ወደ ተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች #በቅርቡ የየብስ ትራንስፖርት እንደሚጀምር ማሳወቁ አይዘነጋም።

ቢሮው ከአየር ትራንስፖርት በተጨማሪ የየብስ ትራንስፖርት በቅርብ ቀን ለማስጀመር ከፌዴራል መንግስት ጋር በመነጋገር ኮሚቴ ተቋቁሞ እየተሰራ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopia
Forwarded from Bank of Abyssinia
አፖሎ የተሰኘው ልዩ የዲጂታል መተግበሪያ ለተጠቃሚ ዝግጁ መሆኑን ስንገልጽልዎ በታላቅ ደስታ ነው።
አፖሎን አውርደው ዛሬውኑ ይጠቀሙ።
መተግበሪያውን ለማውረድ ሊንኩን ይጠቀሙ።
https://apollo.bankofabyssinia.com/download-apollo

#Apollo #OurNewProduct #DigitalEthiopia #Ethiopia #technology #innovation #digital #BankofAbyssinia #DigitalEthiopia #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ #The_Choice_For_all #Apollodigitalproduct, #AbyssiniaDigital #Abyssiniabank, #poweredbybankofabyssinia, #thechoiceforall
#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ቡድን ዛሬ ወደ ትግራይ መቐለ እንደሚጓዝ ተሰምቷል።

ይኸው ቡድን 5 አባላት ያሉት ሲሆን በትግራይ ትምህርት ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር ነው ዛሬ ወደ መቐለ እንደሚያቀና ፋና ብሮድካስቲንግ የዘገበው።

በትምህርት ሚኒስቴር  የአስተዳደር እና መሠረተ ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሰለሞን አብርሃ ፤ " ቡድኑ ወደ መቐለ የሚያቀናው በትግራይ ክልል የከፍተኛ እና አጠቃላይ ትምህርትን ለማስጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ለመምከር ነው " ብለዋል።

የሥራ ኃላፊዎቹ ቡድን በመቐለ ቆይታው ከመቐለ እና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች ጋር ትምህርት ዳግም መጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚመክር ገልፀዋል።

በተጨማሪ በትግራይ ክልል አጠቃላይ ትምህርትን ዳግም ለማስጀመር በሚቻልበባቸው ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደሚደረግ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም የባለሙያዎች ቡድን ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ አቅንቶ በዩኒቨርሲቲው ዳግም የመማር ማስተማር ሥራ እንዲጀመር በሚያስችሉ ሁኔታዎች ላይ ምክክር ማድረጉ መጠቆሙን ፋና ብሮክዳስቲንግ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
#AddisAbaba

ከ2.5 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ሀይሌ ግራንድ አዲስ ባለ 5 ኮከብ ሆቴል በይፋ ስራ ጀመረ።

በመዲናችን አዲስ አበባ በየካ ክፍለ ከተማ ላም በረት መናኽሪያ አካባቢ በ15 ሺህ ካ.ሜ ቦታ ላይ ያረፈውና ባለቤትነቱ የሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገ/ስላሴ የሆነው የሀይሌ ሆቴሎችና ሪዞርቶች ስምንተኛ መዳረሻ " ሀይሌ ግራንድ አዲስ አበባ " ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመሩ ዛሬ ተገልጿል።

2.5 ቢልየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት "ሃይሌ ግራንድ አዲስ አበባ" እ.ኤ.አ ከጥቅምት 01/2022 ጀምሮ በሙከራ ደረጃ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል።

ሆቴሉ ለ450 ሰራተኞች ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ለ120 #አዲስ_ተመራቂ ሰራተኞች ስልጠና በመስጠት ስራ እንዱጀምሩ መደረጉ ተገልጿል።

ሆቴሉ በውስጡ ፦

- 130 ክላሲክ ፤ 14 ስዊት ፤ 12 ፕሪሚየር እና 1 ፕሬዝዳንሻል ባጠቃላይ 175 አልጋዎችን የያዘ 157 ምቹና ሰፊ የመኝታ ክፍሎችን
- 4 ሬስቶራንቶች እና 2 PDR ፤
- 4 ባር፤
- 1pastery & coffe shop፤ 
- 1 የተሟላ የባህል ምግብ አዳራሽ፤
- 8 የስብሰባ አዳራሾች እና 2 ትላልቅ Ballrooms
- የጤና እና የውበት መጠበቂያ ማዕከል
- ጂም እንዲሁም 200 ተሽከርካሪዎችን የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ ስፍራ ይዟል።

ሆቴሉ የተገነባው በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ብቻ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በቀጣይ #ሐምሌ ወር ላይ #የወላይታ_ሶዶው ሆቴል እንደሚመረቅ፤ #የሻሸመኔው ሪዞርትም ጥገና ላይ እንዳለ ተገልጿል።

Tikvah Family (Addis Ababa)

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ት ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካቸው ለስራ ጉብኝት #ሱዳን፤ ካርቱም ገብቷል።

የስራ ጉብኝቱ ለአንድ ቀን እንደሆነ ተገልጿል።   

የሱዳን ሪፐብሊክ የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ጄኔራል አብደል ፈታሕ አል ቡርሃን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ልዑካቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Photo Credit : PMOEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መቼ ይገለፃል ? በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች በሁለት ዙር ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተሰጠው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ይፋ የሚደረግበትን ቀን እየጠየቁ ይገኛሉ። በቲክቫህ ቤተሰብ አባላት የመልዕክት መቀበያ አድራሻም እጅግ በርካታ መልዕክቶች ከውጤት ጋር ተያይዞ ከተማሪዎች እና በተማሪ ወላጆች ደርሶናል። የፈተናው ውጤት መዘግየቱን…
ከ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ ምን አዲስ ነገር አለ ?

እጅግ በጣም በርካታ ወላጆች እና ተማሪዎች " የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ጉዳይ ከምን ደረሰ ? ይፋ የሚደረግበት ቀን ታውቋል ወይ ? " የሚሉ ጥያቄዎችን ካለፈው ሰኞ / ጥር 15 ጀምሮ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መልዕክት መቀበያ @OfficialTikvahethiopiaBot ላይ እያስቀመጡ ይገኛሉ።

የተቀመጡት የወላጆች እና ተማሪዎች ጥያቄ ብዙ መሆናቸውን ተከትሎ እና ተማሪዎችም ያለመደበኛ ትምህርት እያሳለፉ ያሉት ቀናት እጨመረ በመሆኑ ከትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ለማግኘት ጥረት አድርገናል።

ባለፈው ሳምንት ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር " የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቼ ይፋ ይደረጋል ? " ብለን ጠይቀናቸው ፤ ከጥር 15 ጀምሮ ባሉት ቀናት የሚል ምላሽ ሰጥተውን ነበር።

ዛሬ ይህንኑ ጥያቄ በድጋሚ ለትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አቅርበን ውጤት ይፋ ማድረጊያ ቀኑ  " ከነገ እንደማያልፍ " በዚገይ ደግሞ እስከ ቅዳሜ ሊሆን እንደሚችል ጠቁመውናል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ930 ሺ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው መገለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መክፈቻ ጸሎት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል። የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ምእመናን የሦስት ቀናት ጸሎት አውጇል። ምልዓተ ጉባኤው በነገው ዕለት ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የሚሰበሰብ ሲሆን ከቀናት በፊት ቤተክርስቲያን ሕገ ወጥ ስትል በጠራችው ሹመት ዙሪያ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል። Photo Credit : EOTC …
#NewsAlert

ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አሳለፈ።

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በሶዶ ዳጩ ወረዳ ሐሮ ባለወልድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ፦
1ኛ. አባ ሳዊሮስ
2ኛ. አባ ኤዎስጣቴዎስ
3ኛ. አባ ዜና ማርቆስ የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና በመጣስ ባልተሰጣቸው ስልጣን 26 ኤጴስ ቆጰሳትን ሾመናል፤ ሲኖዶስ አቋቁመናል በማለት በማኅህበራዊ እና በብሮድካስት ሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ የተረጋገጠ መሆኑን ገልጿል።

በዚሁ ድርጊታቸውም በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ዓለም የሚኖረውን ሕዝበ ክርስቲያንን በማታለል የክህደት እና የኑፋቄ ተግባር ፈፅመዋል ብሏል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ተግባር እንደሚያወግዝ ገልጾ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ከዲቁና ጀምሮ ያለው ሙሉ ሥልጣነ ክህነት በመሻር አውግዞ እንደለያቸው አሳውቋል።

@tikvahethiopia