TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ETHIOPIA በዩናይትድ ኪንግደም (UK) የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከቢቢሲ " ኒውስ ሀወር " ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ያደረጉት ቃለ ምልልስ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA በዩናይትድ ኪንግደም (UK) የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከቢቢሲ " ኒውስ ሀወር " ጋር በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ያደረጉት ቃለ ምልልስ ! @tikvahethiopia
አምባሳደሩ ምን አሉ ?

" ኤርትራ ችግር ናት ብዬ አላስብም ፤ ህወሓት ነው የቀጠናው ችግር፤ አሜሪካ ግጭቱን በማስቆም ረገድ ግልፅ ከሆነች በህወሓት ላይ ጫና ማሳደር ይገባታል " - አምባሳደር ተፈሪ መለሰ

በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ከቢቢሲ ኒውስ ሀውር ጋር ቆይታ አድርገው የነበረ ሲሆን በዚህም ወቅት አሁን ስላለው ሁኔታ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስቶላቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ፤ የተኩስ አቁሙ ከታወጀ በኃላ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶች ወደ ትግራይ በየቀኑ ጥሩ በሚባል ሁኔታ እየሄዱ ነበር ብለዋል። በአየር በረራዎችም መድሃኒትን ጨምሮ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች ሲጓጓዙ እንደነበር ገልፀዋል። ይህ ሁሉ ወደ ሰላም ጥረቱ ለማምራት ሲሆን ለዚህ ጥረት ምላሹ ግን  ያ አልነበረም (ሰላም አልነበረም) ሲሉ የነበረውን ሁኔታ አስረድተዋል።

የአሜሪካው የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሃመር በአሁን ሰዓት ኢትዮጵያ እንዳሉ እና ጉብኝታቸውን በተመለከተ የተጠየቁት አምባሰደሩ ...

" ከዚህ በፊትም እዚያው ነበሩ ፤ የአውሮፓ ህብረት እና የዩናይትድ ኪንግደም ልዩ ልዑካንም ኢትዮጵያ ነበሩ ህወሓት /TPLF ወደ ሰላም ጠረጴዛውን እንዲመጣ ለማበረታት። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ገና ከጅምሩም አቋሙ ገልጽ ነው በማንኛውም ቦታ እና ጊዜ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለድርድር ዝግጁ መሆኑን ገልጿል " ሲሉ መልሰዋል።

አሜሪካ፤ ኤርትራ ወደ ግጭቱ ዳግም መግባቷን በመግለፅ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር መስራቷን እንድታቆም እና በኢትዮጵያ በኩል የሚፈፀሙ የአየር ጥቃቶች እንዲቆሙ ጠይቃለች በሚል ለተነሳው ....

" ይህ በቀላሉ እውነት አይደለም። ኤርትራ ሉአላዊ ሀገር ነች ፤ ከህወሀት ጋርም የራሳቸው ታሪክ አላቸው። እንደሚታወቀው ከኤርትራ ጋር ያለውን አለም አቀፍ ድንበር የሚቆጣጠሩት የህወሓት ሃይሎች ናቸው እንጂ የኢትዮጵያ ጦር አይደለም፤ ድንበሩ ለኛ ነው እኛ ግን እየተቆጣጠርነው አይደለም " ብለዋል።

የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ህወሓትን ለመደምሰስ እንደሚፈልግ ተናግሯል በዚህስ ላይ ...

" የኤርትራን መንግስት ወክለን ልንናገር አንችልም። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ ግን እነሱም ህወሓት ወደ ዋና ከተማዋ አስመራ በተኮሳቸው ሚሳኤሎች እና ሮኬቶች ተተንኩሰዋል። (በህወሓት) "

የኢትዮጵያ ወታደሮች ኤርትራ ውስጥ ሰፍረዋል ? በሚል ለቀረበ ጥያቄ ...

" አይ ፤ /No / ፤ ያ መረጃ የለኝም " ሲሉ መልሰዋል።

የኢትዮጵያ ወታደሮች እዛ እንዳሉና ከፕሬዜዳንት ኢሳያስም ትዕዛዝ እንደሚቀበሉ የሚገልፁ ሪፖርቶች አሉ በሚል ለተነሳው ሀሳብ...

" ያን ለማመን ይከብዳል ምክንያቱም ጦራችን #ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለ እንዲሁም በሌሎች የአካባቢው ሀገራት እንደነበረው ለሰላም አስከባሪ ሃይል #ካልተጠራን በስተቀር ወታደሮቻችን ኤርትራ የሚሄዱበት ምንም ምክንያት የለም " ብለዋል።

የኤርትራስ ወታደሮች በኢትዮጵያ ውስጥ አሉ ወይ  ? ለሚለው ጥያቄ ...

" አይ / no / " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በትግራይ ያለው ከበባ እንዲያበቃ በኢትዮጵያ ያሉ የኤርትራ ወታደሮች ይውጡ በሚለው ላይ ምላሹ " የሉም " የሚል ነው ? በሚል ለቀረበው ጥያቄም ...

" ጥሩ ! እኛ እስከሚገባን ምንም አይነት እገዳ የለም። በዓለም አቀፍ ህግ የዓለም አቀፍ ድንበሮቻችንን የመከላከል ኃላፊነት አለብን (መንግስት ኃላፊነት አለበት) ነገር ግን አሁን ላይ ከኤርትራ ጋር ባለው ድንበር ላይ እየተፈጠረ ላለው ነገር ተጠያቂ አይደለንም " ብለዋል።

ለአዲስ የተኩስ አቁም እድል ይኖር እንደሆነ ተጠየቀው ...

" መንግስት እስካሁን በመከላከል አኳኋን ላይ ነው ያለው። በትግራይ ውስጥ ጥቃት እየፈፀምን አይደለም ፤ እስካሁን በመከላከል ላይ ነን ፤ እንዲሁም ህወሓት ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ እንዲመጣ ጥሪ እያደረግን ነው፤  ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህን እንዲያደርግ እናበረታታለን ምክንያቱም በጦርነት ምንም መፍትሄ የለም። " ሲሉ መልሰዋል።

አሜሪካ ኤርትራ ዳግም ወደ ግጭት ገብታለች በሚል ከማውገዟ ጋር ተያይዞ ኢትዮጵያ ባሉት የአሜሪካው ልዩ መልዕክተኛ ምን መልዕክት ደረሰ በሚል ለተነሳ ጥያቄም ...

" ኤርትራ ችግር ናት ብዬ አላስብም ፤ ህወሓት ነው የቀጠናው ችግር። አሜሪካ ይየሶስተኛውን ዙር ግጭት / ጦርነት በማስቆም ረገድ ግልፅ ከሆነች በህወሓት ላይ ጫና ማሳደር ይገባታል። " ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia
አቶ አብይ ኤፍሬም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ አብይ ኤፍሬም በድንገተኛ ህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የ96 ዓመቷ ዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት  በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የንግስቷን ህልፈት ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትምራን ትምራን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ጋር በመተባበር ነገ ሀሙስ " የሴቶች የሰላም የእግር ጉዞ " ይካሂዳሉ። በዚህም ወቅት ለመጪው አዲስ አመት የሰላም ምኞቶ የሚተላለፍበት እንዲሁም ግጭቱ እንዲቆምና ሴቶች በሰላም ግንባታ ተግባራት ውስጥ እንዲሳተፋ የሚጠየቅበት መርሀግብር ይኖረናል ተብሏል። የእግር ጉዞው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ላይ በካዛንቺ ሴቶች አደባባይ ጀምሮ መስቀል አደባባይ…
ፎቶ ፦ ትምራን ከኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (NEWA) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት " የሴቶች የሰላም የእግር ጉዞ " ዛሬ ሀሙስ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

የእግር ጉዞ ተሳያፊዎቹ ለመጪው አዲስ አመት የሰላም ምኞታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በሀገራችን ግጭቱ እንዲቆምና ሴቶች በሰላም ግንባታ ተግባራት ውስጥ እንዲሳተፋ ጠይቀዋል።

በዕለቱ ከተላለፉ መልዕክቶች መካከል ፦

🪧 #በቃን መደፈር !
🪧 የሀገር ሰላም የሴቶችም ሰላም እና ደህንነት ነው !
🪧 የሴቶች ሰውነት የጦር ሜዳ አይደለም !
🪧 ጦርነት የሞት፣ የረሃብ፣ የስደት እና የጥፋት መንስኤ እንጂ የልማት መሳሪያ አይደለም !
🪧 በጦርነት የትኛውም አይነት አለመግባባት መፍትሄ አግኝቶ አያውቅም። እኛ የኢትዮጵያ ሴቶች ሰላማዊ የግጭት መፍቻ ዘዴዎችን እንደግፋለን የሚሉት ይገኙበታል።

የፎቶ ባለቤት ፦ የኢትዮጵያ ሴት የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ጥምረት

@tikvahethiopia
#AI2022 #ኢትዮጵያ🇪🇹

ሀገራችን ኢትዮጵያ የመጀመሪየውን የፓን አፍሪካን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ኮንፈረንስ ልታካሂድ ነው።

ኮንፈረንሱ ከጥቅምት 4 እስከ 5 (2022) ድረስ ነው የሚካሄደው።

ይኸው የመጀመሪያ የሆነው ኮንፈረንስ የሚካሄደው በአዲሱ የሥነ ጥበብ እና ሳይንስ ሙዚየም መሆኑ ታውቋል።

ኮንፈረንሱን ለመታደም ለመመዝገብ : panafriconai.org

Via Billene Seyoum (ቢልለኔ ስዩም)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሩቶ እ.ኤ.አ. መስከረም 13 አምስተኛው የኬንያ ፕሬዜዳንት ሆነው ቃለ መሃላ ይፈፅማሉ። በዛሬው ዕለት የጎረቤት ሀገር ኬንያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዊሊያም ሩቶን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማሸነፍ አፅንቷል። ፍርድ ቤቱ የነሀሴ 9 (እኤአ) ድምጽ ውጤት እንዲሰረዝ ለማድረግ የቀረቡ ሁሉንም ክሶች ውድቅ አድርጓል። ሩቶ በመጪው መስከረም 13 (እኤአ) የኬንያ አምስተኛው ፕሬዝዳንት ሆነው ቃለ መሃላ…
የሩቶ በዓለ ሲመት ማክሰኞ ይካሄዳል።

የተመራጩ የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በዓለ ሲመታቸዉ ማክሰኞ በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚካሄድ ሲሆን ለዚሁ በዓለ #ኢትዮጵያን 🇪🇹 ጋብዘዋል።

የኬንያ 5ኛው ፕሬዝዳንት በመሆን የተመረጡት ሩቶ መንበረ ሥልጣኑን ከፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በሚረከቡበት በዚህ ቀን ከኢትዮጵያ መሪ በተጨማሪ ከ40 በላይ የሃገራት መንግሥታት እና የመንግሥታት ተጠሪዎችን መጋበዛቸው ተሰምቷል።

በሥነ-ስርዓቱ ላይ እንዲገኙ ከተጋበዙት መካከል፤ የግብጽ፤ ዩጋንዳ፤ ናይጀሪያ፤ ጋና እና የደቡብ አፍሪቃ መሪዎች ይገኙበታል።

የአውሮፓ ህብረት፣ የአፍሪቃ ህብረትና መንግሥታዊ የልማት ጉዳይ ባለሥልጣናት ተወካዮች በሥነ-ስርዓቱ ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

መረጃውን ዴይሊ ኔሽንን ዋቢ አድርጎ የዘገበው ዶቼ ቨለ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የ96 ዓመቷ ዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት  በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የንግስቷን ህልፈት ባኪንግሃም ቤተ-መንግሥት አሳውቋል። @tikvahethiopia
የንግስት ኤልዛቤት ዳግማዊት ህልፈትን ተከትሎ የዓለም ሀገራት መሪዎች እና ተቋማት ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ መሪ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድም በንግስቷ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ስም ገልጸዋል።

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በተረጋገጠ የትዊተር ገፃቸው ባሰራጩት የሀዘን መልዕት ፤ " በመንግስት እና በኢትዮጵያ ህዝብ ስም የተሰማኝን ሀዘን ለንጉሳውያን ቤተሰብ (The Royal Family) ፣ ለብሪታኒያ መንግስትና ህዝብ መግለፅ እወዳለሁ " ብለዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም እና የኮመን ዌልዝ አገራት ንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት ትላንት ሀሙስ ጳጉሜን 3 በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወቃል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia