TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Somalia

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በዓለ ሲመታቸው ይከናወናል።

ለዚህም በዓለ ሲመት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ሶማሊያ ሞቃዲሾ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካቸው ጋር ሞቃዲሾ ገብተዋል።

በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በተመራው የልዑካን ቡድን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ይገኙበታል።

ዶ/ር ዐቢይ ዛሬ ሞቃዲሾ ከገቡ በኃላ ከፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ጋር መገናኘታቸውን የሶማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሶማሊያ በሚኖራቸው ቆይታ በፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በዓለ ሲመት ላይ ንግግር እንደሚያርጉ ፤ በተጨማሪም በበዓለ ሲመቱ ከሚታደሙ ከሌሎች የሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትሽ ምክክር እንደሚያደርጉ ተሰምቷል።

ፎቶ ፡ Ahmed K Kosar / Somali Guardian

@tikvahethiopia
#Somalia

የግብፁ " Banque Misr " እና የቱርኪዬ " Ziraat Katilim " ባንኮች ሶማሊያ ውስጥ እንዲሰሩ ፍቃድ ፀደቀላቸው።


ጎረቤት ሶማሊያ ለግብፅ እና ቱርኪዬ ባንኮች የስራ ፍቃድ አፅድቃለች።

የሶማሊያ ማዕከላዊ ባንክ ቦርድ ትላንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ መስፈርት አሟልተው ለተገኙት ሁለት ዓለም አቀፍ ባንኮች በሀገሪቱ ውስጥ ቅርጫፎቻቸውን እንዲመሰርቱ እና እንዲንቀሳቀሱ ፍቃድ አፅድቋል።

ፍቃዱ ረጅም ወራት ከወሰደ ሂደት በኃላ ነው የፀደቀው።

ፍቃድ የፀደቀላቸው ባንኮች የግብፁ " Banque Misr " እና የቱርኩ " Ziraat Katilim " ሲሆኑ በሶማሊያ የፋይናንስ ሴክተር እና በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ፍቃዱን ያፀደቀው CBS ገልጿል።

ሁለቱ ባንኮች ሶማሊያ ውስጥ እንዲሰሩ ፍቃድ ያገኙ #የመጀመሪያዎቹ ዓለም አቀፍ ባንኮች ሆነው ተመዝገበዋል።

@tikvahethiopia
#Somalia

አልሸባብ ዛሬ #ሶማሊያ ውስጥ ባደረሰው ጥቃት የሰዎች ህይወት ጠፋ።

በሽብር ቡድኑ በሶማሊያ ደቡባዊ አቅጣጫ በተለያዩ ቦታዎች በተፈፀሙ ሁለት የቦንብ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል።

በመጀመርያው ጥቃት ታችኛው ሸበሌ ክልል በአፍጎዬ ከተማ በእንስሳት የገበያ ቦታ በተወረወሩ 2 ቦምቦች በትንሹ 4 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ተነግሯል።

ሁለተኛው ጥቃት ማርካ በተባለችው የወደብ ከተማ የተፈፀመ ሲሆን የወረዳው ኮሚሽነር አብዱላሂ አሊ ዋፎው በጥቃቱ መገደላቸው ተዘግቧል።

ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።

የአካባቢው ፖሊስ እንዳስታወቀው ጥቃቱ የተፈፀመው የማርክ ወረዳ ኮሚሽነር በወረዳዉ ጽሕፈት ቤት ቅጥር ግቢ ዉስጥ ለተሰበሰቡ ነዋሪዎች ንግግር ሲያደርጉ ነው።

ንግግር ሲያደርጉ የነበሩት ኮሚሽነሩ አብዱላሒ ዓሊ አሕመድ ዋፎው እና ሌሎች ስምንት ተሰብሳቢዎች ወዲያዉ ሞተዋል።

ምንጭ፦ ሮይተርስ እና ዶቼ ቨለ

@tikvahethiopia