TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኬንያ(ናይሮቢ)🛫

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሐመድ አብዱላሂ መሐመድ ከኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር #ለመወያየት በአሁኑ ወቅት ወደ #ናይሮቢ ኬንያ አቅንተዋል።

ጠ/ሚር ዶ/ር #ዐቢይ_አሕመድ በሶማሊያና ኬንያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት እንደ ምሥራቅ አፍሪካ በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ሊቀ መንበርነታቸው በቅርበት በመከታተል ወደ #ዕርቅ የሚመጡበትን መላ እያፈላለጉ ነው።

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የኬንያው ፕሬዚዳንት ኬንያታና የሶማሊያው አብዱላሂ መሐመድ ወደ ኢትዮጵያ ለይፋዊ ጉብኝት በዘለቁ ወቅት ከሁለቱም ጋር ባደረጉት ምክክር፤ ይህንን የኬንያና የሶማሊያ መሪዎች የፊት ለፊት ውይይት ለማመቻቸት ወስነው ነበር። ይህ የውይይት መድረክም በሁለቱ መካከል ያለውን የተካረረ ውጥረት ያረግባል ተብሎ ይታመናል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737 አውሮፕላን ዛሬ ጠዋት #ከአዲስ_አበባ ተነስቶ ወደ ኬንያ #ናይሮቢ ሲበር #ተከስክሶ የሰው ህይወት አልፏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኬንያ የአህያዎች ቁጥር ከዕለት ዕለት እየተመናመነ ነው። መቀመጫውን #ናይሮቢ ያደረገው የአፍሪካ የእንሰሳት ደህንነት ተሟጋቾች ቡድን እንዳጠናው ከሆነ የአህያ ዝርያ የመጥፋት አደጋ ተጋርጦበታል። ሶስት አመት በፊት በኬንያ አራት የአህያ ቄራዎች መከፈታቸውን ተከትሎ በቀን ብዙ አህዮች ይታረዳሉ። ድርጅቱ እንደሚለው ከሆነ በሥራ ቀናት በሳምንት በትንሹ 410 አህዮች ይታረዳሉ። የአህያዎቹ ቆዳም ወደ ቻይና ይላካል። ድርጅቱ እንደሚለው ኑሯቸውን በአህያ አገልግሎት ላይ የመሠረቱ ማኅበረሰቦች ቄራዎቹ ከተከፈቱ በኋላ ለችግር ተጋርጠዋል። በኬንያ አሁን ያሉት አህዮች ብዛት በድምሩ 2 ሚሊዮን ይጠጋል።

Via #BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia