TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአፍጋኒስታን ጦርነት ...

የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ፡

- 2 ትሪሊዮ ዶላር በጦርነቱ ምክንያት ውጪ ሆኗል።

- ለጦርነት ብቻ 300 ሚሊዮን ዶላር በየቀኑ ሲወጣ ነበር፤ ለ20 ዓመታት።

- 20,744 አሜሪካውያን ተጎድተዋል።

- 2,461 ሞተዋል፤ የባለፈው ሳምንቱን 13 ወታደሮች ጨምሮ።

ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በ #አፍጋኒስታን_ጦርነት በእሳቸው ስልጣን ዘመን ሌላ ትውልድ የአሜሪካውያን ልጆችን ለመላክ ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ግልፀው ይህ ጦርነት መቆም ከነበረበት ቆይቷል ብለዋል ፤ የ20 ዓመታቱ ጦርነት አሁን ላይ ማብቃቱን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ የተሳተፈችባቸው ጦርነቶች ...

በ21ኛው ክፍለ ዘመን የዓለም ኃይል እንደሆነች የሚነገርላት አሜሪካ በበርካታ ሀገራት ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች እጇን አስገብታለች።

በጥቂቱ...

#አፍጋኒስታን

አል-ቃይዳ መስከረም 11 ቀን 2001 በአሜሪካን ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ አሜሪካ ታሊባንን ከስልጣን ለማስወገድ አሜሪካ የአፍጋኒስታንን ወረራ መርታለች። 20 ዓመታት የዘለቀ እጅግ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ነበር። በመጨረሻ ግን ታሊባን ወደቦታው ተመለሰ። አሜሪካም ጓዛን ጠቅልላ ወጣች።

#ኢራቅ

በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ 2003 ኢራቅን በመውረር ሳዳም ሁሴን ከሥልጣን አስነስታለች። በኢራቅ ጦርነት በርካቶች አልቀዋል፣ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ኢራቅ ዛሬም አስተማማኝ ሙሉ ሰላም የላትም። ለዳግም ግንባታም ደፋ ቀና እያለች ነው።

#የድሮን_ጥቃቶች

አሜሪካ ሽብርን ለመዋጋት በሚል በፓኪስታን፣ የመን፣ ሱማሊያ፣ ሊቢያ የድሮን ጥቃቶችን ፈፅማለች (አሜሪካ ከፍተኛ የሰራዊት ቁጥር አላሰፈረችም)።

እነሊቢያ፣የመን፣ ሱማሊያ በጦርነት ምስቅልቅላቸውን አውጥቶት ዛሬም ማገገም ያልቻሉ ለደህንነት አስጊ ሀገራት ሆነው ቀርተዋል።

#ሊቢያ

የአሜሪካና የአውሮፓ አጋሮች እኤአ በ 2011 በሊቢያ የአየር ዘመቻ ከፍተው ነበር ፤ ጥቃቱ ሙአመር ጋዳፊ በአረብ አብዮት ለመቃወም በተነሳሱ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለመከላከል በሚል ነው ፤ የእነ አሜሪካ መዘቻ ጋዳፊን አወረደ ፣ ሊቢያ ግን ወደ ትርምስና ቀውስ ገባች፤ ዛሬም እዛው ናት።

አሜሪካ እጇን ባስገባችባቸው ሀገራት ትክክለኛ ውሳኔ እንደሆነ የምትሞግት ሲሆን በምታካሂዳቸው ዘመቻዎች ከሽብር ጥቃት ዜጎቿን መከላከል /የሀገሯን ደህንነት ማስጠበቅ እንደቻለች በተለያየ ጊዜ ታነሳለች።

@tikvahethiopia
አሜሪካ የተሳተፈችባቸው ጦርነቶች ...

#Repost

በ21ኛው ክፍለ ዘመን አሜሪካ በበርካታ ሀገራት ውስጥ በተደረጉ ጦርነቶች እጇን አስገብታለች።

በጥቂቱ...

#አፍጋኒስታን

አል-ቃይዳ መስከረም 11 ቀን 2001 በአሜሪካን ላይ ጥቃት ከሰነዘረ በኋላ አሜሪካ ታሊባንን ከስልጣን ለማስወገድ አሜሪካ የአፍጋኒስታንን ወረራ መርታለች። 20 ዓመታት የዘለቀ እጅግ ዋጋ ያስከፈለ ጦርነት ነበር። በመጨረሻ ግን ታሊባን ወደቦታው ተመለሰ። አሜሪካም ጓዟን ጠቅልላ ወጣች።

#ኢራቅ

በፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ ዘመን አሜሪካ እ.ኤ.አ. በ 2003 ኢራቅን በመውረር ሳዳም ሁሴን ከሥልጣን አስነስታለች። በኢራቅ ጦርነት በርካቶች አልቀዋል፣ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል። ኢራቅ ዛሬም አስተማማኝ ሙሉ ሰላም የላትም። ለዳግም ግንባታም ደፋ ቀና እያለች ነው።

#ሊቢያ

የአሜሪካና የአውሮፓ አጋሮች እኤአ በ 2011 በሊቢያ የአየር ዘመቻ ከፍተው ነበር ፤ ጥቃቱ ሙአመር ጋዳፊ በአረብ አብዮት ለመቃወም በተነሳሱ ተቃዋሚዎች ላይ የደረሰውን ግፍ ለመከላከል በሚል ነው ፤ የእነ አሜሪካ መዘቻ ጋዳፊን አወረደ ፣ ሊቢያ ግን ወደ ትርምስና ቀውስ ገባች፤ ዛሬም እዛው ናት።

#ሶሪያ

አሜሪካ ከሌሎች አጋሮቿ ጋር ሆና በሶሪያ ጦርነት ውስጥም እጇ ያለበት ሲሆን በሶሪያ የሚንቀሳቀሱ የበሽር አል አሳድ ተቃዋሚዎችን ለማጥፋት በምትወስደው እርምጃ የሶሪያ ከተሞች ክፉኛ አውድማለች።

#የድሮን_ጥቃቶች

አሜሪካ ሽብርን ለመዋጋት በሚል በፓኪስታን፣ የመን፣ ሱማሊያ፣ ሊቢያ የድሮን ጥቃቶችን ፈፅማለች (አሜሪካ ከፍተኛ የሰራዊት ቁጥር አላሰፈረችም)።

እነሊቢያ፣የመን፣ ሱማሊያ ጦርነት ምስቅልቅላቸውን አውጥቶት ዛሬም ማገገም ያልቻሉ ለደህንነት አስጊ ሀገራት ሆነው ቀርተዋል።

@tikvahethiopia