TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#China #SouthKorea #Russia

- ባለፉት 24 ሰዓት በቻይና አስራ አራት (14) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ ፤ ሁለቱ ከውጭ የገቡ እንደሆኑ ተገልጿል። በቻይና በአንድ ቀን ከ10 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ9 ቀናት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

- በደቡብ ኮሪያ በ24 ሰዓት 34 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በደቡብ ኮሪያ ከአንድ ወር በኃላ በአንድ ቀን ከ30 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

- ሩሲያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 11,012 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በተጨማሪ 88 ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot