TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FDREDefenseForce

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ የመከላከያ ሰራዊቱ በምሥራቁ ግንባር ራያን ሙሉ በሙሉ ነጻ ማውጣቱን ገለፀ።

ሰራዊቱ ጨርጨር፣ ጉጉፍቶ መሖኒን ነጻ አውጥቷል ተብሏል።

በየቦታው የነበሩትን ወሳኝ የኮንክሪት ምሽጐችንም እንዳፈረሰ ተገልጿል።

ሠራዊቱ በአሁኑ ጊዜ ወደ መቐለ በመገሥገሥ ላይ ነው።

በምዕራብ ግንባር "በአዲ ነብሪድ እና በአዲ ዳእሮ" የሚገኙ ከባድ ምሽጎችንም በማፍረስ ሽሬን ተቆጣጥሮ ወደ አክሱም እየገሰገሰ መሆኑ ተገልጿል።

በውጊያው እጅግ ብዙ መሣሪያዎች ተማርከዋል ፤ የትግራይ ልዩ ኃይል አባላትም በቁጥጥር ሥር ውለዋል ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,778
• በበሽታው የተያዙ - 339
• ህይወታቸው ያለፈ - 7
• ከበሽታው ያገገሙ - 163

አጠቃላይ 103,395 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,588 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 64,293 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

320 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SecretaryPompeo

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ምኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ህወሓት በኤርትራ ላይ የፈጸመውን ጥቃት አወገዙ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ "ህወሓት በኤርትራ ላይ የፈጸመውን ጥቃት እና ግጭቱን ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ ያደረገውን ሙከራ አጥብቀን እናወግዛለን" ብለዋል።

"ህወሓት" እና የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ግጭቱን ለማብረድ ፣ ሰላምን ለማስፈን እና የሰላማዊ ሰዎችን ደሕንነት ለመጠበቅ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ እናቀርባለን" ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ፖምፕዎ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ፥ ኤርትራ የአጸፋ እርምጃ ባለመውሰድ መታቀቧ ግጭቱ እንዳይስፋፋ ማገዙን ጠቅሰው አመስግነዋል።

በተጨማሪ የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኞች ለተጋላጮች ዕገዛ እንዲያቀርቡ ደሕንነቱ የተጠበቀ መተላለፊያ ሊፈቀድላቸው ይገባል ብለዋል ፖምፕዎ።

የአሜሪካ ዜጎችን ጨምሮ ሰላማዊ ሰዎች ከጉዳት ሊጠበቁ ፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ ሊሰጣቸው እና ከግጭት ቀጠናው የሚወጡበት መተላለፊያ ሊፈቀድላቸው እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

ገለልተኛ የሆነ ዘገባ ለመስራት እንዲቻልና የአሜሪካ ዜጎችን ጨምሮ ከሰላማዊ ሰዎች መገናኘት እንዲቻል በትግራይ የተቋረጡ የመገናኛ አገልግሎቶች ወደ ሥራ ሊመለሱ እንደሚገባም መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ 'ህወሓት' የትግራይ መሰረት ልማቶችን እያፈረሰ ነው አለ።

"ህወሓት" በሁሉም አቅጣጫዎች ወደ #መቐለ የሚወስዱት መንገዶች ላይ የሚገኙ አራት (4) ድልድዮችን አፍርሷል ሲል ገልጿል።

በሽሬና በአክሱም መካከል የሚገኘውን አስፓልት "በግሬደር" ቆፍሮ ወደ ጉድጓድነት ቀይሮታል ሲልም አሳውቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ፥ "ህወሓት እስከዛሬ ከፈጸማቸው ወንጀሎች በተጨማሪም ባወደማቸው መሠረተ ልማቶች በቅርቡ ይጠይቅባቸዋል" ብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'የንፁሃን ዜጎቻችን ስደት'

በትግራይ ክልል ያለውን ወጊያ በመሸሽ ወደ ሱዳን እየገቡ ያሉ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ነው።

አሁን ላይ ያለው ሁኔታም እጅግ አሳሳቢ ነው።

UNCHR ሰላማዊ ከሆነው ኑሯቸው ላይ ተፈናቅለው ሱዳን ለገቡት የሀገራችን ዜጎች ከሱዳን መንግስት ጋር በመሆን የህይወት አድን እርዳታ ለመስጠት እየሰራ ይገኛል።

እስከዛሬ ድረስ ባለው መረጃ ወጊያውን ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ ዜጎቻችን ከ30,000 ይበልጣሉ።

በትግራይ የኢንተርኔት መቋረጥ ፣ የባንኮች መዘጋት ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት አለመኖር ፣ የመሰረታዊ አቅርቦት እጥረት መፈጠሩ በእጅጉ ዜጎቻችን ለችግር አጋልጧቸዋል።

በትግራይ ክልል ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ፣ ዘመድ አዝማዶቻቸው ትግራይ ውስጥ የሚኖሩ እርስ በእርስ ከተገናኙ 15 ቀን ሊሆናቸው ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል እያካደ የሚገኘውን "ሕግ የማስከበር እንቅስቃሴ" በብሔር ወይም በሌላ ወገንተኝነት ላይ የተቃኘ ነው የሚለውን የተሳሳተ እሳቤ አጥብቆ እንደሚያወግዝ ዛሬ ህዳር 9/2013 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

እየተካሄደ ባለው "የህግ ማስከበር ዘመቻ" የትግራይ ህዝብ የመጀመሪያው ተጠቃሚ ይሆናል ሲል በመግለጫው ላይ ገልጿል።

* የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ታሽገዋል

ዋልያ ቆዳ ፋብሪካ እንዲሁም አዲስ አበባ ቆዳ ፋብሪካ አክሲዮን ማህበር የአካባቢ እና የህብረተሰቡን ጤና የሚጎዳ ብክለት በማድረሳቸዉ ምክንያት ታሸጉ።

በአቃቂ ቃሊቲ እና በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ የሚገኙት ሁለቱ ፋብሪካዎች የሚለቁት ከፍተኛ የሆነ ያልታከመ አደገኛ ፈሳሽ ቆሻሻ በአካባቢዉ ላይ ብክለት እያደረሰ እንደሚገኝ ህብረተሰቡ አቤቱታዎችን ሲያቀርብ ነበር።

የአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን የአካባቢ ብክለት ኢንስፔክሽን ባለሙያዎችም በመስክ ባደረጉት ምልከታ ይህንን ማረጋገጥ ችለዋል።

ይህ መረጃ ከአዲስ አበባ ከተማ አካባቢ ጥበቃ እና አረንጓዴ ልማት ኮሚሽን የተገኘ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዶክተር ደብረፅዮን መግለጫ ፦

የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ዛሬ በሰጡት መግለጫ "በሁሉም ግንባር ድል እየተቀዳጁ" መሆናቸው ተናግረዋል።

ሊያጠቃን የመጣው ኃይል በሁሉም ግንባሮች ከባድ ሽንፈት እየተከናነበ ነው የሚገኘው ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን በከተሞች ህዝብን እያንገላታ ይገኛል ብለዋል።

ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል ፥ "እስከ አሁን በጠላት ላይ የደረሰውን ከባድ ኪሳራ እና ሽንፈት በማጠናከር ወራሪዎችን ጠራርገን ለመደምሰስም መላእ የትግራይ ህዝብ ይዝመት" ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ዛሬ የጦር ሀይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም ጀነራል ብርሀኑ ጁላ መግለጫ ሰጥተዋል።

ሠራዊቱ በሁሉም ግንባሮች ድልን እየተጎናፀፈ እንደሚገኝ ተነግረዋል።

ጄኔራል ብርሃኑ ፥ "ህወሓት እያንዳንዳቸው 2 ሺ 500 የሰው ሀይል የያዙ 11 ብርጌድ ልዩ ሀይል፣ 14 ብርጌድ የዞን ታጣቂ እና አንድ ብርጌድ ሚሊሻ ቢገነባም፣ አሁን ነፍስ አውጭኝ ላይ ይገኛል" ብለዋል።

ነጻ በወጡ አካባቢዎች የሚገኘው ህብረተሰብም ለሠራዊቱ ከፍተኛ የሆነ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ህዝቡ ሠራዊታችንን ከሁዋላው እንዲመታ ቢያስታጥቁትም ፣ ምንም ሳይተኩሱ 200 መትረየስና ክላሽ አዲኮኮብ እና ሽሬ ላይ ለሠራዊታችን እስረክቧል ብለዋል።

የህወሓት ቡድን ኮማንድ ፖስቱን እና ትኳሾቹን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቢያደርግም ሠራዊታችን ነጥሎ ለመምታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ሲሉም ተደምጠዋል።

"ህወሓት" አሁኑ ላይ ኢትዮጵያን ወደ ጦርነት ለማስገባት እና ሀገሪቷን ለመበታተን ያቀደው እንደከሸፈበት እና በመከበቡ ነፍስ አውጭኝ ላይ ይገኛል ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Harari

በሐረሪ ክልል የሐኪም ወረዳ ፖሊስ ጽ/ ቤት ለጥፋት ዓላማ ሲዘጋጁ የነበሩ 17 ተጠርጣሪዎች ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳወቀ።

በ15ቱ ተጠርጣሪዎች መኖርያ ቤት በተደረገው ፍተሻ በርካታ የጦር መሳሪያዎች ተይዘዋል።

የጦር ሜዳ መነጽር ፣ የራዲዮ መገናኛ ፣ ፎቶ ካሜራ ፣ የጦር መሳርያ መያዣ ቁሳቁሶች ፣ 20 የሚደርሱ ሲም ካርዶች ፣ የጦር ሜዳ የመጀመርያ ህክምና መስጪያ ቁሳቁሶች ከተጠርጣሪዎቹ የተያዙ ናቸው።

በተጨማሪ የተለያዩ መታወቂያዎች፣ የባንክ ቤት ቼክና ደብተር፣ ላፕቶፖች፣ የጸረ ሽምቅ ውጊያ ማስተማሪያ መጽሃፎች እና ሌሎች ቁሳቁሶችም በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

Via ENA
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TikvahFamily

ሀሰተኛ ፎቶዎች/ምስሎችን እንዴት ልለይ ?

ሀገራችን ያለችበትን 'ከባድ ውጥረት' ሁላችንም የምናውቀው ነው። ይህን ተንተርሶ እጅግ በጣም ብዙ "ሀሰተኛ ፎቶዎች" እየተሰራጩ እንደሆነ ተመልክተናል።

ስለዚህ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚያጠራጥራችሁን ፎቶ ስትመለከቱ በቀላሉ የትኛውንም ሚዲያ ወይም ግለሰብ እንዲያጣራላችሁ ሳትጠብቁ በእጅ ስልካችሁ ማረጋግጥ ትችላላችሁ።

በቅደሚያ 'ሀሰተኛ' የመሰላችሁን ፎቶ/ምስል ወደ ስልካችሁ Save አድርጉት።

በቀላሉ ስልካችሁ ላይ "Google Chrome App" ካለ ፦
-www.google.com ግቡ
-ወደ Desktop Site ቀይሩት
-በቀኝ በኩል ከላይ Image የሚለውን ምረጡ
-የካሜራ ምልክቱን ተጫኑ የፎቶውን URL/ፎቶውን Upload አድርጉት።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን "የአገር ክህደት ወንጀል" ፈፅመዋል በተባሉ 76 ጄነራል መኮንኖች፣ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች እና የበታች ሹማምንቶች ላይ የመያዣ ትዕዛዝ እንደወጣባቸው አሳውቋል።

* የፌዴራል ፖሊስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia