TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መግለጫ‼️

(15.04.2011ዓ.ም የሲዳማ ዞን ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ)

ወቅታዊ የሀዋሳ ከተማን #ፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ በከተማው አስተዳደር ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የተሰጣዊ ዜጣዊ መግለጫ፦

ሀገራችን ኢትዮጵያ በፈጣን ፖለቲካዊ የለውጥ ሂደት ውስጥ መሆኗ በግልፅ የሚታወቅ ሀቅ ነው፡፡ ለውጡን ተከትሎ በከተማችን ሀዋሳም አልፎአልፎ አሉታዊ ክስተቶች ይስተዋላሉ፡፡

ከእነዚህ አሉታዊ ክስተቶች መካከል ከሰኔ 10/2010 ዓ.ም ጀምሮ በከተማው ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ እየተስተዋሉ ያሉት ግጭቶችና የፀጥታ መናጋት በቀዳሚነት ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ይህን አልፎ አልፎ የሚከሰተው ግጭት ሀዋሳ ከተማ የምትታወቅበትን ነዋሪዎቿ ለዘመናት ያዳበሩት የመከአበክሮ የመፈቃቀድ እና አብሮ የመኖር እሴት እንዳይሸረሽር መንግስት አበክሮ በመስራት ላይ ነው፡፡

በከተማዋ ለዘመናት የቆየውን አብሮ የመኖር እሴት ለማጠልሽት፣ ቅሬታ ለመፍጠርና የጥላቻ ጥቁር ነጥብ ጥለው ለማለፍ የሚዳክሩ አካላትን ጥረት ለማክሸፍና የህግ የበላይነትን ለማስፈን ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ ግጭቶች በሰው ህይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሱ የጥፋት ሀይሎችን ለህግ በማቅረብ ባጠፉት ልክ ተጠያቂ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፤ ወደፊትም ተጠናክሮ ቀጥላል፡፡

ይሁንና ፀረ-ሰላም ሀይሉ ከድርጊቱ ባለመቆጠብ የተሳሳተ የትግል ስልቱን በመቀያየር የእውቀት መገበያያ የሆነውን ትምህርት ቤት የጦርነት አውድማ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

በዛሬው እለትም በሀዋሳ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ በሚገኘው አዲስ ከተማ 2ኛ ደረጃ እና መሰናዶ ትምህርት
ቤት ሁከትና እረብሻ በመፍጠር 12 ወጣቶች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሰባቱ ተማሪዎች ሲሆኑ አምስቱ ደግሞ ተማሪ ያልሆኑ መሆናቸው ተለይቷል፡፡

በግጭቱም እርስበእርስ ድንጋይ በመወራወር በአስሩ ላይ ቀላል ጉዳት እንዲሁም ለፀጥታ ሀይሉ ባለመታዘዝ በሁለቱ ላይ ደግሞ ከባድ አደጋ ደርሷል፡፡

ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለቱ ወጣቶች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል እና በአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

የረብሻው መንስኤ ገና በፀጥታ ሀይሉ #በመጣራት ላይ ያለ ቢሆንም በርካታ የትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ አካላት ያልሆኑ ነገር ግን እራሳችውን ከተማሪ ጋር ያመሳሰሉ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ወደ ትምህርት ቤቱ በመግባት ተማሪዎችን ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ከተዋል፡፡

ክስተቱን #የብሔር_ግጭት ቅርፅ ለማስያዝ ጥረት ለማድረግ የሞከሩ ቢሆንም አብሮ መኖርን ባህሉ ያደረገው የከተማው ነዋሪ ግን አልተባበራቸውምና ልፋታቸው ሳይሳካ #መና ሆኖ ቀርቷል፡፡

በዚህ ድርጊት #ጠንሳሽነትና ተሳታፊነት የተጠረጠሩ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር የማዋል ስራ የተጀመረ ሲሆን በቀጣይም
ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በፀጥታ ሀይሉና በህብረተሰቡ የጋራ ጥረት የከተማው #ፀጥታ_ሁኔታ ወደነበረበት የተመለሰ ሲሆን ለከተማው ሰላም ወዳድ ህዝብ የከተማው አስተዳደር ያለውን ክብርና አድናቆት እየገለፀ በቀጣይም ነዋሪው ከመንግስት ጎን በመቆም የከተማውን ሰላም ለማደፍረስና አብሮ የመኖር እሴትን ለማጠልሸት የሚንቀሳቀሱ አካላትን አጋልጦ በመስጠት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪውን እያቀረበ የከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ሰላም እና ፀጥታ የማስጠበቅ ስራውን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ያስታውቃል፡፡

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ ባህል ቱሪዝምና የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ ስድስት ኪሎ አካባቢ አንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል የስራ ባልደረባውና #ባለቤቱ የሆነችውን የፖሊስ አባል ዛሬ ረፋድ ላይ በጥይት #መግደሉ ተሰማ። የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ምክትል ሃላፊ ኮማንደር #ተስፋዬ_ምትኩ ለኢዜአ እንደገለጹት ተጠርጣሪው የፖሊስ አባል የሆነችውን የትዳር አጋሩን ስድስት ኪሎ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ካምፕ መግደሉን አረጋግጠዋል። መንስኤው ገና #በመጣራት ላይ ቢሆንም ግድያው የተፈፀመው በመካከላቸው በተፈጠረው ጊዜያዊ አለመግባባት መሆኑም ታውቋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethioia
#DrLiaTadesse

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 1,861 ላቦራቶሪ ምርመራ ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መቶ ዘጠና አራት (194) ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሴቶች ሲሆኑ እድሜያቸው ከ23-33 ዓመት የሆኑ ይገኙበታል። የሁሉም ታማሚዎች የመኖሪያ ቦታ አዲስ አበባ ነው።

የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦

• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 0

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው- 2

• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት #በመጣራት ላይ ያለ - 1

ተጨማሪ መረጃ ፦

በትላንትናው ዕለት ሁለት ሰዎች (1 ከአዲስ አበባ እና 1 ከኦሮሚያ ክልል) ከበሽታው ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ዘጠና አምስት (95) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የተሰጠ መረጃ፦

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 88 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ሁለት (2) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ38 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላት ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 2 - የ16 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምዕራብ ሸዋ ዞን ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላት ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 2,670
• ባለፉት 24 ሰዓት የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 88
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 2
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 8
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• በበሽታው ህይወታቸ ያለፈ - 1
• አጠቃላይ ያገገሙ - 10
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 19

#TikvahEthiopia
@tikvhhethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የተሰጠ መረጃ፦

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 292 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው አራት (4) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 2 - የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላቸውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 3 - የ29 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 4 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የምስራቅ ሀረርጌ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #ያለው

በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,769
• ባለፉት 24 ሰዓት የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 292
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 4
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 14
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አጠቃላይ ያገገሙ - 10
• በበሽታው ህይወታቸ ያለፈ - 1
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 25

Via @tikvahethAFAANOROMOO

#TikvahEthiopia
@tikvhhethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 308 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ሶስት (3) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ36 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሰንዳፋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 2 - የ22 ዓመት ኢትዮጵያዊት የሱሉልታ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላት ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።

ታማሚ 3 - የ23 ዓመት ኢትዮጵያዊት የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት #ያላት

Via @tikvahethAFAANOROMOO (Biiroo Fayyaa Oromiyaa)

#TikvahEthiopia
@tikvhhethiopiaBot @tikvahethiopia
#Oromiyaa

የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

ታማሚ 1 - የ47 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሰበታ ከተማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 2 - የ26 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ከተማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ።

ታማሚ 3 - የ21 ዓመት ኢትዮጵያዊት የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

ታማሚ 4 - የ24 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሸዋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘች።

ታማሚ 5 - የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊ የምዕራብ ሸዋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላቸውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኙ።

ታማሚ 6 - የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዳማ ነዋሪ ፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 7 - የ30 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ነዋሪ ፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 8 - የ12 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዳማ ነዋሪ ፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላት።

ታማሚ 9 - የ10 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዳማ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያለው።

ታማሚ 10 - የ5 ዓመት ኢትዮጵያዊት የአዳማ ነዋሪ ፤የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላት።

ሌላኛዋ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዟ የተረጋገጠው አንዲት የ35 ዓመት ሴት ስትሆን ህይወቷ ካለፈ በኃላ በተደረገ 'የአስክሬን ምርመራ' ነው ቫይረሱ እንዳለባት የተረጋገጠው። የመኖሪያ አድራሻዋ #በመጣራት ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopia