TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ብዙ አይነት ቀለም ቢኖረንም #በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ አንድ ነን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከብሄራዊ ትያትር⬆️

"የክቡር ዶ/ር አርቲስት #ጥላሁን_ገሰሰ 78ኛ ዓመት #የልደት ቀን መታሰቢያ ዝግጅት ዛሬ #በኢትዮጵያ_ብሔራዊ ቲያትር በደመቀ ስነ ስርዓት እየተከበረ ይገኛል።"

ምንጭ፦ ሱራፌል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀለኞች መሸሸጊያ የላቸውም...

#በኢትዮጵያ_ወንጀል_ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የትም ሆነ የት መሸሸጊያ ያላቸውን እጃቸውንም #አንጠልጥዬ ለኢትዮጵያ መንግስት አስረክባለሁ ሲል አለም አቀፍ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ማስተማመኛ ሰጠ፡፡

ትናንትና አዲስ አበባ የመጡት የኢንተርፖል ዋና ሀላፊ ዶ/ር ጀርጋን ስቶክ ከፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው ወሬው የተሰማው፡፡

ከንግግሩ በኋላ መግለጫ የሰጡት ኮሚሽነር ጀነራል #እንዳሻው_ጣሰው በኢትዮጵያ ወንጀል ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያንን ኢንተርፖል ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደሚሰጥ ማስተማመኛ ሰጥቷል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙና ሀገር የዘረፉ ሰዎች ግማሾቹ በሀገር ውስጥ ግማሾቹ ደግሞ ባህር አቋርጠው በውጭ አገር እንደሚኖሩ ታውቋል ብለዋል፡፡

ይህንን ወንጀል ፈፃሚዎቹ የትም ይደበቁ የትም ይኑሩ ኢንተርፖል እጃቸውን አንጠልጥሎ ለኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያስረክብ ሀላፊው አረጋግጠውልናል ሲሉ መናገራቸውን ከመንግስታዊ ምንጮች ስምቻለሁ ብሎ ሸገር ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሰሞኑ ባስተላለፉት መልዕክት በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች ማንም ይሁን ማን ከየትኛውም ብሔር ገብተው ይደበቁ፣ የትኛውም ወገን ይጩህላቸው በወንጀል እስከተጠረጠሩ ድረስ ካሉበት አድነን ለህግ እናቀርባቸዋልን ማለታቸው
ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አና ጎሜዝ አዲስ አበባ ገቡ🔝

#አና_ጎሜዝ አዲስ አበባ ገብተዋል። አና ጎሜዝ #በኢትዮጵያ የሦስት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ ነው ዛሬ የካቲት 9 ቀን 2011 ዓ.ም. አዲስ አበባ የገቡት። በሦስት ቀናት ቆይታቸው የመንግስት #ባለስልጣናትን፣ የፓርቲ #መሪዎችንና የበጎ አድራጎት አመራሮችን እንዲሁም ከመገናኛ ብዙሃን ጋር እንዲገናኙ ፕሮግራም ተይዞላቸዋል፡፡

Via Getu Temsegn
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር🔝

#በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉት የፀጥታ ችግሮች በርካቶች ከቀያቸው #እንዲፈናቀሉ እና የሰው ሕይወት በየቦታው #እንዲቀጠፍ ምክንያት እየሆኑ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ 51 አህጉረ ስብከቶች ስለሰላም የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና አተገባበር ዙሪያ ለሃይማኖት አባቶች እና ለምዕመናን በባሕር ዳር ስልጠና እየሰጠች ነው፡፡

በባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ደብረ ፀሐይ ሰላም አድርጊው ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ ፍቅረ ማርያም ‹‹አሁን ላይ በሀገሪቱ የተፈጠረው የሰላም እጦት የሰው ልጆች ለእግዚአብሔር ያለመታዘዝ ምንጮች ናቸው፤ እግዚአብሔር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ በምድር ላይ ሳለን የሰላም አስፈላጊነት የሁሉም ነገር ቁልፍ ናት ብሎ አስተምሮናል፤ ይህ ሰላም እንዲኖር የሃይማኖት አባቶች በጸሎት እና አስተምህሮ ከዚህ የበለጠ መሥራት እንደሚጠበቅብን አመላካች ነው›› ብለዋል፡፡

የፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አስተዳዳሪ መልአከ ገነት ሰፊው ወልደትንሳኤ ካህናት ሕዝቡ ሰላምን ያገኝ ዘንድ እንዲያስተምሩ አደራ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ ‹‹ካህናት ስለሰላም የሠራነው ሥራ ስለምን በዚህ ትውልድ ፍሬ #አላፈራም? ሕዝቡስ ስለምን ሰላምን አጣ? ብለን ሁከት የሚፈጥር እንዳይኖር በትኩረት እንድንሠራ ኃለፊነት አለብን›› ብለዋል፡፡

የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ #አብርሃም ደግሞ ሀገሪቱ ዜጎች እየተሰደዱ፣ ሀብት ንብረታቸው እየወደመ እና ሕይወታቸውን እያጡ ያሉበት ወቅት ላይ እንደምትገኝ ነው የተናገሩት፡፡ ሁኔታው ቤተ ክርስቲያን #ስለሰላም ከዚህ በላይ መሥራት እንዳለባት አመላካች መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ብጹዕነታቸው ‹‹ሰላምን የማይሻ ሰው ውስጡ የፍርሃት ባሕር አለ፡፡ በፍርሃት የሚቅበዘበዝ ትውልድ ደግሞ የተዋቡ ከተሞችን ዶግ አመድ ያደርጋል›› ነው ያሉት፡፡ ግጭት የሕጻናት እና እናቶችን ዋይታ እንደሚያበዛና ለፀብ የሚያነሳሱ ሰበቦችና መደለያዎች ግን በርካታ መሆናቸውንም አመልክተዋል፡፡ ‹‹የምንመራው ሕዝብ #ሰላም_ከሌለው አይጸድቅም፤ ጽድቅ የማያገኝ የእግዚአብሔር ትውልድ እንዳይኖር ደግሞ የሃይማኖት አባቶች ከዚህም በላይ መሥራት ይኖርብናል›› በማለትም አቡነ አብርሃም አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethioia