TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አርቲስት ሄለን መለስ🛬ባህር ዳር ገባች!

የኤርትራ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ባሕር ዳር ገቡ፡፡ የኤርትራ ኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ዛሬ ባሕር ዳር ላይ ለሚኖራቸው የሙዚቃ ድግስ ነው አሁን ባሕር ዳር የገቡት፡፡

የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎቹን ናሆም ዩሃንስ እና ሄለን መለስን የያዘዉ ልኡክ ባሕር ዳር ገብቷል፡፡

ልዑኩ ባሕር ዳር ዕለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና አድናቂዎቻቸው አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🙏222,222 TIKVAH-ETH🙏
#Update የአፋር ክልል ምክር ቤት ሰኞ በሚያደርገው አስቸኳይ ጉባዔ #አዲስ የክልል ርእሰ መስተዳድር ይሾማል።

Via-FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
OPA🔝

#የኦሮሚያ_ሀኪሞች_ማህበር በዛሬው ዕለት የኦሮሚያ ጤና ቢሮ፣ የአትዮጵያ ሐኪሞች ማህበር ተወካይ እና አክቲቪስት #ጀዋር_መሃመድ በተገኘበት በኢሊሊ ሆቴል የመጀመሪያ ጉባኤ እና የምስረታ ክብረበዓል ተከናውኗል።

Oromiyaa Physcians Association(OPA) inaugration ceremony held @ Elili International Hotel!

©ዶክተር ሲሳይ ከOPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake News Alert‼️

"66ቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወታደራዊ እርምጃ (ቀጥታ #ተገደሉ)" በሚል በሶሻል ሚዲያው የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀለኞች መሸሸጊያ የላቸውም...

#በኢትዮጵያ_ወንጀል_ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የትም ሆነ የት መሸሸጊያ ያላቸውን እጃቸውንም #አንጠልጥዬ ለኢትዮጵያ መንግስት አስረክባለሁ ሲል አለም አቀፍ የፖሊስ ተቋም ኢንተርፖል ማስተማመኛ ሰጠ፡፡

ትናንትና አዲስ አበባ የመጡት የኢንተርፖል ዋና ሀላፊ ዶ/ር ጀርጋን ስቶክ ከፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንዳሻው ጣሰው ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው ወሬው የተሰማው፡፡

ከንግግሩ በኋላ መግለጫ የሰጡት ኮሚሽነር ጀነራል #እንዳሻው_ጣሰው በኢትዮጵያ ወንጀል ሰርተው በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያንን ኢንተርፖል ለኢትዮጵያ አሳልፎ እንደሚሰጥ ማስተማመኛ ሰጥቷል ብለዋል፡፡

ኮሚሽነር ጀነራሉ በሰብአዊ ፍጡር ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙና ሀገር የዘረፉ ሰዎች ግማሾቹ በሀገር ውስጥ ግማሾቹ ደግሞ ባህር አቋርጠው በውጭ አገር እንደሚኖሩ ታውቋል ብለዋል፡፡

ይህንን ወንጀል ፈፃሚዎቹ የትም ይደበቁ የትም ይኑሩ ኢንተርፖል እጃቸውን አንጠልጥሎ ለኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያስረክብ ሀላፊው አረጋግጠውልናል ሲሉ መናገራቸውን ከመንግስታዊ ምንጮች ስምቻለሁ ብሎ ሸገር ዘግቧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሰሞኑ ባስተላለፉት መልዕክት በወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎች ማንም ይሁን ማን ከየትኛውም ብሔር ገብተው ይደበቁ፣ የትኛውም ወገን ይጩህላቸው በወንጀል እስከተጠረጠሩ ድረስ ካሉበት አድነን ለህግ እናቀርባቸዋልን ማለታቸው
ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የፕሬዘዳንት ግርማ የቀብር ስነ ስርዓት...

የቀድሞ ፕሬዚዳንት #ግርማ_ወልደጊዮርጊስ የቀብር ስነ ስርዓት የፊታችን ረቡዕ እንደሚፈፀም ተገለፀ።

የቀብር ስነ ስርዓቱም የፊታችን ረቡዕ ታህሳስ 10 2011 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ከቀኑ 10 ሰዓት ከ30 ላይ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንደሚፈፀመም ተነግሯል።

ከዛ ቀደም ብሎም ህዝቡ በተገኘበት ለአስከሬናቸው አሸኛኘት ስነ ስርዓት ይደረጋል የተባለ ሲሆን፥ ጊዜው እና ቦታው ወደፊት እንደሚገለፅም ታውቋል።

በአዋጅ ቁጥር 653/2009 አንቀፅ 11 ላይ በተደነገገው መሰረትም በመላው ሀገሪቱ የ1 ቀን ብሄራዊ ሀዘን የሚታወጅ ይሆናል። የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፊታችን ማክሰኞ ታህሳስ 9 2011 ዓ.ም በሚያደርገው ስብሰባው ብሄራዊ የሀዘን ቀኑን እንደሚያውጅ ይጠበቃል።

ይህንን ተከትሎም የሀገሪቱ ሰንደቅ ዓላማ በመላው ሀገሪቱ እንዲሁም በውጭ ሀገራት በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ የሚደረግ ይሆናል።

የቀብር ስነ ስርዓታቸውም ለክብራቸው እና ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋጽኦ ሚመጥን መልኩ እንደሚከናወንም ተገልጿል።

ይህንን ለመፈፀምም 11 ዓባላት ያሉት ብሄራዊ ኮሚቴ የተዋቀረ ሲሆን፥ የኮሚቴው አባላትም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር፣ ከፌደራል ፖሊስ እና ከሀገር መከላከያ የተውጣጡ መሆናቸውም ታውቋል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ🔝

ቡሌ ሆራ ከተማ ሰሞኑን ከነበረው አለመረጋጋት ተላቃ ወደሰላማዊ እና ወደቀደመው መደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች። የንግድ ተቋማት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ ነው። የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ወደነበረበት ተመልሷል።

ፎቶ፦ ገሜ(ቡሌ ሆራ TIKVAH-ETH)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወንጀል ነክ መረጃ‼️

#መሀመድ_ሁሴን 1ኛና #ዳኜ_አሰፋ 2ኛ ተከሳሽ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ክልል ልዩ ቦታው አፍሪካ ካፌ ውስጥ ህዳር 10 ቀን 2008 ዓ.ም ከረፋዱ 05፡30 ሰዓት ሲሆን በ1996 ዓ.ምየወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ እና 692/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በፈፀሙት አታላይነት ወንጀል ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

የክስ ዝርዝሩ እንደሚያስረዳው ተከሳሾች ለጊዜው ባልተያዘው ግብረ አበራቸው አማካኝነት የግል ተበዳይ አቶ ታዬ ጀቤሳን አግኝተው 1ኛ ተከሳሽ እኔ ጅንአድ ውስጥ ነው የምሰራው 400 ፍሬ ባለ25 ሊትር ዘይት ትወስዳለህ አብርንም እንሰራለን ህጋዊ ደረሰኝም እሰጥሀለሁ ክፈልና ትወስዳለህ በማለት ሲለው2ኛ ተከሳሽ ደግሞ ዘይቱ መኪና ላይ እስኪጫን ለመተማመኛ እንዲሆንህ ቼክ እሰጥሃለሁ በማለት 200,000 ሺህ ብር ከተቀበሉ በኋላ የተሰወሩ በመሆኑ በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት የአታላይነት ወንጀል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አራዳ ምድብ ጽ/ቤት ዐቃቤ ህግ ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ ደረቅ ቼክ ፅፎና ፈርሞ በመስጠቱ
ሁለተኛ ክስ መስርቶበታል፡፡

ዐቃቤ ህግ የተከሳሾችን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ሁለት የሰው ምስክሮችን በማቅረብ አሰምቶ የተከራከረ ሲሆን ተከሳሾችም ባለመከላከላቸው ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

በመጨረሻም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ወንጀል ችሎት ህዳር 27 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾችን ያርማል በማለት 1ኛ ተከሳሽ በ2 ዓመት ከ6 ወር እስራት እና 2000 ብር 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ በ2ዓመት ከ3 ወር እስራትና በ2000 ብር እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡

ምንጭ፦ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia