TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አርፈዋል!

* ለ12 ዓመተታት ያህል ሀገራችንን በፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል

* ከሁለት ሳምንት በኋላ ታህሳስ 19 በመኖሪያ ቤታቸው 95ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን በደማቅ ስነ ስርዓት ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነበር፡፡

* ዛሬ በሀርመኒ ሆቴል በኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ቀጠሮ ነበራቸው

#ግርማ_ወልደጊዮርጊስ ታህሳስ 19 ቀን በ1917 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ፤ በልጅነታቸውም የቤተክህነት ትምህርት ከተማሩ በኋላ፣ በ1926 ዓ.ም. በተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት ገብተው እስከ ጣልያን ወረራ ድረስ ዘመናዊ ትምህርት ተከታትለዋል፡፡

መቶ አለቃ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ከመስከረም 28 ቀን 1994 ዓ/ ም ጀምሮ ለሁለት ዙር እስከ መስከረም 27 ቀን 2006 ዓ/ም የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሆነው ያገለገሉ አዛውንትና ከዘውድ ስርዓት ጀምሮ በደርግ እና በኢሕአዴግ መንግሥት የሠሩ የቀድሞ ወታደር ናቸው። መቶ አለቃ ግርማ ኦሮሚኛ፣ አማርኛ፣ አፋርኛ፣ እንግሊዘኛ፣ ጣሊያንኛ እና ፈረንሳይኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ።

ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በ1930-33 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያትም በአዲስ አበባ “ዘ ስኮላ ፕሪንሲፔ ፒዮሞንቴ” በተባለው የጣሊያኖች ትምሕርት ቤት ገብተው ጣልያንኛ ቋንቋ አጥንዋል፡፡

በ1942 እና 1944 ዓ.ም. መካከለል ባሉት ጊዜያት ደግሞ በዓለም ዓቀፍ የሲቪል ማኅበር ድጋፍ በሚሰው የማሠልጠኛ መርኃግብር፣ ከሆላንድ አገር በአስተዳደር ሙያ፣ ከስውዲን አገር በአየር ትራፊክ አስተዳደር፣ እንዲሁም ከካናዳ አገር በአየር ትራፊክ መቆጣጠር የተለያዩ የምሥክር ወረቀቶችን አግኝተዋል፡፡

መንግሥታዊ፣ አስተዳደር ተሞክሮዎቻቸው፦

- በ1933 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች የሬዲዮ መገናኛ ክፍል ባልደረባ፣

- በ1936 ዓ.ም. ከገነት ውትድርና ማሠልጠኛ ት/ቤት የምክትል ሌፍተናንት ምሩቅ፣

- በ1938 ዓ.ም. የኢትዮጵያን አየር ኃይል በመቀላቀል ልዩ ልዩ አስተዳደራዊ ኮርሶችን ተከታትለዋል፤

- በ1940 ዓ.ም. በ አየር መቃወሚያና በረራ መቆጣጠሪያ ማዕከል ረዳት መምህር፣

- በ1947 የኤርትራ ፌዴራላዊ መንግስት የሲቪል አቪዬሽን የበላይ አዛዥ፣

- በ1951 ዓ.ም. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጠቅላይ ዳይሬክተር፣

- በ1953 ዓ.ም. የፓርላማ አባል፣

- ለሦስት ተከታታይ አመታት የፓርላማ ፕሬዝደንት፣

- በዓለም አቀፍ የፓርላማ ማኅበርም አገራቸው ኢትዮጵያ የፓርላማ መቀመጫ ታገኝ ዘንድ ከመስራታቸውም በላይ በስዊዘርላንድ፣ ዴንማርክና የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ ኮንፈረንስ ተካፋይ ትሆን ዘንድ ትልቅ አስተዋጽኦ ሲያበረክቱ፣ በ52ኛው ዓለማአቀፍ የፓርላማ ስብሰባ ላይ ተቀዳሚ ፕሬዝደንት፣

- በ1967 ዓ.ም. የንግዱን ማኅበረሰብ
በሲቪል ኮንሰልቲቭ ኮሚሽን እስከፈረሰበት ድረስ የውክልና አገልግሎት፣

- በአይ ኤም ፒ ኢ ኤክስ አስመጪና ላኪ፣

- በ1969 ዓ.ም. በጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት የኤርትራን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በተቋቋመው የሰላም ኮሚሽነር ፕሮግራም ተቀዳሚ ኮሚሽነር፣

- በ1992 ዓ.ም. በተደረገው 2ኛ ዙር ምርጫ፣ በምዕራብ ሸዋ ዞን፣ በቾ ወረዳ፣ በግል በመወዳደር የኢ. ፌ. ዲ. ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል፣

ከመንግሥት አስተዳደር ውጪ የሆኑ ተሞክሮዎቻቸው፦

- የኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤት የቦርድ አባል፣

- በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ ንግድ ልዑክ ወኪል፣

- የጊቤ እርሻ ልማት ማኅበር መስራችና ዳይሬክተር፣

- የከፋ ቲምበር ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ መስራችና ዳይሬክተር፣

- ከ1982 ዓ.ም. በፊት ደግሞ በኤርትራ አገር የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ኤርትራ ቅርንጫፍ ፕሬዝዳንት፣

- የቼሻየር ሆም የቦርድ ፕሬዝዳንት፣

- የሊፕረዚ መቆጣጠሪያ ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር፣

- በ1982 ዓ.ም. ከኤርትራ ሲመለሱም በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የቦርድ ዳይሬክተርና በዚሁ መስሪያ ቤት በዓለምአቀፍ ሎጅስቲክስ ዲፓርትመንት የበላይ ጠባቂ፣

- በ1983 ዓ.ም. ለም ኢትዮጵያ በተሰኘውና በአካባቢ ጥበቃ ላይ በሚሰራው ማኅበር የቦርድ ፕሬዝዳንት ሆነው ሲያገለግሉ፣

- ፕሬዝዳንቱ የኦሮሚኛ፣ አማርኛ፣ ትግሪኛ፣ ጣልያንኛ፣ እንግሊዘኛና ፈረንሳይኛ፣ በድምሩ የስድስት ቋንቋ ባለቤት ናቸው፡፡

- የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ ጊዮርጊስ ባለቤት ወ/ሮ #ሳሊም_ጳውሎስ በ89 ዓመታቸው አረፈዋል። የቀብር ሥነ ሰርዓታቸው ነሐሴ 11 ቀን 2009ዓ.ም. በእንጦጦ ገዳመ ኤልያስ ቤተ ክርሲቲያን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተፈጽሟል።

ፕሬዝዳንት ግርማ ባለትዳርና የአምስት ልጆች አባት ናቸው፡፡

ነፍስ ይማር!
***
እባክዎን ይህንን መልዕክት ሼር በማድረግ ይተባበሩን

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Fake Twitter Page Alert‼️

የትዊተር ገፁ "Egyptian local News" የሚባል ሲሆን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ አንዴ "ግብፅ በተዋጊ ጀቶች #ትመታዋለች" ሌላ ግዜ "ሰላዮቻችንን ልከን ቪድዮ እያስቀረፅን ነው" በማለት የኢትዮጵያውያንን ትኩረት ስቦ ቆይቷል። ይህ አንድ ሺህ የማይሞላ ተከታታይ ያለው የትዊተር ገፅ ሌላ የፌስቡክ፣ የጋዜጣ፣ የሬድዮ፣ የቲቪ ወይም የድረ- ገፅ አድራሻ የለውም። የትዊተር ሀንድሉ እራሱ "RenaissanceDam" መሆኑ ሲጨመር ኢትዮጵያውያንን ሆን ብሎ #ለማስፈራራት ወይም የሀሰት ዜና ስለ ግድቡ ለመልቀቅ ታስቦ የተከፈተ የሀሰት ገፅ መሆኑን ያሳያል።

via Eliyas Meseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
🕊ትግራይ🕊አማራ🕊

በትግራይና አማራ ህዝቦች መካከል ግንኙነት #ለማጠናከር ያለመ የሰላም ፎረም በመቀለ ዩኒቨርስቲ ተካሂዷል። በሁለቱም ህዝቦች መሀከል #ግጭት ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን የተባለው እንቅስቀሴ ለመግታት የሰላም ታጋይነትና ተሟጋችነት በመጠቀም የሚሰራበት መንገድ በፎረሙ ውይይት ተካሂዷል።

© VOA የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ🔝

የቡሌ ሆራ ከተማ ወደቀደመ #ሰላማዊ እንቅስቃሴዋ ብትመለስም በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተፈጠረው አለመረጋጋት ግን እስካሁን እልባት አላገኘም። ከላይ በፎቶው የምትመለከቱት ትላንት ምሽት ተማሪዎች ያደሩበትን ሁኔታ ነው። በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሚማሩ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት መንግስት ለተቋሙ አስቸኳይ መፍትሄ ለፈልግ ይገባል ብለዋል። ጥፋተኞች እና የተማሪውን #ደህንነት አደጋ ላይ የጣሉ እንዲሁም የተቋሙ ሰላም እንዲደፈርስ እጃቸውን ያስገቡ ሁሉ ተይዘው መጠየቅ አለባቸው ሲሉ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሞያሌ‼️

በሞያሌ ከተማ በተከሰተ ግጭት 21 ሰዎች #መሞታቸውንና 61 ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱን የሶማሌ ክልል  መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ  ገለጸ።

በሞያሌ ከተማና አከባቢዋ የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ውይይት እየተደረገ ነው።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ #ሱረው_መሐመድ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት በዜጎች ላይ ጉዳቱ የደረሰው ባለፉት ሁለት ቀናት በደረሱ ግጭቶች ነው።

በግጭቱ የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ወገኖችን ለመርዳት ሁለት ቡድኖች ወደ አካባቢው ተልከው ሕክምና መስጠት መጀመራቸውን ገልጸዋል።

በግጭቱ ከተፈናቀሉት ወገኖች የተወሰኑት ወደ ኬንያ #መሰደዳቸውንም አቶ መሐመድ ተናግረዋል።

በመከላከያ ሠራዊት ካምፕ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች ደግሞ የክልሉ መንግሥት እርዳታ ለማቅረብ እንቅስቃሴ ጀምሯል ብለዋል።

በሞያሌ ከተማና አከባቢዋ የሚከሰቱ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የፌዴራል፣የሶማሌና የኦሮሚያ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮችና ባህላዊ መሪዎች እየተወያዩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ መንግሥት በሞያሌ ከተማና አካባቢውና የሚታዩ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑን ምክትል ኃላፊው አስታውቀዋል።

ሕዝቡ የሁለቱ ክልሎችን ሕዝብ ወደ አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ለማስገባት የሚንቀሳቀሱ አካላትን እንቅስቃሴ ለማክሸፍ እንዲረባረብ አቶ መሐመድ ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሶሪያ ሰደተኞች በአዲስ አበባ‼️

ጉጉሻ የተባለ የTIKVAH-ETHIOPIA ቤተሰብ አባል ትላንት በአዲስ አበባ ከተማ መንገድ ላይ የሚለምኑ የሶሪያ ስደተኞችን በአይኑ በመመልከቱ ልቡ ተሰብሯል። ስደተኞቹ ሲለምኑ የሚያሳዩ ፎቶዎችንም አጋርቶኛል።

"እኛም ስለሰላም አጥብቀን ካልሰበክን እና ስለሰላም ተግተን ካልሰራን እጣ ፋንታችን ልክ እንደ ሶሪያዊያኑ ስደተኞች እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለኝም። ዛሬን #ሰላም ካልሰበክን #እመኑኝ አንድ ቀን እኛም በኬንያ ወይም በሌላ ሀገር መንገዶች ላይ ቁጭ ብለን #እንለምናለን!"

ያሳዝናል!!
ሰላም ዋጋዋ ትልቅ ነው!
#ሼር #Share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሀዘን መግለጫ‼️

ከጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ የተላለፈ የሃዘን መግለጫ፦

ከ1994 እስከ 2006 ዓም የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት በመሆን ያገለገሉት ክቡር ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ በማረፋቸው በኢፌዳሪ መንግሥት እና በራሴ ስም የተሰማኝን ጥልቅ #ኀዘን ለመግለጽ እወዳለሁ።

ክቡር ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የኢፌዲሪ መንግሥትን ለአስራ ሁለት ዓመት በፕሬዚዳንትነት ያገለገሉ፣ በልዩ ልዩ ኃላፊነት ለሀገራቸው ረዥም ዘመን የሠሩ፣ በዕውቀታቸውና በሞያቸው ለሕዝባቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የሰጡ፣ የታታሪነት፣ የቅንነትና፣ የሕዝባዊ አገልግሎት ሰጭነት ተምሳሌት ነበሩ።

በክቡር ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ዕረፍት ለቤተሰቦቻቸውና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን እመኛለሁ። መንግሥታዊ የቀብሩን ሥነ ሥርዓት የሚያስፈጽም ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን በቅርቡ አስፈላጊውን መግለጫ ይሰጣል።

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️መሳሪያ ታጥቀው ቤተ መንግስት ከገቡት ወታደሮች መካከል 66ቱ ከ5 ዓመት እስከ 14 ዓመት በሚደርስ ፅኑ #እስራት ተቀጡ። ወታደሮቹ በወታደራዊ ፍርድ ቤት #በግልፅ ችሎት #መዳኘታቸውን የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡

ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እንኳን ደስ ያለዎት! የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶክተር #ዐቢይ_አሕመድ_ዓሊ በአፍሪካን ሊደርሺፕ መጽሔት "የዓመቱ ምርጥ አፍሪቃዊ" ተብለው #ተመርጠዋል። እንኳን ደስ ያለዎት! እንኳን ደስ አላችሁ!

©አፈንዲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና‼️

ከነ #ትጥቃቸው ቤተ መንግሥት በገቡ የመከላከያ ሠራዊት ኮማዶዎች ላይ #የተላለፉ_ቅጣቶች ዝርዝር ይፋ ሆነ፦

1. አንድ ተከሳሽ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት

2. ሦስት ተከሳሾች በ13 ዓመት ጽኑ እስራት

3. 11 ተከሳሾች በ12 ዓመት ጽኑ እስራት

4. 12 ተከሳሾች በ11 ዓመት ጽኑ እስራት

5. አራት ተከሳሾች በ10 ዓመት ጽኑ እስራት

6. 16 ተከሳሾች ከ9 ዓመት እስከ ዘጠኝ ዓመት ከስድስት ወር ጽኑ እስራት

7. ሁለት ተከሳሾች በስምንት ዓመት ጽኑ እስራት

8. 10 ተከሳሾች ከሰባት ዓመት ከስድስት ወር እስከ ሰባት ዓመት ጽኑ እስራት

9. አምስት ተከሳሾች ከስድስት ዓመት ከስምንት ወር እስከ ስድስት ዓመት

10. አንድ ተከሳሽ በአምስት አመት ጽኑ እስራት ተቀጥተዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

ፍላሚንጎ ከሰንሻይ አጠገብ ከሚሰራው ህንፃ ላይ ሁለት የኮንስትራክሽን ሰራተኞች #ወድቀው አንደኛው ህይወቱ አልፏል። አንደኛው ለህክምና እርዳታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል። ፖሊስ ጉዳዩን እያጣራ ይገኛል።

ምንጭ፦ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia