TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አፋን ኦሮሞ📌የ6ኛ ቀን ትምህርት እንዲሁም የ7ኛ እና 8ኛ ቀን ትምህርት ከነገ እስከ እሁድ ድረስ በ @TIKVAHETHEDU ይስጣል። በማስከተልም #በድምፅ ቋንቋውን የሚያሰተምሩ የቋንቋን ተናጋሪዎች ይቀላቀሉናል።

የትግርኛ ቋንቋ ትምህርት ሙሉ ዝግጅት እየተጠናቀቀ በመሆኑ ጥቂት ጊዜ ትታገሱን ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ።

23,000 በላይ ኢትዮጵያዊያን በአጭር ጊዜ ውስጥ የTIKVAH-EDU አባላት ሆነዋል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA(ተስፋ ኢትዮጵያ)!

በሺዎች የሚቆጠሩ አስተያየቶችን አንብቢያለሁ አብዛኛው ገንቢ እና አበረታች ነው። የሚያኮራና እኔ እንዲህ ነኝ የሚያስብል ሳይሆን ተጨማሪ ሰዓት ጨምሬ አንገቴን አቀርቅሬ እንድውል የሚያደርገኝ ነው። ትልቅ ሀላፊነት ነው ያሸከማችሁኝ። በነገራችን ላይ በስድብ ያጠረገረጉኝም እንደውም ከአንዱ #ብሄር አስገብተውኝ ለመሳደብ፤ ሞራሌን ለመንካት የጣሩም አሉ ግን ይህ የሚጠበቅ ነገር በመሆኑ እየሳቅኩ እና ለሰደቡኝ ሰዎችም ፈጣሪ ማስተዋልን እንዲሰጣቸው እየለመንኩ ነው ያነበብኩት። በአጠቃላይ ሁላችሁንም ከልቤ ተንበርክኬ አመሰግናለሁ። እውነት ተስፋ ሆናችሁኛል። ምኖርለት ነገር እንዳለኝ አሳይታችሁኛል።

*ፀጋአብ ወልዴ* ሰው ነኝ ሲቀጥል ኢትዮጵያዊ #ብቻ ነኝ!! እኔ እራሴን ማስበው ፈጣሪ ለሰው ልጅ ሁሉ የፈጠረኝ አድርጌ ነው። የሰዎችን ብሄር፣ እምነት እና ባህል እጅግ በጣም አከብራለሁ። እኔ ግን ከሁሉም ነኝ! እኔ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ሱማሌ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ....ነኝ! የአንዱ ብቻ ሆኜ መኖር አልፈልግም። እንዲህ መኖር አትችልም ሰው ሆነህ መኖር አትችልም የሚለኝ አካል ከሀገሬ ያስወጣኝ።

እኔ እንደሰው የሁሉም ስቃይ እንዲሰማኝ፣ የሁሉም መከራ እንዲያሳዝነኝ፤ የሌላው ችግር የኔም ችግር እንደሆነ እንዲሰ ማኝ እፈልጋለሁ። ወዳጆቼ ከየትም ብሄር ይሁኑ እደሰው ስለማከብራቸው ቋንቋቸውን፤ ባህላቸውን እምነታቸውን አከብርላቸዋለሁ። እኔ ግን የሁሉም ሰው ልጅ ነኝ! ብሄሬ የሚያስጨንቀው ሰው ካለ ይህ ነው መልሴ እኔ ኦሮሞ፣ አማራ፣ ትግሬ፣ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ከንባታ፣ ሱማሌ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ...ሁሉም ነኝ!

ሰው ሆኜ ስለተፈጠርኩ የሰው ሁሉ ስጦታ ነኝ!! ይህን ለማለት ያስገደደኝ ብሄር ተኮር ስድብ ስላስተናገድኩ ነው።

ወደ ቻናላችን ስመለስ....

1. ቻናሉን የትኛውም ድርጅት እና ግለሰብ ስለማያግዘው አሁንም ወደፊትም በማስታወቂያዎች ብቻ ነው የሚዘልቀው። ቻናሉ ብቻ ሳይሆን ምርታቸውን የሚያስተዋውቁ አካላትም የስራ እድላቸው ይሰፋል።

🔹ብዙዎች የማስታወቂያ መብዛት ቅር እንዳሰኛችሁ ግልፃችኃል ማስታወቂያዎች ይቀነሳሉ ለዚህም ዝግጅት ተደርጓል። አሁን እየተሰራበት ያለውም አሰራር ስንቀይረው በቀን የሚቀርበው ማስታወቂ ቁጥር ለመቀነስ ይሞከራል።

2. መረጃ ከበፊቱ እጅግ በጣም በተሻለ ፍጥነት ይቀርባል። ምንጮች የመንግስት ሚዲያዎች፣የግል ሚዲያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ እንዲሁም የTIKVAH-ETH የአይን እማኞች ይሆናሉ።

3. በየከተማው ያለ የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎች ከበፊቱ በተሻለ ይቀርባል።

4. በቀን የተመጠኑ መረጃዎች ይቀርባሉ። መረጃ ነው እየተባለ እያመጣሁ ከዚህ በኃላ አለጥፍም። ጥራት እና ለህዝብ ጠቃሚነቱን አይቼ አቀርባለሁ።

5. አሁንም ገለልተኛ ሆኖ የሁሉም ድምፅ ይቀርብበታል።

6. በፍፁም የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት ልሳን ሆኖ አሰራም።

7. ዜናዎችን በፍጥነት ለማቅረብ ይሞከራል ። ፍጥነት ከጥንቃቄ ጋር ስለሆነ ወዲያው የሚሰራጩ መረጃዎች ችግር ፈጣሪም ስለሚሆኑ ጥንቃቄ ይደረጋል።

8. ከተለያዩ ገፆች መረጃዎችን ቀጥታ የማቀርበው በፌ ቡክ ያለውን የስድብ ኮሜንቶች እንድታነቡት ስለማልፈልግ ነው። ብዙ የtikvah ቤተሰብ አባላት ራሳቸውን ከፌስቡክ እያራቁ እንደሆነ ነግረውኛል።

የተጨመሩ፦

TIKVAH-ETH በአፕሊኬሽን ከሚተላለፉት ዜናዎች በተጨማሪ፦

.ምልከታዎች

.የውጭ ዜናዎች

.ጥቆማ

.ውይይት

. #UpdateSport የየዕለቱ ስፖርታዊ የሆኑ ጥቂት መረጃዎች

.የመዝናኛ ወሬዎች ከሀገር ውስጥ እና ከውጭ

.የቴክኖሎጂ ዜናዎች

.ልዩ ልዩ፦ ድንቃድቅ እውነታዎች

.🔹ላስተዋውቃችሁ🔹ይህ የምትኖሩበትን አካባቢ የምትገልፁበት መንገድ ነው። ከተማችሁን ታስተዋውቋታላችሁ። 15 መስመር በመሆን ፅሁፍና በፎቶ!

.የሙዚቃ ምርጫ(ሀገራዊ እና እጅግ በጣም አስተማሪ የሆኑ ሙዚቃዎች እጠቁማችኃለሁ)

.ቲፕ

ከላይ የተጨመሩት ቻናሉን የበለጠ ማራኪ ለማድረግ ታሶቦ ነው። ትልቁ ስራ ከመላው ኢትዮጵያ ምን እየሆነ እንዳለ እና በየቦታው ያሉትን መረጃዎች መዳሰስ ነው።

ሌላው አዲሱ ነገር ከዚህ ቀደም በአማርኛ ከእናተ የሚላኩ መረጃዎች የሚቀርቡ ሲሆን በእንግሊዘኛ ፅሁፍ የሚቀርቡትን ግን የመቅረብ እድላቸው አነስተኛ ነው በመሆኑም #በድምፅ መረጃዎችን ላኩ!! በድምፅ መረጃ ማስተላለፍ መጀመራችንን ስናበስ በደስታ ነው😁

🔹ማስታውቂያ የምታስነግሩ፦

1.ህጋዊ ብቻ
2.ተጠያቂ
3.እናተም ብቻ ሳይሆን ተገልጋዩን የሚጠቅም
4.አገልግሎት ሰጪዎች
5.በስራ ላይ የማይንቀሳቀሱ እና እንደው ለጊዜው ብቻ የተከፈቱ ቻናሎች አይተዋወቁም

🔹የተሻሻለውም የማስታወቂያ ህግ እና የአሰራር ሁኔታ ድርጅቶች ማየት ትችላላችሁ።

(ኮንትራት ያልጨረሳሁትን አይመለከተም። እናተ ያላችሁ ኮንትራት ሲያልቅ አዲሱን አሰራር ማየት ትችላላችሁ)

ይህ ለማድረግ የተገደድነው ገዘንብ ለማግበስበስ እና ትርፋማ ለመሆን አይደለም ማስታወቂያዎችን ለመቀነስ ብቻ ነው!!

ቻናሉ ገንዘብ ለመሰብሰብ እና ለማግበስበስ የተቋቋመ አይደለም! ሰዎችን እናግዝ ሰርተን አብረን እንስራ!!

ሌሎቹም በተመለከተ፦

.TIKVAH-EDU ለአሁን 2 ቋንቋዎች ላይ ይሰራል። ከቋንቋ በተጨማሪ ሌሎች ትምህርት ነክ ጉዳዮች ያስተናግዳል።

.TIKVAH-AID ሁሉም የሚሳተፍበት እና እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በግላቸው አካውንት የምናግዝበት ነው። እንዲሁም አነቃቂ የእንተጋገዝ መልዕክቶች የሚቀርቡበት ነው።

.TIKVAH-AID 2 ይህ በኛው አካውንት እያሰባሰብን ለሰዎች የተለያዩ ድጋፎች የምናደርግበት እና የተስማሙ ብቻ የገቡበት ነው።

.TIKVAH-UNIVERSITY በዩኒቨርሲቲዎች ዙሪያ ሰፊ ስራ ለመስራት የሚቻልበት በየግቢው ያሉ እንቅስቃሴዎች የሚቀርቡበት ነው። የተለያዩ ማዕበራት በዚህ ላይ ተሳታፊ ሁኑ! አድሚም ሆናችሁ የግቢያችሁን ሁኔታ እና እንቅስቃሴ ለሌሎች አጋሩ!

አመሰግናለሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia